የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ በገንደ ተስፋ ለገ-ኦዳ አካባቢ ለሚኖሩ የማህበረሰብ ክፍሎች ያሰራቸውን ሶስት የቦኖ ውሀዎች አስመርቋል ።
የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ከሚያከናውናቸው የመማር ማስተማርና የምርምር ስራዎች ባሻገር በተለይም የነዋሪውን ህብረተሰብ ችግር ሊፈቱ የሚችሉ የተለያዩ ማህበራዊ ስራዎችን በማከናወን ላይ ይገኛል ። ከዚሁ ጋር ተያይዞም የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ በገንደ ተስፋ ለገ-ኦዳ አካባቢ ለሚኖሩ የማህበረሰብ ክፍሎች በእጅግ የሚያገለግሉና ከ 450 ሺህ ብር በላይ ወጪ የተደረገባቸው ሶስት የቦኖ ውሀዎችን ከፍተኛ የአስተዳደሩ አመራሮች በተገኙበት አስመርቋል ። በዚሁም የምረቃት ስነ-ስርአት ላይ…


