የኮሪደር ልማት ስራ የሚከናወንባቸው ስፍራ ላይ ያሉ የንግድ እና መኖሪያ ቤቶች ደረጃቸውን የጠበቁ እንዲሆኑ እየተደረገ እንደሚገኝ ተገለፀ

በድሬዳዋ አስተዳደር የኮሪደር ልማትና የህንፃ ስታንዳርዶች እንዲሁም የቀጣይ የኮሪደር ልማት ምዕራፎችን ለማስተግበር ከሚመለከታቸው ነዋሪዎች፣ የህንፃ ባለቤቶችና ተቋማት ጋር የምክክር መድረክ ተካሂዷል። በዚህም በመድረኩ የተገኙት የድሬዳዋ አስተዳደር የግንባታ ፍቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን ዳይሬክተር አቶ ኤፍሬም ግርማይ በኮሪደር ልማት ስራ የተከናወኑና በቀጣይም የሚከናወኑ ስራዎችን ዘመናዊና ደረጃቸውን የጠበቁ እንዲሆኑ የሚያስችል ተግባር እየተከናወነ እንደሚገኝ ገልፀዋል። በተለይም በኮሪደሩ የሚለሙ አካባቢዎች ላይ…

Read More

400 ለሚሆኑ ተማሪዎች የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ ተደረገ

ሼክ በክሪ ሳፖሎ ፋውንዴሽን እና ራሀ ሪሊፍ ኤንድ ሁማኒቴሪያል አሶሴሽን ከዚህ ቀደም በድሬዳዋ አስተዳደር በተለያዩ የበጎ አድራጎት ስራዎች ላይ በመሳተፍ በርካታ ድጋፎችን ያደረገ ሲሆን በዛሬው እለትም በድሬዳዋ በአራቱም የገጠር ክላስተር አነስተኛ ገቢ ላላቸው 400 ለሚሆኑ ተማሪዎች የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ አድርገዋል ። በመርሀ-ግብሩም የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ክቡር አቶ ከድር ጁሀር ጨምሮ በብልፅግና ፓርቲ የድሬዳዋ አስተዳደር ቅርንጫፍ…

Read More

ሕዝባዊ እና ሃይማኖታዊ በዓላት የኢትዮጵያ ብዝኃነት ማሳያ ናቸው – የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት

የመስቀል ደመራ በዓል ኢትዮጵያ በዓለማቀፍ ደረጃ በማይዳሰስ ቅርስነት ካስመዘገበቻቸው መካከል አንዱ ነው። በዓሉ በመላው ኢትዮጵያ ከትውልድ ወደ ትውልድ እየተወራረሰ ተጠብቆ የቀጠለ ክዋኔን የሚያሳይ የኢትዮጵያ ብዝኃነት እና ኅብረ ብሔራዊ አንድነት ማሳያ ነው። በተባበሩት መንግሥታት የትምህርት፣ ሳይንስ እና ባህል ድርጅት (ዩኔስኮ) በዓለም ቅርስነት የተመዘገበውም ይህን ነባር የአከባበር ትውፊቱን ይዞ እንዲቀጥል፤ ከኢትዮጵያ አልፎ የሰው ልጆች ኹሉ የጋራ ቅርስነቱ…

Read More

ከሩስያ ጋር የጋራ የኒኩሊየር ኃይል ማመንጫ ለማልማት ስምምነት ተፈራርመናል – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

ከፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ጋር በተለያዩ ዘርፎች ላይ አጠቃላይ ውይይት ማካሄዳቸውን የጠቀሱት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ፤ እነዚህም የኃይል ማመንጫ፣ ግብርና፣ የጤና ዘርፍ ልማት እና የመከላከያ ትብብርን እንደሚያካትቱ ገልጸዋል። በተለይም ለማኅበረሰብ አገልግሎት የሚውል ንፁህ ኃይል ለማቅረብ የጋራ የኒኩሊየር ኃይል ማመንጫ ለማልማት ስምምነቶችን በመፈራረም የጋራ ፍላጎቶቻችንን የሚያጎለብቱ ጉዳዮች ላይ ተማክረናል ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትስስር ገፃቸው ባሰፈሩት ፅሑፍ።

Read More

በድሬዳዋ አስተዳደር የደመራ በዓልን ምክንያት በማድረግ በዓሉ የሚከበርበትን ስፍራ የማፅዳት መርሀ-ግብር ተከናወነ

በመርሃ-ግብሩም የድሬዳዋ አስተዳደር ክቡር ከንቲባ አቶ ከድር ጁሀር ከኃይማኖት አባቶች እና ከወጣቶች ጋር በጋራ በመሆን የደመራ በዓል የሚከበርበትን ስፍራ አፅድተዋል። ድሬዳዋ ሁሉም እምነቶች በፍቅር፣ በአብሮነትና በሰላም የሚኖሩባት ከተማ መሆኗ የተገለፀ ሲሆን፤ እንደነዚህ አይነት በዓላትም ወንድማማችነትን እና እህትማማችነትን እንደሚያጠናክሩ ተጠቁሟል። በፅዳት ዘመቻው ሲሳተፉ ያነጋገርናቸው የእስልምና፣ የፕሮቴስታንት እና የሌሎችም እምነት ተከታይ እህት ወንድሞች በድሬዳዋ ሁሉም በዓል በጋራ…

