የአስተዳደራችን ነዋሪዎች በክረምት በጎ ፍቃድ የጤና ምርመራና የህክምና አገልግሎት ዘመቻን በመጠቀም ያለምንም ክፍያ የጤና ምርመራ ማድረግ እንደሚገባቸው ተጠቆመ፡፡

    ‹‹በጎነት ለጤናችን›› የሚል መሪ ሃሳብ ያለው የነፃ የጤና ምርመራና ህክምና የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ዘመቻ በዛሬው ዕለት የአስተዳደሩ ከንቲባ ክቡር አቶ ከድር ጁሃርና የድሬዳዋ አስተዳደር የመንግስት ተጠሪ አቶ ዩሱፍ ኢብራሂም እንዲሁም ሌሎች የአስተዳደሩ ከፍተኛ አመራሮችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት በይፋ ተጀምሯል፡፡ በመክፈቻ መረሃ-ግብሩ ተገኝተው የክረምት የበጎ ፍቃድ አገልግሎት ነፃ የጤና ምርመራና ህክምና ዘመቻውን በይፋ ያስጀመሩት የአስተዳደሩ…

    Read More

      በድሬዳዋ አስተዳደር በክረምት በጎ ፍቃድ አገልግሎት ከነሃሴ 16-21/2014 ዓ/ም 5000 ለሚሆኑ መክፈል ለማይችሉ የከተማችን ነዋሪዎች የነፃ ምርመራና ህክምና አገልግሎት ይሰጣል።

      ከነሃሴ 16/2014 ዓ.ም ጀምሮ ለአንድ ሳምንት በሚቆየው በዚህ “በጎነት ለጤናችን” የነፃ ምርመራና ህክምና የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ዘመቻ ወቅት የተጠናከረ የጤና አጠባበቅ ትምህርት፣የደም ግፊት ምርመራና ህክምና ፣የደም ውስጥ ስኳር ምርመራና ህክምና እና ሌሎችም ያለምንም ክፍያ የሚሰጡ ይሆናል። በአስተዳደራችን በዋናነት 3 ግዜያዊ የነፃ ምርመራና ህክምና ጣቢያዎች የሚቋቋሙ ሲሆን የታሰቡት ቦታዎችም 1. ምድር ባቡር አደባባይ 2. ኮኔል ድልድይ…

      Read More

        #ስንተጋገዝ ሸክማችን ይቀልላል፤ ስንደጋገፍ የበለጠ #እንጠነክራለን።

        በውጭና ሀገር ውስጥ የሚገኙ ቅን የድሬዳዋ ልጆች እና ወዳጆች ተባብረው፤ ለመልካ አቡነ አረጋዊ የሴቶች ገዳም መነኮሳት እና እህቶቻቸው ያደረጉት ድጋፍ የሰብዓዊነት ማሳያ በጎ ተግባር ነው። #ለገዳሙ የዳቦ መጋገሪያ ማሽን፣ ለጾም መፍቻ የሚሆን ሰንጋ እንዲሁም ሌሎች ስጦታዎችን፤ ላበረከታችሁ #የትንሿ_ኢትዮጵያ የድሬ ልጆች፤ የአክብሮት ምስጋናዬን አቀርባለሁ። ትውልድ የሚያንፁ እናቶቻችንን ቀሪ ጉድለት በምንችለው አቅም ለመሙላት ቃል እገባለሁ።

        Read More

          የብልፅግና ፓርቲ የድሬዳዋ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት የ 2014 በጀት አመት የማጠቃለያ ኮንፍረንስ አካሄደ ።

          በዛሬው እለት በኢትዮ-ጣሊያን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ መሰብሰቢያ አዳራሽ የብልፅግና ፓርቲ የድሬዳዋ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት የ 2014 በጀት አመት የማጠቃለያ ኮንፍረንስ በደመቀ ሁኔታ የተካሄደ ሲሆን በዚሁም መድረክ ላይ በመገኘት ንግግር ያደረጉት የፓርቲዉ መዕከላዊ ኮሚቴ አባል እና የአሰተባባሪ ኮሚቴ ሰብሳቢ የሆኑት የአሰተዳደሩ ከንቲባ አቶ ከድር ጁሀር የብልፅግና ፓርቲ በሀገራችን ኢኮኖሚያዊ ፣ ማህበራዊና ፖለቲካዊ አመራር የሚፈልቀው ህገ-መንግስታዊ በሆነ…

