የድሬደዋ አስተዳደር ምክር ቤይ 3ተኛ የስራ ዘመን 5ተኛ አመት 3ተኛ አስቸኳይ ጉባኤ አካሄዷል።

ምክር ቤቱ ካፀደጋቸው ሹመቶች አንዱ አቶ ብሩክ ወርቅነህ የድሬደዋ መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳይ ቢሮ ሃላፊ አድርጎ የሾመ ሲሆን በዛሬው ዕለት ከቀድሞ የቢሮ ኃላፊ አቶ ብሩክ ፈለቀ ጋር የስራ ርክክብ አድርገዋል። እንዲሁም ከቢሮው የሥራ ኃላፊዎችና ባለሙያዎች ጋር ተዋውቀዋል።

Read More

የማህበረሰብ እሴቶችን በመጠቀም ሙስናና ብልሹ አሰራሮችን መከላከል የሁሉም ማህበረሰብ ኃላፊነት መሆኑ ተገለፀ

የድሬዳዋ አስተዳደር ስነ-ምግባር እና ፀረ ሙስና ኮምሽን በአስተዳደሩ ለሚገኙ የሴቶች እና ወጣቶች አደረጃጀት “ሙስናና ብልሹ አሰራር ለመከላከል እና የማህበረሰቡ ስነ-ምግባር ለመገንባት የአደረጃጀት ሚና”በሚል ርዕስ ስልጠና ሰጠ። በዚህም በስልጠና በመድረኩ በመገኘት የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የድሬዳዋ አስተዳደር ስነ-ምግባር እና ጸረ ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር ፌኑስ አብዱልጀባር ወጣቶች እና ሴቶች ለሀገር ልማት እና ብልፅግና ጉልህ ድርሻ እንዳላቸው ተናግረው፤ሙስናና ብልሹ…

Read More

የድሬዳዋ አስተዳደር ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ኤጀንሲ ከኢትዮጵያ አርተፊሻል ኢንተለጀንስ ኢኒስቲትዮት ጋር በመተባበር በድሬዳዋ አስተዳደር ለሚገኙ የአይሲቲ ባለሞያዎች ስልጠና እየተሰጠ ነው

አቶ ይታገሱ ደሳለኝ የኢትዮጵያ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ምክትል ዋና ዳይሬክተር የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ስራን በማላቅ ረገድ ያለውን ፋይዳ ከግምት በማስገባት በንቃት ስልጠናውን ተከታትለው ለውጤት እንዲያበቁት አሳስበዋል። ኢንጂነር መሐዲ መሐመድ በበኩላቸው የኤ አይን የላቀ እና የተቀላጠፈ እምቅ አቅም ከተቋማት አገልግሎት አሰጣጥ ጋር በማቀናጀት ምርታማነትን እና የአገልግሎት እርካታን ለተገልጋይና ተደራሽ የማድረግ እድል ስለሚፈጥር ከዚሁ አንጻር በትኩረት ስልጠናውን መከታተል…

Read More

በድሬዳዋ አስተዳደር እስከ መጋቢት 10/2018 ዓ.ም ድረስ የሚፈፀመውን የ100 ቀን ዕቅድ በውጤት ለመጨረስ ርብርብ ማድረግ እንደሚገባ የድሬዳዋ አስተዳደር ክቡር ከንቲባ አቶ ከድር ጁሀር አመላከቱ

”በመደመር መንግስት ዕይታ የዘርፎች እመርታ” በሚል መሪ ሀሳብ ሲሰጥ በነበረው የስልጠና ማጠቃለያ ላይ ክቡር የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚንስትር ዶ/ር አብይ አህመድ በሠጡት የስራ አቅጣጫዎች መሠረት በተመረጡ ዘርፎች ላይ ተግባራዊ የሚደረግ የ100 ቀን እቅድ በድሬዳዋ አስተዳደር የተዘጋጀ ሲሆን፤ በዛሬው ዕለት እቅዱን ወደ ስራ ለማስገባት ከአስተዳደሩ አመራሮች ጋር ውይይት ተካሂዷል። በዚህም በመድረኩ የድሬዳዋ አስተዳደር ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት…

Read More

በሳንባ ምች ምክንያት የሚሞቱ ህፃናትን ለመቀነስ በርብርብ እንደሚሰራ ተገለፀ::

በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ 21ኛ ጊዜ በሀገራችን ደግሞ ለ6ኛ ጊዜ “በተቀናጀ ዘዴ ለህፃናት ህይወት” በሚል የሳንባ ምች ቀን ከጤና ጥበቃ እንዲሁም ከተለያዩ ክልሎች የተወጣጡ እንግዶች በተገኙበት በድሬዳዋ አስተዳደር ተከብሯል። በዚህም በመርሃ-ግብሩ የተገኙት የአስተዳደሩ ጤና ቢሮ ተወካይ አቶ አቤል ሽፈራው የሳንባ ምች በዓለም ዙሪያ በተለይም ህፃናትን እና እድሜያቸው የገፉ የህብረተሰብ ክፍሎችን ጨምሮ በርካታ ሰዎችን የሚያጠቃ በሽታ…

