የዴንጊ ትኩሳት በሽታ ወረርሽኝ በአስተዳደራችን መከሰቱና የጥንቃቄ እርምጃዎች መውሰድ እንደሚገባ ተጠቆመ፡፡
የደንጊ ትኩሳት በሽታ ወረርሽኝ በየዓመቱ ዝናብን ተከትሎ እንደሚከሰት የሚታወቅ መሆኑንና በዚህ ዓመትም 87 ናሙና ወደ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ተልኮ 4 ሰዎች በደንጊ ትኩሳት በሽታ መያዛቸውን የሚያረጋግጥ የምርመራ ውጤት መገኘቱን የድሬዳዋ አስተዳደር ጤና ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ለምለም በዛብህ ለሚዲያ ባለሞያዎች በሰጡት መግለጫ ተናግረዋል፡፡ ኃላፊዋ አያይዘውም የዴንጊ ትኩሳት በሽታ በፍጥነት የሚተላለፍና እስከሞት የሚያደርስ በመሆኑ ህብረተሰቡና ፅዳትና ውበት…


