ታላቁ ህዳሴ ግድብ ተጠናቆ ለመመረቅ በተዘጋጀበት ጊዜ “የጽናት ቀን” ማከብራችን ደስታችንን እጥፍ ድርብ ያደርገዋል ሲሉ የድሬዳዋ ከተማ ነዋሪዎች ተናገሩ
ጳጉሜ አንድ የፅናት ቀን “ፅኑ መሠረት፤ ብርቱ ሀገር ” በሚል መሪ ሃሳብ በድሬዳዋ አስተዳደር በወታደራዊ ትርኢቶች እና በተለያዩ ዝግጅቶች ተከብሯል። ኢትዮጵያ ሀገራችን ሉዓላዊነቷ ተጠብቆ እንዲትቆይ የአባቶቻችን ፅናት እንዲሁም ጀግናው መከላከያ ሰራዊት እና የጠቅላላው የሰላምና ጸጥታ አካላት አስተዋጽኦ እጅግ ከፍተኛ እንደሆነ የድሬዳዋ አስተዳደር ፍትህ ፀጥታና ህግ ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ አቶ አብዱሰላም አህመድ በመግለፅ ምስጋናቸውን አቅርበዋል። በዓሉን…


