የሀገራችንን የብልፅግና ጉዞ ለማፋጠን እንዲሁም ጠንካራ ኢኮኖሚን ለመገንባትና የህዝቡን ተጠቃሚነት ይበልጥ ለማረጋገጥ የዲጂታል አሰራሮችን ማጎልበት እንደሚገባ ተጠቆመ::
የድሬዳዋ አስተዳደር ክቡር ከንቲባ አቶ ከድር ጁሀር እና የካቢኔ አባላት በፕላንና ልማት ሚኒስተር ሚኒስትር ፍፁም አሰፋ (ዶ/ር) ከተመራ ልዑካን ቡድን ጋር በፌደራል ደረጃ ተተግብረው ውጤታማ የሆኑ ዲጂታላይዝ አሰራሮችን እና ተሞክሮዎችን ወደ አስተዳደሩ ለማውረድ በሚቻልባቸው ነጥቦች ላይ ውይይት አድርገዋል። በዚህም በውይይት መድረኩ ክቡር ከንቲባ አቶ ከድር ጁሀር በፌደራል ደረጃ የተገኙ ተሞክሮዎችን ወደ ድሬዳዋ አስተዳደር ለማስፋት አስተዳደሩ…