Read More

ወጣቶች እና ታዳጊዎች ክረምቱን በስፖርታዊ እንቅስቃሴዎች ማሳለፋቸው አካላዊ ጥንካሬያቸውን እንዲያጎለብቱ ከማድረጉ በተጨማሪ ተተኪ ስፖርተኞችን ለማግኘት ከፍተኛ ሚና እንዳለው ተጠቆመ

በድሬዳዋ አስተዳደር የወረዳ 2 ወጣቶችና ስፖርት ማስተባበሪያ አስተባባሪነት የ2017/18 ዓ.ም የታዳጊዎች የክረምት እግር ኳስ ውድድር ማጠቃለያ መርሃ-ግብር ማምሻውን በድምቀት ተካሂዷል። በዚህም መርሀ-ግብሩ የተገኙት የድሬዳዋ አስተዳደር የብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት የአደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ አቶ ደረጀ ፀጋዬ ወጣቶች ክረምቱን ማህበረሰቡን የሚጠቅሙ ሰው ተኮር ስራዎች ላይ ተሰማርተው ከማገልገላቸው ጎን ለጎን ስፖርታዊ እንቅስቃሴን ማድረጋቸው የእርስ በእርስ ወንድማማችነትን እና እህትማማችነትን…

Read More

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከቤላሩስ ፕሬዝዳንት ጋር ተወያዩ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከቤላሩስ ፕሬዝዳንት አሌክሳንደር ሉካሼንኮ ጋር በሁለትዮሽና አለም አቀፍ ጉዳዮች ላይ ውይይት አድርገዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው፤ ከአለም አቀፍ የአቶሚክ ፎረም ጎን ለጎን ከቤላሩስ ፕሬዝዳንት አሌክሳንደር ሉካሼንኮ ጋር በሁለትዮሽና አለም አቀፍ ጉዳዮች ላይ ውይይት አድርገናል ብለዋል። የግብርና ሜካናይዜሽንን ጨምሮ በተለያዩ የኢንቨስትመንት ጉዳዮች ላይ በጋራ በሚሰራበት ሁኔታ ላይ መምከራቸውንም ጠቅላይ ሚኒስትሩ…

Read More

“ድሬ-መሶብ”የተገልጋዮች እንግልትን በመቅረፍ ቀልጣፋ እና ዲጂታል የሆኑ አገልግሎቶችን የሚሰጥ መሆኑን የድሬዳዋ አስተዳደር ክቡር ከንቲባ አቶ ከድር ጁሀር ገለፁ

በድሬዳዋ አስተዳደር “ድሬ መሶብ” የአንድ ማዕከል አገልግሎት መስጫ ማዕከል በዛሬው ዕለት በድምቀት ተመርቋል። በዚህም በምርቃት በመርሃ-ግብሩ የድሬዳዋ አስተዳደር ክቡር ከንቲባ አቶ ከድር ጁሀር ማዕከሉ ፈጣንና ቀልጣፋ አገልግሎት ለማህበረሰቡ ከመስጠቱ በተጨማሪ የዲጂታል ድሬን ጉዞ የሚያፋጥን መሆኑን አብራርተዋል። ከንቲባ ከድር አያይዘውም “ድሬ መሶብ” የአንድ ማዕከል አገልግሎት በቴክኖሎጂ የታገዘ ቀልጣፋ አገልግሎት በአንድ ቦታ ላይ መስጠት የሚያስችል መሆኑን በመግለፅ፤ይህም…

Read More

‎በአስተዳደሩ ለጎርፍ ተጋላጭ የሆኑ የማህበረሰብ ክፍሎች ዘንድ የቅድመ መከላከል ስራዎችን አስቀድሞ በመሰራቱ ላለፉት አምስት አመታት የከፋ ችግር በዜጎች ላይ አለመድረሱን በድሬደዋ አስተዳደር አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አስታወቀ።

‎በድሬደዋ አስተዳደር አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮምሽን የአደጋ ስጋት ቅነሳ ስራዎችን በተቋማት የልማት እቅድ ውስጥ ማካተትን በተመለከተ ለሴክተር ተቋማትና ለግል ድርጅቶች ባለሞያዎች እና አመራሮች ስልጠና ተሰጥቷል። ‎ ‎በአደጋ ስጋት ቅነሳ አጠቃላይ በመንግስት ተቋማት የተቀናጀ ስራ በመስራቱ በራስ አቅም በአስተዳደር ደረጃ የአደጋ ቅነሳ ስራዎች በስፋት መከወናቸውን በድሬደዋ አስተዳደር አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮምሽን ኮምሽነር አቶ ሱሌማን…

Read More

የ2018 በጀት ዓመት የካፒታል ፕሮጀክት ማስፈጸሚያ የቃል-ኪዳን ሰነድ ፊርማ ሥነ-ሥርዓት ተካሄደ

የካፒታል ፕሮጀክት የቃል -ኪዳን ሰነዱን የድሬደዋ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ከድር ጁሀር በተገኙበት 19 ተቋማት ተፈራርመዋል። “በ2018 በጀት አመት በአስተዳደሩ ከተያዙ የካፒታል ፕሮጀክቶች የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የሚያግዙ የንፁህ የመጠጥ ውሀና የመስኖ ውሀ ፕሮጀክቶች እንዲሁም የጋራ የመኖሪያ ቤቶች ግንባታ ትኩረት እንደሚደረግ ከንቲባ ከድር ጁሀር በፊርማ ስነ-ስርዓቱ ላይ ገልፀዋል። በፊርማ ስነ ስርዓቱ ላይ ከአዲስ እና ነባር ፕሮጀክቶች መካከል…

Read More