ህዝቡ ለሰራዊቱ እየሰጠ ያለው ድጋፍና ክብር ዘመቻውን በፍጥነት ለመቋጨት ጉልበት ነው – የአየር ኃይል ምስራቅ ምድብ
መላው ህዝብ ለሀገር መከላከያ ሠራዊት እየሰጠ ያለው ድጋፍና ክብር የህግ የበላይነት ለማረጋገጥ እየተካሄደ ያለው ዘመቻ በፍጥነትና በስኬት እንዲጠናቀቅ አቅም የሚፈጥር መሆኑን የኢፌደሪ አየር ኃይል የምስራቅ ምድብ ዋና አዛዥ ኮሎኔል አበበ ለገሰ አስታወቁ፡፡ በድሬዳዋ አስተዳደር የጀልዴሳ ገጠር ክላስተር ነዋሪ አርብቶ አደሮች ለሀገር መከላከያ ሠራዊት 430 ሺህ ብር የሚያወጡ ስምንት ግመሎችና አንድ ሰንጋ ትናንት በድጋፍ አበርክተዋል። ድጋፉን…


