የድሬ መሶብ አንድ ማዕከል አገልግሎት ስማርት ድሬዳዋን እውን ለማድረግ እየተደረገ ያለውን ጥረት በእጅጉ የሚያጠናክር መሆኑ ተገለፀ

በድሬዳዋ አስተዳደር የተገነባው የድሬ መሶብ አንድ ማዕከል አገልግሎት በዛሬው እለት በይፋ ተመርቋል ። የድሬ መሶብ አንድ ማዕከል አገልግሎት ግንባታ በአስተዳደር ደረጃ ተግባራዊ እየተደረገ ያለውን የመንግስት አገልግሎት እና አስተዳደር ሪፎርም ውጤታማ ለማድረግ የማይተካ ሚና የሚኖረው ከመሆኑም በላይ የተቋማት አገልግሎቶች በቴክኖሎጂ የተደገፉ ፣ ቀልጣፋና ጥራት ያላቸው እንዲሆኑ ማድረግ የሚቻልበትን አቅም በመፍጥር ስማርት ድሬዳዋን እውን ለማድረግ እየተደረገ ያለውን…

Read More

በድሬዳዋ አስተዳደር የተገነባው የድሬ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት የማስመረቅና የማስጀመር መርሀ-ግብር በአሁን ሰአት እየተካሄደ ይገኛል ።

የድሬዳዋ አስተዳደር የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮም የድሬ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት የማስመረቅና የማስጀመር መርሀ-ግብር ላይ ያሉትን አጠቃላይ መረጃዎች ወደ እናንተ የምናደርስም ይሆናል ።

Read More

በቅርቡ የኢፌዴሪ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር በመሆን የተሾሙት ክብርት እናትዓለም መለስ በድሬዳዋ አስተዳደር የተገነባውን መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት መስጫ ማዕከልን ለመመረቅ ድሬዳዋ አስተዳደር ገቡ

ክብርት ሚኒስትሯ ድሬዳዋ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ ሲደርሱ በድሬዳዋ አስተዳደር ክቡር ምክትል ከንቲባ አቶ ሀርቢ ቡህ፣ በካቢኔ አባላት እንዲሁም በአስተዳደሩ በየደረጃው በሚገኙ አመራሮች ደማቅ አቀባበል ተደርጎላቸዋል። ክብርት ሚኒስትሯ የድሬዳዋ አስተዳደር የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ የኮሚኒኬሽኑን ስራ በማዘመኑ ረገድ የሰራቸውን ስራዎችም ይጎበኛሉ ተብሎ ይጠበቃል። ” መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ” በአንድ ጣራ ስር የተለያዩ የመንግስት አገልግሎቶችን…

Read More

በድሬዳዋ አስተዳደር የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ መጠናቀቅን አስመልክቶ ታላቅ የድጋፍ ሰልፍ እየተካሄደ ነው

የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ ተጠናቆ መመረቁን አስመልክቶ ዛሬ በድሬዳዋ አስተዳደር ታላቅ ሕዝባዊ የድጋፍ ሰልፍ እየተካሄደ ነው። በአሁን ሰዓት በአስተዳደሩ የሚኖሩ ነዋሪዋች ወደ እስታዲየም የተለያዩ መፈክሮችን ይዘው በመግባት ላይ ይገኛሉ ። የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ የድጋፍ ሰልፉን የተመለከቱ ዘገባዎችን ተከታትሎ ባሉት የዲጂታል ሚዲያ አማራጮቹ የሚያቀርብ ይሆናል።

Read More

ልጆችን ማዕከል ያደረገ ድጋፍ ትውልድን መገንባት እንደሆነ ተገለፀ።

የኤስኦኤስ የህፃናት መንደር በድሬዳዋ ለ635 ህጻናት የትምህርት መረጃ ቍሳቁስ ደጋፍ አድርጓል። በድጋፍ ስነስርአቱ ላይ የኤስኦኤስ የህፃናት መንደር የሎኬሽን ኘሮግራም ዳይሬክተር አቶ መሉቀን አስፋው እንዳሉት የተደረገው ድጋፍ የኤስኦኤስ ህጻናት ወንደር በድሬዳዋ አሰተዳደር ከተማ ሶስት ፕሮጀክቶች እንዳሉት ገልፀው ሁለቱ ፕሮጀክቶች ውሎና አዳራቸውን ጐዳና ላይ ያደረጉ ህጻናትን የሚደግፍ መሆኑን ገልዋል፡ ከዚህ ውስጥ የዛሬው ድጋፍ አንዱ ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ…

