Amharic
በድሬዳዋ አስተዳደር ጳግሜ 2 “የህብር ቀን” በእግር ኳስ ጨዋታ ተከበረ።
በድሬዳዋ አስተዳደር ጳግሜ 2 “የህብር ቀን” በተለያዩ ስፖርታዊ ጨዋታዎችና በእግር ኳስ ጨዋታ ተከብራል። በወጣቶችና ስፖርት ኮሚሽን አስተናጋጅነት ዛሬ ጳጉሜን ሁለትን በማስመልከት ከማለዳ ጀምሮ በርካታ ስፖርታዊ ክንዉኖችን የተካሄዱ ሲሆን ከሰዓት ደግሞ በድሬዳዋ አለም አቀፍ ስታድየም የእግር ኳስ ጨዋታ ተከናውኗል። 70 ደቂቃ በፈጀዉ ጨዋታው ድሬ ጤና ቡድን ከድሬ ሰላም የተገናኙ ሲሆን በድሬ ጤና ቡን 5 ለ 0…
እኛ የአባይ ልጆች ብቻ ሳንሆን የአባይ ንጉሶች ጭምር ነን :- የድሬዳዋ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ ዋና አዛዥ ኮሚሽነር ዓለሙ መግራ ።
የድሬዳዋ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ ዋና አዛዥ ኮሚሽነር ዓለሙ መግራ አዲስ ዘመንን አስመልክተው ለሚዲያ አካላት በዛሬው እለት በሰጡት መግለጫ እንዳስታወቁት ታላቁ ህዳሴ ግድብ ቀደምት አያት አባቶቻችን አባይን የመገደብ ህልም ሲወርድ ሲዋረድ እኛ ጋር ደርሶ እውን ያደረግነው አኩሪ አሻራቸን መሆኑን ገልፀዋል የህዳሴው ግድብ መገባደድ በተለይም በአዲሱ 2018 ዓ.ም ዘመን መለወጫ በዓል ጋር ብስራቱ በመያያዙ በአዲስ የመፈጠር ያህል…
ቢቢሲ የሕዳሴ ግድብን ግዙፍነት እንዴት ገለጸው?
ቢቢሲ ስለ ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ግዙፍነት በገለጸበት ዘገባው፣ “ኢትዮጵያ በአፍሪካ በግዙፍነቱ ቀዳሚ የሆነውን የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ግድቧን በያዝነው የፈረንጆቹ መስከረም ወር ታስመርቃለች” ብሏል። በዓባይ ወንዝ ላይ በ4.6 ቢሊዮን ዶላር ወጪ የተገነባው ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ከ5 ሺህ በላይ ሜጋ ዋት ኃይል እንደሚያመነጭም ጠቁሟል። በንፅፅር ሲያስቀምጠውም፣ የግብጹ አስዋን ግድብ እና የአሜሪካው ሁቨር ግድብ ከሚያመነጩት ኃይል…
አፍሪካን እና ካሪቢያን ሀገራትን ጂኦግራፊ አለያይቶናል ታሪክ ግን አንድ አድርጎናል – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
አፍሪካን እና ካሪቢያን ሀገራትን ጂኦግራፊ ቢያለያያቸውም ታሪክ ግን አንድ አድርጎናል፤ በቀጣይም በተጠናከረ ትብብር መስራት ያስፈልጋል ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ተናገሩ። ሁለተኛው የአፍሪካ ካሪቢያን ማኅበረሰብ የመሪዎች ጉባዔ “ለአፍሪካውያን እና ዘረ አፍሪካውያን የማካካሻ ፍትሕን ለመሻት አኅጉር ተሻጋሪ አጋርነት” በሚል መሪ ሃሳብ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በጉባዔው ባስተላለፉት መልዕክት፤ የአፍሪካ እና…
“በህብር በመቆማችን ፈተናዎችን አልፈን ሀገራዊ ሉዓላዊነትን በማስከበር ለድል በቅተናል… “ክቡር አቶ ሀርቢ ቡህ የድሬዳዋ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ
