የኢትዮጵያን እናልብስ አረንጓዴ አሻራ ዘመቻ መርሃ ግብር በድሬደዋ አስተዳደር ደረጃ ሁለት ሚልየን ችግኝ ለመትከል መታቀዱ ተገለጸ::
ሃሙስ ሃምሌ 28 በአንድ ጀምበር ግማሽ ሚልየን ችግኝ ለመትከል ቅደመ ዝግጅቶች መጠናቀቃቸውን የድሬደዋ አስተዳደር ውሃ ማዕድንና ኢነርጂ ቢሮ ኃላፊ አቶ ኢብራሂም ይሱፍ ተናግረዋል ፡፡ እንደ ኃላፊው ገለጻ የችግኝ መትከል መርሃ ግብሩ ህጻናትን ጨምሮ የሃይማኖት አባቶች ፤ የሃገር ሽማገግሌዎች ፤ ዑጋዞች እንዲሁም የመንግስት ሰራተኞች ተሳታፊ እንደሚሆኑ አስረድተዋል፡፡ በቀጣይ ከድሬደዋ ባለፈ ለጎረቤት ሃገራት የሚሆን አንድ ቢሊየን ችግኝ…