          Read More

            ወጣቶች በሥራ ላይ የሚያተኩሩ፤ ሀገራቸውን ለማወቅ የሚተጉ፣ የሀገራቸውን ጸጋ የሚያለሙ፣ ፈጣሪያቸውን አመስጋኝ መሆን አለባቸው። ሀገራቸው ኢትዮጵያ ትልቅ እንደ ነበረች አስታውሰው ወደ ቀደሞ ከፍታዋ እንድትመለስ በኅብረ ብሔራዊ አንድነት ማጽናት የዚህች ድንቅ ሀገር ልጆች ግዴታ ነው። ክቡር ጠ/ሚ ዶ/ር አብይ አህመድ

            Read More

              በውጭና ሀገር ውስጥ የሚገኙ ቅን የድሬዳዋ ልጆችና ወዳጆች ተባብረው ለመልካ አቡነ አረጋዊ የሴቶች ገዳም መነኮሳት እና እህቶቻቸው ያደረጉት ድጋፍ የሰብዓዊነት ማሳያ በጎ ተግባር በመሆኑ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ክቡር ከንቲባ ከድር ጁሀር ገለጹ

              በዛሬዉ ዕለት በዉጪ ሀገር የሚኖሩ የድሬዳዋ ተወላጆችና ወዳጆች መልካ በሚገኘዉ አቡነ አረጋዊ የሴቶች ገዳም በመገኘት የተለያዩ ድጋፎችን አበርክተዋል በድጋፍ አሰጣጥ ስነ ስርአቱ ላይ የተገኙት ክቡር ከንቲባ ከድር ጁሀር ለገዳሙ ለተደረገዉ ድጋፍ የተሰማቸዉን ልባዊ ደስታ የገለጹ ሲሆን ከተማችንን በማሳደግ ህብረተሰባችንን መለወጥ እንድንችል የመተባበር፣መደጋገፍ እና የመተጋገዝ ባህላችን በእጅጉ ማደግ አለበት ብለዋል ክቡር ከንቲባዉ ። በእለቱ ለገዳሙ የዳቦ…

              Read More

                የብልፅግና ፓርቲ የድሬዳዋ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት የ 2014 በጀት አመት የማጠቃለያ ኮንፍረንስ በኢትዮ-ኢጣሊ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ መሰብሰቢያ አዳራሽ እየተካሄደ ይገኛል ።

                በዚሁም የውይይት መድረክ ላይም የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ከድር ጁሀርን ጨምሮ በምክትል ከንቲባ ማእረግ የመንግስት ተጠሪና የብልፅግና ፓርቲ የድሬዳዋ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ሀላፊ አቶ ኢብራሂም ዩሱፍ ፣ የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ የተከበሩ ወ\ሮ ፈቲህያ አደን ፣ የድሬዳዋ አስተዳደር የካቢኔ አባላት ፣ የብልፅግና ፓርቲ የድሬዳዋ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት አመራሮችና አባላት እንዲሁም የተፎካካሪ ፓርቲ አመራሮች ተሳታፊ…

                Read More

                  የድሬዳዋ አስተዳደር ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ እና የድሬዳዋ አስተዳደር ፍትህ ፀጥታና ህግ ጉዳዮች ቢሮ የብልፅግና ፓርቲ መሠረታዊ ድርጅት የ2014ዓ.ም ማጠቃለያ ኮንፍረንስ ተካሄደ።

                  በማጠቃለያ ኮንፍረንሱ የመሠረታዊ ድርጅቱ የ2014 ዓ.ም እቅድ አፈፃፀም ሪፖርት እንዲሁም የ2015 ዓ.ም እቅድ በዝርዝር የቀረበ ሲሆን በኮንፍረንሱ ተሳታፊ በሆኑ የፓርቲው አባላት እና አመራሮችም ሰፊ ወይይት ተደርጎበታል። የቀጣይም በ2014ዓ.ም የእቅድ አፈፃፀም የነበሩ መልካም ስራዎችን አጠናክሮ በማስቀጠል እንዲሁም የታዩ ክፍተቶችን በመለየት እና በኮንፍረንሱ ማጠቃለያ ከተሳታፊዎች የተነሱ ሀሳቦችን በግብዓትነት በመውሰድ በ2015 ዓ.ም የመሠረታዊ ጅርጅቱን አፈፃፀም የተሻለ ለማድረግ ሁሉም…

                  Read More