Amharic
ስነ-ምግባራዊና ቅንጅታዊ አሰራርን በማሳደግ የማህበረሰቡን እርካታ የሚጨምር አገልግሎት መስጠት እንደሚገባ ተጠቆመ::
የድሬዳዋ አስተዳደር ሥነ-ምግባር እና ፀረ ሙስና ኮሚሽን በአስተዳደር ለሚገኙ ለሴክተር እና ትምህርት ተቋማት የሰው ሀብት ባለሞያዎች እና ድጋፍ ሰጪ ሰራተኞች “ሙያዊ ስነ- ምግባር ለስነ-ምግባራዊ አገልግሎት አሠጣጥ እና ቅንጅታዊ አሰራር” በሚል ርዕሰ ስልጠና ሰቷል። በዚህም በስልጠና መድረኩ የድሬዳዋ አስተዳደር ሥነ-ምግባር እና ፀረ ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር ፌኑስ አብዱልጀባር ስልጠናው የስነ-ምግባር ብልሽቶችን ለመከላከል አቅም የሚፈጥር መሆኑን የተናገሩ ሲሆን፤…
ለሀገር በርካታ ውለታ የዋሉ አረጋውያን ወገኖች ተጠቃሚ እንዲሆኑ ለማስቻል ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ እንደሚገኝ ተገለፀ::
በድሬዳዋ አስተዳደር “ለአረጋውያን ደኅንነት እና መብቶች መጠበቅ ሁለንተናዊ ኃላፊነታችን እንወጣ” በሚል መሪ ቃል በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ35ኛ ጊዜ በኢትዮጵያ ለ34ኛ ጊዜ ዓለም አቀፍ የአረጋውያን ቀን የማጠቃለያ መርሃ-ግብር ተካሂዷል። በዚህም በመርሃ-ግብሩ የድሬዳዋ አስተዳደር ሴቶች ህፃናትና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ የሴቶች ዘርፍ ኃላፊ ወ/ሮ ፍሪ ጥበቡ ለበዓሉ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክታቸውን በማስተላለፍ፤ አረጋውያን የሀገር ባለውለታ ለትውልድ አርዕያ የሚሆኑ በርካታ…
በመሰረታዊ የሰብዓዊ መብት ጽንሰ ሃሳብ ዙሪያ የአቅም ግንባታ ስልጠና ተሰጠ::
የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባኤ በመሰረታዊ የሰብዓዊ መብት ጽንሰ ሃሳብ ዙሪያ ለባለድርሻ አካላት የአቅም ግንባታ ስልጠና ሰጥቷል። ስልጠናው በዋናነት ዜጎች በተፈጥሮ የተሰጣቸውን ጸጋ ሰብአዊ መብቶቻቸውን እንዲያውቁ እና ሰብዓዊ ክብር ማክበርና መጠበቅ ለሰው ልጆች ሁለንተናዊ እድገትና ብልጽግና መሰረት ዜጎች እምቅ ኃይላቸውን ለመጠቀም የሚያስችላቸው ንቁ፣ ደስተኛና ውጤታማ ሕብረተሰብ ለመፍጠር ዓላማ ያደረገ ስልጠና መሆኑን የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባኤ የክትትል…
በክቡር ከንቲባ ክቡር አቶ ከድር ጁሀር አንዲሁም በምክትል ከንቲባ ክቡር አቶ ሀርቢ ቡህ የተመራው የአስተዳደሩ ከፍተኛና መካከለኛ አመራር በትላንትናው ውሎ የኢትዮጵያ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት መጎብኝቱን አስቃኝተናችሗል።
በሁለተኛው ቀን ውሎ በክቡር ከንቲባ ክቡር አቶ ከድር ጁሀር የተመራው ልዑክ ወደ ጅማ ሲያቀና በምክትል ከንቲባ ክቡር ሀርቢ ቡህ የተመራው ከአስተዳደሩ ከአራቱም የገጠር ክላስተር የተውጣጣ ልዑክ ወደ ማእከላዊ ኢትዮጵያዊ ስልጤ ዞን ሁልባራግ ወረዳ የገጠር ኮሪደር ልማትን እንዲሁም የሌማት ቱሩፋትን የተመለከቱ ስራዎችን በመጎብኝት ላይ ይገኛል።
