ምርጫው በሰላማዊ መንገድ እየተካሄደ እንደሚገኝ የድሬዳዋ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ

    ሰኔ 14/2013 ምርጫው በሰላማዊ መንገድ እየተካሄደ እንደሚገኝ የድሬዳዋ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ። የአስተዳደሩ የፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር አለሙ መግራ ለፋና እንደተናገሩት ምርጫው በሠላም ይጠናቀቅ ዘንድ ዘርፈ ብዙ ስራዎች መሠራታቸውን ገልጸዋል። ይህም ለማድረግ ያስችል ዘንድ የተለያዩ የአስተዳደሩ የፀጥታ አካላት ከህብረተሰቡ ጋር በመሆን ከቅድመ ምርጫ ዝግጅት ጀምሮ በቅንጅት ሲሰራ መቆየቱን አስታውቀዋል። ምንጭ፡-ከዋልታ

    Read More

      የድሬዳዋ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አቶ አህመድ መሐመድ ድምጽ ሰጡ ሰኔ 14 ፣ 2013 የድሬዳዋ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አቶ አህመድ መሐመድ ቡህ በስድስተኛው ሃገራዊ ምርጫ ድምፃቸውን ሰጡ።

      በድሬዳዋ አስተዳደር በከዚራ መንደር ሁለት የምርጫ ጣቢያ ተገኝተው ድምፃቸውን የሰጡት አቶ አህመድ በድሬዳዋ ዛሬ በሁሉም የምርጫ ጣቢያዎች ምርጫው በሠላም እየተካሄደ መሆኑን ገልፀዋል፡፡ ምክትል ከንቲባው ድምፃቸውን ከሰጡ በኋላ ችግኝ በመትከል አረንጓዴ አሻራቸውን አኑረዋል። ምንጭ፡-FBC

      Read More

        በድሬዳዋ አስተዳደር በሚገኙ አራት የገጠር ክላስተር የሚገኙ ከ 1150 በላይ የሚሊሻ አባላት የአጭር ጊዜ ስልጠና በመስጠት ተመረቁ ።

        በድሬዳዋ አስተዳደር 6 ተኛው ሀገራዊ ምርጫን ተከትሎ በአስተዳደሩ የሚወዳደሩ ተፎካካሪ ፓርቲዎች የምርጫ ቅስቀሳቸው ፍፁም ሰላማዊ በሆነ መንገድ በከተማዋ የተለያዩ አካባቢዎች አካሂደዋል ። ከዚሁ ጋር ተያይዞም የፊታችን ሰኞ የሚካሄደው ሀገራዊ ምርጫ ፍፁም ሰላማዊና ያለምንም የፀጥታ ችግር ምርጫው ተጀምሮ ይጠናቀቅ ዘንድ በተለይም በድሬዳዋ አስተዳደር በሚገኙ አራት የገጠር ክላስተር ለሚገኙ ከ 1150 በላይ የሚሊሻ አባላት የአጭር ጊዜ ስልጠና…

        Read More

          6ኛው አገራዊ ምርጫ ሊካሄድ አንድ ቀን ብቻ ቀርቶታል፤ምርጫ በሚካድባቸው የአገሪቱ አካባቢዎች ያለውን አጠቃላይ ዝግጅትና ድባብ እንዴት ታዘቡት? የነገው ምርጫ ሰላማዊ እና ስኬታማ ሆኖ እንዲጠናቀቅ ከተፎካካሪ የፖለቲካ ድርጅቶች፣ ከመንግስት እና ከህብረተሰቡ በተለይ ከእያንዳንዱ ዜጋ ምን ይጠበቃል ይላሉ? የእርስዎን ሀሳብ ያጋሩን፡፡

          Read More

            ምስራቃዊ የእድገት ፋና የበጎ አድራጎት ማህበር 6 ተኛውን ሀገር አቀፍ ምርጫ ለመታዘብ ለተመረጡ ታዛቢዎች የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ አዘጋጅቷል ።

            በ 2001 ዓ.ም የተመሰረተው ምስራቃዊ የእድገት ፋና የበጎ አድራጎት ማህበር በድሬዳዋ አስተዳደር በሚገኙ በከተማም ሆነ በገጠር ጤና ላይ ፣ ትምህርት ፣ ኤች.አይ.ቪ እንዲሁም የተለያዩ ማህበራዊ ስራዎችን በመስራት ላይ ይገኛል። ምስራቃዊ የእድገት ፋና የበጎ አድራጎት ማህበር እያከናወናቸው ካላቸው ዘርፈ-ብዙ የማህበራዊ አገልግሎት ስራዎች በዘለለ የፊታችን ሰኞ የሚካሄደውን 6 ተኛውን ሀገራዊ ምርጫ ተከትሎ ምርጫው ሰላማዊና ፍትሀዊ በሆነ አግባብ…

            Read More

              በታሪካዊው ቀን ታሪክ እንስራ ሰኞ ሰኔ 14 ቀን 2013 ዓ.ም የድምፅ መስጫ ቀን ዜጎች በሀገራቸው ጉዳይ ላይ የሚወስኑበትና ዲሞክራሲያዊ መብታቸውን የሚያረጋግጡበት ቀን ነው።

