በድሬዳዋ አስተዳደር እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ስራዎች የከተማዋን የንግድ፣ የኢንደስትሪና የኢንቨስትመንት ማዕከልነት በከፍተኛ ሁኔታ የሚያጠናክሩ መሆናቸው ተጠቆመ

በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሬዝዳንት አቶ አቤ ሳኖ የተመራ ልኡካን ቡድን ከድሬዳዋ አስተዳደር ክቡር ምክትል ከንቲባ አቶ ሀርቢ ቡህ እንዲሁም ከአስተዳደሩ ከፍተኛ አመራሮች ጋር በጋራ በመሆን በድሬዳዋ አስተዳደር እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ስራዎችን ተዘዋውረው ጎብኝተዋል። በጉብኝታቸውም የድሬዳዋ አስተዳደር ልዩ ኢኮኖሚክ ዞንን፣ አማ የምግብ ዘይት ፋብሪካን፣ የተለያዩ የብረታ ብረት ውጤቶችን የሚያመርተውን ድሬ ስቲል ፋብሪካን፣ ደረቅ ወደብን፣ በኢንደስትሪ መንደር…

Read More

“ድሬ ማይክሮ ፋይናንስ ደንበኞቹን ከህልማቸው በማገናኝት ከድህነት ወደ ብልጽግና እያሸጋገረ ያለ ተቋም ነዉ ” ክቡር ከንቲባ አቶ ከድር ጁሀር

ድሬ ማይክሮ ፋይናንስ የማህበረሰቡን የጋራ እድገትን እውቅና የሚሰጥበት ዓመታዊ የደንበኞች ኮንፍረንስ መድረክ በዛሬው እለት አካሂዷል። በመርሃ ግብሩም ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የድሬዳዋ አስተዳደር ክቡር ከንቲባ አቶ ከድር ጁሀር ድሬ ማይክሮ ፋይናንስ በአስተዳደሩ ኢኮኖሚ ላይ እያሳደረ ያለውን በጎ ተጽእኖ ከፍተኛ መሆኑን አንስተው በዚህም ስራ ፈጣሪ ወጣቶች፣ ሴቶች ፣ነጋዴዎች፣ አርሶ አደሮች እና የእጅ ባለሞያዎች በመደበኛ ብድር የማግኝት እድል…

Read More

ግብርን በወቅቱ በመክፈል ለአስተዳደራችን እድገት እና ብልፅግና የበኩላችንን ሀላፊነት መወጣት እንደሚገባ ተገለፀ

በድሬዳዋ አስተዳደር ገቢዎች ባለስልጣን የ 2018 ዓ.ም የታክስ ንቅናቄ ማስጀመሪያ እንዲሁም በተሻሻለ የፌደራል ገቢ አዋጅ ቁጥር 1395 \ 2017 ዙሪያ በዛሬው እለት ከንግዱ ማህበረሰብ ጋር ውይይት ተካሂዷል ። በመርሀ-ግብሩ የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ክቡር አቶ ከድር ጁሀር ግብር ለአንድ ሀገር እድገት እና ብልፅግና አይነተኛ አስተዋፆ እንዳለውና በተለይም ከግብር ከፋዩ ማህበረሰብ በሚሰበሰበው ገቢም በአስተዳደሩ ላይ የተለያዩ የልማት…

Read More

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከድሬዳዋ አስተዳደር ጋር በጋራ በመሆን የድሬዳዋን የስማርት ሲቲ ጉዞ ለማፋጠን እንዲሁም በዲጂታል ቴክኖሎጂ ዘርፍ እየተከናወኑ የሚገኙ ስራዎችን ማጠናከር በሚቻልባቸው ነጥቦች ላይ ለመመካከር የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሬዝዳንት አቶ አቤ ሳኖ የተመራ ልኡካን ቡድን ድሬዳዋ ከተማ ገብቷል።

ልኡክ ቡድኑ ድሬዳዋ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ ሲደርስ በድሬዳዋ አስተዳደር ክቡር ከንቲባ አቶ ከድር ጁሀር፣ በድሬዳዋ አስተዳደር ክቡር ምክትል ከንቲባ አቶ ሀርቢ ቡህ እንዲሁም በመስተዳደሩ ከፍተኛ አመራሮች እና በኢትዮጲያ ንግድ ባንክ ድሬዳዋ ዲስትሪክት አመራሮች እና ቅርንጫፍ ሥራ አስኪያጆች ደማቅ አቀባበል ተደርጎላቸዋል።

Read More

የኢትዮጲያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ መጠናቀቅን አስመልክቶ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ተካሄደ

” እምርታ እና ማንሰራራት ” በሚል መሪ ሀሳብ ታላቁ የኢትዮጲያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ መጠናቀቅን አስመልክቶ በዛሬው እለት የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ተካሂዷል ። የድሬዳዋ አስተዳደር ወጣቶች እና ስፖርት ኮሚሽን ባዘጋጀው የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ላይም የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ክቡር አቶ ከድር ጁሀርን ጨምሮ ከፍተኛ የአስተዳደሩ አመራሮች ፣ የመንግስት ሰራተኞች እንዲሁም የአስተዳደሩ ነዋሪዎች ተሳታፊ ሆነዋል ።

