ከድሬዳዋ አስተዳደር ባለሀብቶች ለሀገር መከላከያ ሰራዊት 22.4 ሚሊየን ብር መሰብሰቡ ተገለፀ።
ሀገር የማዳን ጥሪ ተቀብለው <<ሀገራችን ሀብታችን፤ሀብታችን ለሀገራችን >>በሚል መሪ ቃል የአስተዳደሩ ባለሀብቶች ላደረጉት ድጋፍ በአስተዳደሩ የእውቅናና የምስጋና መረሀ ግብር በዛሬው እለት ተካሄዶል። የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ አቶ አህመድ መሀመድ ቡህ በመረሀ ግብሩ ላይ እንደተናገሩት ህውሓት አሸባሪ ቡድን በኢትዮጵያ ላይ አገዛዙን ጭኖ በቆየባቸው ባለፉት 27 ዓመታት የኢትዮጵያ ሕዝብ አንድነት እንዳይኖረው በመከፋፈልና እርስ በርስ እንዲጋጭ በማድረግ የቆየው አሸባሪ…