              ይህንን ታሪካዊ ቀን “ኢትዮጵያን እናልብሳት” በሚል መሪ ቃል እየተከናወነ ያለውን 3ተኛውን የአረንገጓዴ አሻራ ቀን ምክንያት በማድረግ “ምርጫዬን እመርጣለሁ አረንገጓዴ አሻራዬን አኖራለሁ” በሚል መርህ በዚህ ታሪካዊ ቀን ታሪክ እንስራ ፡፡ ስለሆነም መምረጥ ዲሞክራሲያዊ መብታችን ነው ችግኝ መትከል ግን ታሪካዊ ግዴታችን ፤ በመሆኑም በእለቱ ምርጫ እየመረጥን በነብስ ወከፍ 6 ችግኞችን በመትከል ኢትዮጵያን አረንገጓዴ በማልበስ በታሪካዊው ቀን ታሪክ…

              Read More

                የምርምር ጽሁፎች ማቅረቢያ መጽሔት በምሁራን መካከል ጠንካራ ትስስር እንዲኖር ትልቅ አስተዋፆኦ እንደሚኖረው ተገለፀ ።

                የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ሃርላ የተሰኘ የምርምር ጽሁፎች ማቅረቢያ መጽሔት (journal) አስመረቀ፡፡ በድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ የምርምርና ማህበረሰብ አገልግት ምክትል ፕሬዝዳንት ፅህፈት ቤት የተዘጋጀውና ከድሬዳዋ ከተማ 12 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በምትገኘው ጥንታዊዋ የሃራላ ከተማ ስም የተሰየመው የምርምር ጽሁፎች ማቅረቢያ መጽሔት (journal) በድሬዳዋ ዩኒቨርስቲ ተመርቋል ። በዚሁም የምረቃ ስነ-ስርዓት ላይ በመገኘት ንግግር ያደረጉት የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት የሆኑት ዶክተር ኡባህ…

                Read More

                  ለበርካታ የአስተዳደሩ ነዋሪዎች የስራ እድል የፈጠረውን የራይት የወንዶችና የሴቶች የውበት ሳሎንን የአስተዳደሩ ከፍተኛ አመራሮች ጎብኝተውታል ።

                  እ.ኢ.አ በ 1991 ዓ.ም በአንድ ደንበርካ ፣ በሁለት ሰከንድ አንድ ማሽን ፣ የጫት ሽርጥና አሮጌ ቴፕ በመያዝ ስራውን ” ሀ ” ብሎ የጀመረው የራይት የወንዶችና የሴቶች የውበት ሳሎን ባለቤት አቶ መዝገቡ ልኡለቃል ወይም በቅጥል ስሙ አብዛኛው የከተማችን ነዋሪዎች የሚያውቁት ኑኑሼ በርካታ የኑሮ ውጣ ውረዶችን በማሳለፍ አሁን ላይ በከተማችን ድሬዳዋ በግንባር ቀደምትነት የሚጠራ የወንዶችና የሴቶች የውበት…

                  Read More

                    4 ሚሊዮን ብር በሆነ ወጪ በህብረተሰቡና በመንግስት የጋራ ስራ የተሰሩ የልማት ፕሮጀክቶች የምርቃትና የጉብኝት መርሀ-ግብር ተካሂዷል ።

                    የተለያዩ ማህበራዊ ፣ ኢኮኖሚያዊ የልማት ዘርፎችና ፕሮጀክቶች ውጤታማ የሚሆኑት በተጠናከረ የህብረተሰብ ተሳትፎ ሲሆን በሀገር አቀፍ ደረጃም ሆነ በየአካካባቢው ለሚሰሩ የልማት ፕሮጀክቶች ስኬታማነት የህብረተሰብ ተሳትፎን ማረጋገጥ የሚቻለው በየደረጃው የሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎችን የልማት ጥያቄ መነሻ ያደረጉ የአካባቢ ልማቶችን በመለየት ቅደም ተከተል በመስጠትና የህብረተሰቡን የገንዘብ ፣ የቁሳቁስና የጉልበት አስተዋፆ ወደ ላቀ ደረጃ በማሸጋገር ነው ። ከዚሁ ጋር ተያይዞም…

                    Read More

                      የብልፅግና ፖርቲ ድሬደዋ አስተዳደር በቢዮ አዋሌ ክላስተር አዋሌ ቀበሌ ከነዋሪዎች ጋር የምረጡኝ ቀስቀሳ አካሂዷል።

                      በቀስቀሳ ላይ ፖርቲው በማህበራዊ ÷ በኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ዘርፍ በቀጣይ የሚያከናውናቸው እቅዶች ገለፃ የተደረገ ሲሆን በዋናነት ከነዋሪው የሚነሱ የልማት ጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠት እንደሚንቀሳቀስ ተገልጿል። በፖርቲው ስር አዋሌቀበሌን ወክለው ለድሬደዋ ምክርቤት የሚወዳደሩ ሶስት እጩዎችን ማለትም:- * አቶ ኑረዲን መሀመድ *ወ/ሮ ሳኒያ ሙስጠፋ *አቶ ሙራድ ሙክታር ለቀበሌው ነዋሪዎች አስተዋውቋል በተጨማሪ አቶ ኑረዲን መሀመድ እንዳሉት ፖርቲያችን ብልፅግናን ከመረጣቹ በቀበሌ…

                      Read More