በድሬዳዋ አስተዳደር ጷግሜ 2 “የህብር ቀን” ብዙሀነት የኢትዮጵያ ጌጥ በሚል መሪ ሀሳብ ህብረብሔራዊ አንድነትን በሚያጠናክሩ ልዩ ልዩ ሁነቶች በድምቀት ተከበረ። በፓናል ውይይቱም የድሬዳዋ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ክቡር አቶ ሀርቢ ቡህ በመክፈቻ ንግግራቸው እንደገለጹት በባለፉት አመታት በህብር በመቆማችን ፈተናዎችን አልፈን ሀገራዊ ሉዓላዊነትን በማስከበር ለድል በቅተናል ብለዋል። ከቅርብ አመታት ወዲህ ኢትዮጵያ ከግጭት ተላቃ ዘላቂ ሰላም ወደ ማጽናት…
የአስተዳደሩ ነዋሪ የሚያነሳቸውን የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን ከመቅረፍ አንፃር በአዲሱ በጀት አመት በአስተዳደሩ አፅዕኖት ተሰጥቶት እንደሚሰራ ተገለፀ።
በኢፌዴሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የድሬዳዋ አስተዳደር እንደራሴዎች እና የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት ተመራጮች ከመረጣቸዉ ህዝብ ጋር የሚወያዩበት የህዝብ ዉክልና ማጠቃለያ መድረክ ተካሄደ። በኢፌዴሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የድሬዳዋ አስተዳደር እንደራሴ የሆኑት አቶ አብዱልጃዋድ መሀመድ በመድረኩ ላይ ተመራጮችና የህዝብ ዉክልና ያላቸዉ አካላት ከመረጧቸዉ ህዝብ ጋር በልማት፣በመልካም አስተዳደር፣የማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮችን አስመልክተው ሀሳባቸውን በማድመጥ የህዝብ ዉክልና የሚወጡበት…
ጳጉሜ 2 የህብር ቀን በድሬዳዋ አስተዳደር በአካል ብቃት እንቅስቃሴና በእግር ጉዞ መርሀግብር ተከበረ ።
የጳጉሜን ወር ቀናትን በተለያዩ ስያሜዎች በመሰየም በተለያዩ ስነ ስርዓቶች እየተከበረ እንደሚገኝ ይታወቃል። ጳጉሜን 2 የህብር ቀን ምክንያት በማድረግ የአካል ብቃት እንቅስቃሴና የእግር ጉዞ ተካሄዷል። በአካል ብቃት እንቅስቃሴ እና በእግር ጉዞ መርሀግብሩ ላይ የድሬዳዋ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አቶ አርቢ ቡህ ጨምሮ ከፍተኛ አመራሮች እና የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ተሳትፈውበታል ። ደማቅ ከነበረው የአካል ብቃት እንቅሰቃሴ በመቀጠል መነሻውን…
ጷግሜ 2 የህብር ቀን በድምቀት እየተከበረ ነዉ
ጷግሜ 2 የህብር ቀን ህብረብሔራዊ አንድነትን በሚያጠናክሩ ልዩ ልዩ ሁነቶች በአስተዳደሩ በድምቀት እየተከበረ ነዉ ህብረብሔራዊነትን ማዕከል ያደረገ ወንድማማች እና እህትማማችነትን፤የመደጋገፍ የመረዳዳት እሴቶችን በሚጠናክሩ ሰው ተኮር የሆኑ ተግባራት፣ የፓናል ውይይት በማከናወን በአስተዳደሩ በድምቀት እየተከበረ ነዉ በፓናል የውይይት መድረኩም የድሬዳዋ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ክቡር አቶ ሀርቢ ቡህ ፣ምክትል አፈጉባኤ ክብርት ወ/ሮ ከሪማ አሊ የብልጽግና ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮች…


