የኦቲዝም ግንዛቤ ማስጨበጫ ወርን አስመልክቶ በድሬደዋ ታላቅ የእግር ጉዞ ፕሮግራም ተደረገ።
በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ16ኛ ጊዜ በሀገር አቀፍ ደረጃ ደግሞ ለ22ኛ ጊዜ የኢትዮጵያ የኦቲዝም የግንዛቤ ማስጨበጫ ወርን አስመልክቶ ከለገሀር አደባባይ እስከ ለገሀሬ የእግር ጉዞ መርሀግብር ተከናውኗል። በዚህም ከማለዳ ጀምሮ በማርሽ ባንድ በታጀበው የእግር ጉዞ መዳረሻም የለገሀሬ አካባቢ ነዋሪዎች ለእግር ጉዞው አስተባባሪዎችና ተሳታፊዎች፣ በኦቲዝም ጥላ ስር ለሚገኙ ልጆች እንዲሁም ለወላጆች ደማቅ አቀባበል አድርገውላቸዋል። በመርሀ-ግብሩ ላይ በኦቲዝም ጥላ…