“የመጣውን ሁሉ ስንከተል ኋላ ቀርተናል፤ ይህ በመደመር መንግሥት ይቀየራል” – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
ቴክኖሎጂ የተለዋዋጩ ምኅዳር ዘዋሪ በሆነበት በዚህ ወቅት ኢትዮጵያ ብሎም አፍሪካ በቂ የሚባል የተጠቃሚነት ድርሻን አላገኙም። ለዘመናት የተላመዱት የተቀባይነት ሚና በራስ ያለመቆምን የሚያለማምድ እና ሉዓላዊነትን የሚጎዳ ነው። በቴክኖሎጂ ውድድር ይህን ዕሳቤ ማራመድ እና ከሌሎች የተገዛ ሲስተም ተቀባይ ብቻ መሆን አዋጭ አለመሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገልጸዋል። ዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ስትራቴጂ በዚህ ዕሳቤ እንደተጀመረ የገለጹት ጠቅላይ…
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ 7ኛው ጠቅላላ ምርጫን አስመልክቶ ከፖለቲካ ፓርቲ ተወካዮች ጋር ተወያየ
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የ7ኛውን ጠቅላላ ምርጫ ረቂቅ የጊዜ ሠሌዳን ጥቅምት 10 ቀን 2018 ዓ.ም. ባስተዋወቀበት ወቅት ከፖለቲካ ፓርቲዎች ከተነሡት ጥያቄዎች ውስጥ “የዕጩዎች የድጋፍ ፊርማ ማቅረብ ይቅር/ይታገድ” የሚለውና “ከገዢው ፓርቲ ጋር መወያየት እንፈልጋለን” የሚሉት በዋነኛነት ይጠቀሳሉ። ቦርዱ ከፓርቲዎች የተነሡት ጥያቄዎች መልስ ሊያገኙ በሚችሉበት አግባብ ሲሠራ የቆየ ሲሆን፤ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ኅዳር 25 ቀን 2018…
የቁሉቢ ገብርኤል የንግስ በዓልን ለማክበር ከተለያዩ የሀገራችን ክፍሎች የሚመጡ ምዕመናን እና የበዓሉ ተሳታፊዎችን በፍቅርና በአክብሮት ለማስተናገድ ዝግጅት መጠናቀቁን የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ገለፁ።
በየዓመቱ የሚከበረውን የቁልቢ ገብርኤል ንግስ በዓል ምክንያት በማድረግ የድሬዳዋ ነዋሪዎች እና የአስተዳደሩ አመራሮች የበዓሉ ተሳታፊ እንግዶችን የሚቀበሉበት መርሀግብር በአመት ሁለት ጊዜ የሚሰናዱ ሲሆን ለበዓሉ ተሳታፊዎች በተለያዩ ፖሊስ ጣቢያዎች የማረፊያ ድንኳን በመጣልና ማረፊያ በማዘጋጀት፥ የእንግዶችን ሰላም፣ደህንነት ከነዋሪው ጋር ተቀናጅተው ይጠብቃሉ። በፍቅር በሰላም ተምሳሌት ትንሿ ኢትዮጵያ ተብላ በምትታወቀው ድሬዳዋ ከተማ በተለያዩ የትራንስፖርት አማራጮች ተጠቅመው ወደ ከተማዋ…
የሰው ሰራሽ አስተውሎትን በየዘርፉ መጠቀም እንደ አገር ያለውን እድገት ለማፋጠን እንደሚረዳ ተገለፀ።
በድሬደዋ አስተዳደር ክቡር ከንቲባ አቶ ከድር ጁሀር የተማራ ልዑክ በኢትዮጵያ አርቴፊሻል ኢንተለጄንስ ኢኒስቲትዩት ጉብኝት አድረጓል። በጉብኝቱ ክቡር ከንቲባ ከድር ጁሀር በድሬደዋ አስተዳደር ዘመናዊ አስተዳደርን በመዘርጋት ስማርት ሲቲን ለመፍጠር የሚያስችሉ ስራዎች እየተከናወነ መሆኑን ገልፀው ለአብነትም የመሶብ አንድ ማእከል አገልግሎት እንዲሁም በፍትህ ዘርፉ የተከናወኑ ተግባራትን ጠቅሰዋል። በቀጣይም በሌሎች ዘርፎች ቴክኖሎጂን በተለይም ሰው ሰራሽ አስተውሎትን ለማስፋፋት እንደሚሰራ በዚህ…


