የ‘ተረኝነት’ ጉዳይን በተመለከት
ሀገራችን ለሁላችንም የሚበቃ ሀብት አላት። የተፈጥሮ፣ የታሪክ፣ የባህል እና ከምንም በላይ የጊዜ ሀብት አለን። ይህን ሰብስቦ ለጥቅም ማዋል ሲቻል፣ ሀገርን እንደ እቁብ አይቶ በዚህኛው ቀን ለእከሌ፣ በሌላ ቀን ለእከሌ በፈረቃ የምትደርስ ያደርጋታል። እንኳን ለሀገር፣ ለመብራትም ፈረቃ ይከብዳል። ሀገር የምትመራው በጋራ ነው። ሕግ አውጪ፣ ሕግ ተርጓም፣ ሕግ አስፈጻሚ እና ርዕሰ ብሔር የሀገረ መንግሥቱ ምሰሶዎች ናቸው። በሲቪል…


