2020
በአከባቢ ልማት ዙሪያ የአስተዳደሩ አመራሮች ዉይይት አካሄዱ ::
የድሬደዋ አስተዳደር ከፍተኛ አመራሮችና የ 9ኙ የከተማ ቀበሌ ስራ አስፈፃሚዎች የተሳተፉበት በአከባቢ ልማት እንቅስቃሴ ላይ ያተኮረና ባለፉት አመታት የተከናወኑ የአከባቢ ልማት ስራዎች ዙሪያ ዉይይት ተካሄደ ፡፡ በዚህ የዉይይት ላይ የመክፈቺያ ንግግር ያደረጉት የኮንስትራክሽንና ቤቶች ልማት ቢሮ ሀላፊ ኢንጂነር ጀማል በልማት ስራዎች ህብረተሰቡን አሳታፊ ማድረግ የልማት ስራዎቹን ህዝቡ በባለቤነት እየተከታተለ እንዲሰሩ ከማድረጉም በላይ ዘላቂ አገልግሎት እንዲሰጡም…
Kulan uu soo diyaariyay xafiiska dhismaha iyo horumarinta magaalada oo lagaga wada xaajoonaayay sidi kor loogu qaadi lahaa mashaaricaha horumarineed ayaa ka qabsoomay holka shirarka e eras huteel.
Kulankani oo ay kazoo qayb galeen masuuliyinta sarsare ee ismaamulka iyo gudoomiyayaasha 9ka qabale ee magaalada ayaa waxaa furitaanki kuankani ka hadlay mudane injineer Jamaal ibraahim oo ah madaxa xafiiska dhismaha iyo horumarinta magaalada ayaa sheegay in mashaaricaha oo laga qayb galiyo bulshada ay abuuri karto cad caadaan iyo waliba in ay mashaaricdasi yeeshaan tayo…
“መምህራን በቀውስ ጊዜ ይመራሉ፤ መጪውንም ይተነብያሉ!” በሚል መሪ ቃል የመምህራን ቀን በአስተዳደራችን በደማቅ ሁኔታ ተከበረ።
የመማር ማስተማር ስራዎች ተጠናክሮ እንዲቀጥሉ የመምህራን የሙያ ብቃትና በተለይም ብቁ ዜጋ ከማፍራት ጎን ለጎን የሀገራችን የብልፅግና ጉዞ መምህራን የላቀ ሚና መጫወት እንዳለባቸው ተገለጸ፡፡ በመድረኩ ላይ የተገኙት የአስተዳደሩ ከንቲባ ክቡር አቶ አህመድ መሀመድ ቡህ አንደገለፁት ዛሬ በዓለም ላይ በሳይንስና ቴክኖሎጂ ከፍተኛ ደረጃ ላይ የደረሱ ሀገሮች ለስኬታቸው ዋናው ምክንያት ለትምህርት ትኩረት በመስጠታቸው ሲሆን በዚህ ረገድ መምህራን ሙያቸውን…
ህብረተሰቡ ሰላሙን በማስጠበቅ እርስ በእርስ የመደጋገፍ ባህሉን እንዲያጠናክር ጥሪ ቀረበ።
የድሬደዋ አስተዳደር በወቅታዊና ሀገራዊ ጉዳዮች ዙሪያ ከሀይማኖት አባቶች ጋር ወይይት አድርገዋል። በውይይት መድረኩ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የአስተዳደሩ ምክትል ከንቲባና የንግድ፣ ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ ኃላፊ አቶ ከድር ጁሀር ድሬዳዋ ያሳለፍናቸው ወራት በህብረተሰቡና በፀጥታ አካላት ትብብር ብዙ ዋጋ በተከፈለበት መስዋዓትነት ወደ ቀድሞ ሰላሟ መመለሷን በመጠቆም ይህንን ሰላም ሊያደፈርሱ የሚፈልጉ ቀን ከሌት የማይተኙ በሰው ህይወት ቁማር የሚጫወቱ አረመኔ…
የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ የኮሮና ቫይረስ ወረርሺኝን በመከላከል የ2013 የመማር ማስተማሩን ሂደት ለማስጀመር ውይይት አካሄደ፡፡
በዩኒቨርሲቲው ውስጥም ተማሪዎችን በዘር፣ በሀይማኖትና በብሔር የሚከፋፍሉ የዩኒቨርሲቲው መምህራንና ሰራኞች ላይ የዩኒቨርሲቲው ቦርድ እንደማይታገስ የዩኒቨርሲቲው የቦርድ ሰብሳቢና የብልጽግና ፓርቲ የፖለቲካ ፓርቲዎችና የሲቪክ ተቋማት ዘርፍ ኃላፊ ዶ/ር አለሙ ስሜ ገልፀዋል፡፡ የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ የ 2013 የትምህርት ዘመንን ለማስጀመር ይረዳ ዘንድ የተለያዩ የቅድመ-ዝግጅት ስራዎችን በማከናዎን ላይ የሚገኝ ሲሆን ዩኒቨርሲቲው እያከናወናቸው ያሉትን የቅድመ ዝግጅት ስራዎችንም ከዚህ ቀደም የዩኒቨርሲቲው የቦርድ…
በድሬደዋ አስተዳደር ስር በሚገኙ የመንግስት አገልግሎት ሰጭ ተቋማት ላይ የሚስተዋሉ የአገልግሎት አሰጣጥ ክፍተቶች በፍጥነት ተፈትሸው ሊታረሙ እንደሚገባ ተገልጋዮች ገለፁ፡፡
የአስተዳደሩ ፐብሊክ ሰርቪስና ሰው ሀብት ቢሮ የመልካም አስተዳደር ዳይሬክቶሬት በተመረጡ አራት የመንግስት አገልግሎት ሰጭ ተቋማት ላይ ከሚዲያ ጋር በመቀናጀት ድንገታዊ ምልከታ አድርጓል፡፡ በአስተዳደሩ ከፍተኛ ተገልጋይን ከሚያስተናግዱና የህዝብ ሮሮ በስፋት ከሚነሳባቸው ተቋማት መካከል በሁለት የቀበሌና በሁለት መንግስታዊ አገልግሎት ሰጭ ተቋማት ላይ የአስተዳደሩ ፐብሊክ ሰርቪስ እና ሰው ሀብት ልማት ቢሮ የመልካም አስተዳደር ዳይሬክቶሬት በአስተዳደሩ ከሚገኙ ሚዲያዎች ጋር…