Read More

አዲሱ የገቢ ግብር አዋጅ ለግብር ከፋዩ ህብረተሰብ ፍትሀዊ የግብር አሰባሰብ ሂደትን እንዲፈጠር በማድረግ በኩል ጉልህ ሚና እንዳላው ተገለጸ

የድሬዳዋ አስተዳደር ገቢዎች ባለስልጣን በተሻሻለው የፌደራል ገቢ ግብር አዋጅ 1395/2017 ላይ በአስተዳደሩ ለሚገኙ ለንግዱ ማህበረሰብ የግንዛቤ ማስጨበጫ የውይይት መድረክ በዛሬው እለት አካሂዷል። ውይይቱ በዋናነት የተሻሻለው የገቢ ግብር አዋጅ ቁጥር 1395/2017 ላይ በተለይም የግብር ስርዓቱ ላይ የሚታዩ የፍትሀዊነት ችግሮች ለመቅረፍ የሚያስችሉ የአሰራር ስርዓቶችን በመዘርጋት የወጡ አዋጆችን ለንግዱ ማህበረሰብ ግንዛቤ ለማስጨበጥ አላማ ያደረገ መሆኑ ተገልጿል። በውይይት መድረኩም…

Read More

የመደመር መንግሥት መጽሐፍ ዜጎች ከመሰረታዊ ፍላጎት ባሻገር በክብር የመኖር ህልማቸውን ለመመለስ አቅጣጫ ያስቀመጠ ነው – አቶ ጌታቸው ረዳ

የመደመር መንግሥት መጽሐፍ ዜጎች ከመሰረታዊ ፍላጎት ባሻገር በክብር የመኖር ህልማቸውን ለመመለስ አቅጣጫ ያስቀመጠ ነው ሲሉ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የምስራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር ጌታቸው ረዳ ገለጹ። በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የተጻፈው የመደመር መንግሥት መጽሃፍ ዛሬ ለንባብ በቅቷል። በመጽሐፉ የምረቃ መርሐ-ግብር ላይ ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀስላሴ፣ የመጽሃፉ ደራሲና የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)፣ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች፣…

Read More

የበርካታ ወጣቶችን ህይወት እያሳጣ የሚገኘውን የህገ-ወጥ ፍልሰትና ስደት ለመከላከል ቅንጅታዊ አሰራርን ማጠናከር እንደሚገባ ተገለፀ

የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ እንዲሁም ከዓለም አቀፉ የሰራተኞች ድርጅት (ILO) ጋር በመተባበር “ስደት እና ልማት”(Migration and Development) በሚል መሪ ቃል ከተለያዩ ሀገራት የተወጣጡ ተመራማሪዎች እና የመንግስት አካላት በተገኙበት አለም አቀፍ ኮንፍረንስ እያካሄደ ይገኛል። ኮንፍረንሱ ለሁለት ተከታታይ ቀናት የሚቆይ ይሆናል። በመድረኩ የድሬዳዋ አስተዳደር ክቡር ከንቲባ አቶ ከድር ጁሀር አለም አቀፍ ኮንፍረንሱ ድሬዳዋ በመዘጋጀቱ የተሰማቸውን ደስታ…

Read More

እኛ መደመር ስንል ጠላቶቻችን ይደነግጣሉ፤ ምክንያቱም ስንደመር እንዴት ታሪክ እንደምንሠራ አሳይተናቸዋልና – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

እኛ መደመር ስንል ጠላቶቻችን ይደነግጣሉ፤ ምክንያቱም ስንደመር እንዴት ታሪክ እንደምንሠራ ከጥንት ጀምሮ አሳይተናቸዋልና ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በመደመር መንግሥት መጽሐፍ ምረቃ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት። ኢትዮጵያውያን በዘር ሳንከፋፈል በጋራ ስንቆም መፍጠር፣ መፍጠን፣ አስፈላጊ ሲሆንም መዝለል እንችላለን ብለዋል። መከፋፈል የኢትዮጵያውያን ሀሳብ አይደለም ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ፤ የምንሰማውን ሀሳብ ለመመርመር ካልተዘጋጀን ከተቀባይነት እና ከተከታይነት በመላቀቅ የኢትዮጵያን…

Read More

የታላቁ ህዳሴ ግድብ መጠናቀቅ የኢትዮጵያን መቻል እና አንድነትን ለዓለም የገለጠ ነዉ ሲሉ የአስተዳደሩ የመንግስት ሰራተኞች ገለጹ

የድሬዳዋ አስተዳደር የታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ መመረቅን አስመልክቶ በተከፈተው የፎቶ አውደርዕይ የመንግስት ሰራተኞች የህዳሴ ግድብ መጠናቀቅ የኢትዮጵያን መቻል እና አንድነትን ለዓለም የገለጠ ነዉ ሲሉ ገለጹ። በፎቶ አውደርዕዩ የድሬዳዋ አስተዳደር የግብርና ውሃ ማዕድን እና ኢነርጂ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ መሀመድ አብዲ በወቅቱ እንዳሉት የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ በመሪዎቻችን በሳል ውሳኔ፣ በህዝባችን ኅብረት፣ ፅናትና መስዋዕትነት በመደመር እሳቤ የተገነባ…

Read More