Read More

በድሬዳዋ አስተዳደር የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ መጠናቀቅን አስመልክቶ ህዝባዊ የውይይት መድረክ ተካሄደ

የግድቡ መጠናቀቅን አስመልክቶ” እምርታ እና ማንሰራራት” በሚል መሪ ሀሳብ ህዝባዊ የፓናል የውይይት መድረክ በዛሬው እለት ተካሂዷል። በፓናል የውይይት መድረኩም የድሬዳዋ አስተዳደር ክቡር ከንቲባ አቶ ከድር ጁሀር በንግግራቸው የህዳሴ ግድባችን ኢትዮጵያውያን በደምና በላብ ዋጋ የከፈልንበት የህብረ ብሄራዊ አንድነታችን ውል የመቻል ምሳሌ ነዉ ብለዋል። የህዳሴ ግድባችን በወጀብ ውስጥ ሳንናወጥ፥ በቁርጥ ቀን በጽናት እንድንቆም ያደረገን የአንድነታችን ውል፥ የጥቁር…

Read More

በድሬዳዋ አስተዳደር የታላቁ ኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ መጠናቀቅን አስመልክቶ ህዝባዊ የፓናል የውይይት መድረክ እየተካሄደ ነው

በድሬዳዋ አስተዳደር የግድቡን መጠናቀቅ አስመልክቶ ”እምርታና ማንሰራራት” በሚል መሪ ሀሳብ ህዝባዊ የውይይት መድረክ እየተካሄደ ይገኛል። በህዝባዊ የውይይት መድረኩም የድሬደዋ አስተዳደር ከንቲባ ክቡር አቶ ከድር ጁሀር የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ክብርት ወ/ሮ ፈቲያ አደን ፣ምክትል ከንቲባ ክቡር አቶ ሀርቢ ብህ የፓርቲ እና የአስተዳደሩ ከፍተኛ አመራሮች፣ የሀይማኖት አባቶች የመንግስት ሰራተኞች እና በርካታ የአስተዳደሩ ነዋሪዎች እየተሳተፉ…

Read More

ኦል-ብራይት ኢንተርናሽናል ኮሌጅ ድሬዳዋ ካምፓስ አንድ መቶ ሃያ ተማሪዎችን ለመጀመሪያ ጊዜ አስመረቀ

ኦል-ብራይት ኢንተርናሽናል ኮሌጅ ድሬዳዋ ካምፓስ በቴክኒክና ሞያ ትምህርት ስልጠና በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያስተማራቸውን አንድ መቶ ሃያ ተማሪዎችን ለመጀመሪያ ጊዜ በዛሬው እለት አስመርቋል ።ከተመራቂ ተማሪዎቹ ውስጥ 80 ያህሉ ሴቶች ናቸው ተብሏል። በምርቃት ስነ-ስርዓቱ ላይ የአስተዳደሩ ከንቲባ ተወካይና እንዲሁም የከንቲባ ፅ/ቤትና የካቢኔ ጉዳዮች ሀላፊ አቶ ገበየሁ ጥላሁን ባደረጉት ንግግር ኮሌጁ በማስተማር ፣ በጥናትና ምርምር እንዲሁም ማኅበራዊ ኃላፊነትን…

Read More

የድሬዳዋ አስተዳደር ክቡር ከንቲባ አቶ ከድር ጁሀር የድሬዳዋን የስማርት ሲቲ ጉዞ የሚያፋጥን የመግባቢያ የስምምነት ፊርማ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሬዝዳንት አቶ አቤ ሳኖ ጋር ተፈራረሙ

በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሬዝዳንት አቶ አቤ ሳኖ የተመራ ልኡካን ቡድን ከድሬዳዋ አስተዳደር ክቡር ከንቲባ አቶ ከድር ጁሀር እንዲሁም በአስተዳደሩ ከሚገኙ ከፍተኛ አመራሮች ጋር የስማርት ድሬን ጉዞ ለማፋጠንና ስራዎችን በጋራ ለመስራት በሚቻልባቸው ነጥቦች ላይ መክረዋል። በዚህም ክቡር ከንቲባ ከድር ጁሀር ለልኡክ ቡድኑ የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል። የስማርት ድሬን ጉዞ ለማፋጠን በርካታ ስራዎች እየተከናወኑ እንደሚገኝ ከንቲባ…

Read More