Read More

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከህንድ አቻቸዉ ናሬንድራ ሞዲ እና ከልዑካን ቡድናቸዉ ጋር ተወያዩ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በማህበራዊ ትስስር ገጻቸዉ ባሰፈሩት መልእክት ለህንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ በብሔራዊ ቤተመንግሥት ይፋዊ አቀባበል ሥነሥርዓት አድርገናል ብለዋል፡፡ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር ውይይት ካደረግን በኋላ ከልዑካን ቡድኖቻችን ጋር የሁለትዮሽ ውይይት አካሂደናል። በውይይታችን በኢትዮጵያ እና ህንድ መካከል እያደገ የመጣውን ትብብር እና የወል ቅድሚያዎች የሚያንፀባርቁ አዳዲስ የትብብር መስኮችን ቃኘተናል ሲሉ ገልጸዋል፡፡ በሁለቱ ሀገራት መካከል…

Read More

አርሶ አደሩን ከተረጂነት ለማላቀቅ የሚከናወኑ ስራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ተገለጸ::

14 ሚሊየን የሚገመት የስራ ቦታ ደህንነት መጠበቂያና የውሃ መሳቢያ ፓንፕ በልማታዊ ሴፍቲኔት መረሃ ግብር ድጋፍ ተደርጓል፡፡ በመረሀ -ግብሩ የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ከድር ጁሃር በአስተዳደሩ ለገጠር ልማት ትኩረት በመስጠት በገጠር ምርታማ ሴፍቲኔት ፕሮግራም የልመናና የተረጂነት አስተሳሰብ በመቀየር በቤተሰብ ደረጃ በምግብ እራስን ለመቻል የሚያስችሉ ስዎችን ጨምሮ እንደ አገር የተቀመጡ የልማት ኢኒሺቲቮች ግብ እንዲመቱ እየተሰራ እንደሚገኝ ገልፀዋል፡፡…

Read More

“የሀገርን ሰላም ለማስጠበቅ ኃላፊነት መውሰድና ሀገርን ማገልገል ትልቅ ክብር ነው”:-የድሬዳዋ አስተዳደር ክቡር ምክትል ከንቲባ አቶ ሀርቢ ቡህ

በድሬዳዋ አስተዳደር የ2018 ዓ.ም አንደኛ ዙር የሀገር መከላከያ ሰራዊትን ለመቀላቀል የተመለመሉ ወጣቶች ሽኝት ተደረገላቸው። በዚህም በሽኝት መርሐ-ግብሩ ላይ የተገኙት የድሬዳዋ አስተዳደር ክቡር ምክትል ከንቲባ አቶ ሀርቢ ቡህ የሀገርን ሰላም ለማስጠበቅ ኃላፊነት መውሰድና ሀገርን ማገልገል ትልቅ ክብር መሆኑን ተናግረዋል። ምክትል ከንቲባ ሀርቢ አያይዘውም የሀገር መከላከያ ሰራዊት ከለውጡ ማግስት ጀምሮ ብቃትና ዲሲፒሊን ባላቸው የሰው ሀይል መደራጀቱን ጠቁመው…

Read More

የ100 ቀናት ዕቅድ የዝግጅት ምዕራፍ ስራዎች ተገመገመ

”በመደመር መንግስት ዕይታ የዘርፎች እመርታ” በሚል መሪ ሀሳብ ሲሰጥ በነበረው የስልጠና ማጠቃለያ ላይ ክቡር የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚንስትር ዶ/ር አብይ አህመድ በሠጡ የስራ አቅጣጫዎች መሠረት በተመረጡ ዘርፎች ተግባራዊ ለማድረግ የተዘጋጀ የ100 ቀን እቅድ አተገባበር ተገምግሟል። በክቡር ጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ (ዶ/ር) የተቀመጡ አቅጣጫዎችን በአስተዳደሩ ተጨባጭ ሁኔታ ተግባራዊ ለማድረግ በተቀመጠው አቅጣጫ መሠረት የብልፅግና ፓርቲ ድሬዳዋ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት…

Read More

ዓለም አቀፍ የፀረ ጾታዊ ጥቃት (ነጭ ሪቫን ) ቀን በአስተዳደሩ በተለያዮ ሁነቶች ተከበረ::

የድሬዳዋ አስተዳደር ሴቶች ህጻናት ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ በአለም አቀፍ ደረጃ ለ34ኛ በሀገራችን ለ20ኛ ጊዜ “ጥቃትን የማይታገስ ማህበረሰብ ለትውልድ ግንባታ “በሚል መሪ ሀሳብ የሚከበረው የፀረ ጾታዊ ጥቃት (ነጭ ሪቫን ) ቀንን በተለያዩ ሁነቶች አክብሯል። በአስተዳደሩ”ጥቃትን የማይታገስ ማህበረሰብ ለትውልድ ግንባታ” በሚል መሪ ሀሳብ 16ቱ የጸረ ጾታዊ ጥቃት ቀን ንቅናቄ በተለያዩ ሴቶችን ከጾታዊ ጥቃት ለመታደግ በሚረድ ተግባራት ሲከናወን…

Read More