በድሬዳዋ አስተዳደር በጎዳና ተዳዳሪና አካል ጉዳተኛ ህፃናት ዙሪያ ለመስራት የሚያስችል ፕሮጀክት በዛሬው እለት በይፋ ተጀመረ ።
ኤስ ኦ ኤስ የህፃናት መንደር ፕሮግራም መንግስታዊ ያልሆነ አለም አቀፋዊ የበጎ አድራጎት ድርጅት ሲሆን በሀገራችን ኢትዮጲያ ወላጆቻቸውን በተለያየ ምክንያት ያጡ ህፃናትን አሰባስቦ ከለላ በመስጠት ራሳቸውን ችለው ሀገራቸውን እንዲያገለግሉ የሚያደርግና የቤተሰብ ማጠናከሪያ ፕሮግራሞችን በመቅረፅ ለቤተሰብና ለማህበረሰብ ተቋማት ድጋፍ በመስጠት ቤተሰብ እንዲጠናከርና ልጆች የመብቶቻቸው ተጠቃሚ ይሆኑ ዘንድ የሚሰራ ተቋም ነው ። ኤስ ኦ ኤስ በድሬዳዋ አስተዳደር ከማርች…


