በዘንድሮ የተቀናጀ የተፋሰስ ልማት ስራ 11 ሺ አባወራዎችን ተጠቃሚ ለማድረግ ታስቧል::

በድሬዳዋ አስተዳደር በአሰሊሶ ክላስተር ለገዶን ገጠር ቀበሌ “የአፈር ሀብታችን ለብልፅግናችን” በሚል የ2017 ዓ.ም የተቀናጀ የተፋሰስ ልማት ስራ መክፈቻ መርሀ ግብር ተካሄደ። በመርሀ ግብሩ የተገኙት የድሬዳዋ አስተዳደር ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽፈት ቤት ምክትልና የፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ሻኪር አህመድ ባለፉት አመታት በህዝብ ንቅናቄ በተሰሩ የተፋሰስ ልማት ስራዎች ከ50 ሺ ሄክታር በላይ መሬትን ማልማት እንደተቻለ፤ እንዲሁም የአፈር ለምነትን…

Read More

በ 2017 ዓ.ም የተቀናጀ የተፋሰስ ልማት ስራ በ 5,550 ሄክታር መሬት ላይ የአፈርና ውሀ ጥበቃ ስራዎች እንደሚሰሩ ተገለፀ::

”የአፈር ሀብታችን ለብልፅግናችን” በሚል መሪ ሀሳብ የ 2017 ዓ.ም የተቀናጀ የበጋ ወራት የተፋሰስ ልማት ስራዎች ማስጀመሪያ መርሀ-ግብር በበአስተዳደሩ በአራቱም የገጠር ክላስተሮች መካሄድ ጀምሯል። በድሬዳዋ አስተዳደር ከለውጡ ማግስት ከተመዘገቡ በርካታ የለውጡ ስኬቶችና የህዝቡን ተጠቃሚነት በላቀ ደረጃ ተጠቃሚ ካደረጉ ስራዎች መካከል የተቀናጀ የበጋ ወራት የተፋሰስ ልማት በቀዳሚነት እንደሚጠቀስ በቢዮ አዋሌ ክላስተር በኬሀሎ ገጠር ቀበሌ ማስጀመሪያ መረሀ ግብሩን…

Read More

የተቀናጀ የበጋ ወራት የተፋሰስ ልማት ስራ በዋሂል ክላስተር በሚገኙ ገጠር ቀበሌዎች የድሬዳዋ አስተዳደር የብልፀግና ፓርቲ ድሬዳዋ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ኢብራሂም ዩሱፍ በይፋ አስጀመሩ።

በዕለቱ የክብር እንግዳ የብልፀግና ፓርቲ ድሬዳዋ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ኢብራሂም ዩሱፍ ባደረጉት የመክፈቻ ንግግር ድሬዳዋ ዝናብ አጠር ብሎም የጎርፍ አደጋ ተጋላጭ እንደመሆኗ የማያቋርጥ የአፈርና ውሃ ሃብት ጥበቃ ስራ ወሳኝ ነው ብለዋል፡፡የአፈርና ውሃ ጥበቃ ስራ ምርትና ምርታማነትን ማሻሻል ላይ አይነተኛ ሚና ይኖረዋል ብለዋል፡፡ ”የአፈር ሀብታችን ለብልፅግናችን” የሚል መሪ ሃሳብን ያነገበው የዘንድሮ የተፋሰስ ልማት ትግበራ ከዚህ…

Read More

በድሬዳዋ አስተዳደር በአሰሊሶ ክላስተር ለገዶን ገጠር ቀበሌ “የአፈር ሀብታችን ለብልፅግናችን” በሚል መሪ ቃል የ2017 ዓ.ም የተቀናጀ የተፋሰስ ልማት ስራ መክፈቻ መርሀ ግብር እየተካሄደ ይገኛል።

በመርሀ ግብሩም የድሬዳዋ አስተዳደር ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽፈት ቤት ምክትልና የፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ሻኪር አህመድ እንዲሁም በአስተዳደሩ በየደረጃው የሚገኙ አመራሮች ተገኝተዋል። በኤደን ሳሙኤል ፎቶ:- ሰላም አበበ

Read More

የአፈር ሀብታችን ለብልፅግናችን በሚል መሪ ሀሳብ የ 2017 ዓ.ም የተቀናጀ የበጋ ወራት የተፋሰስ ልማት ስራዎች የማስጀመሪያ መርሀ-ግብር የድሬዳዋ አስተዳደር ክቡር ከንቲባ አቶ ከድር ጆሀር እና የአስተዳደሩ ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት በአሁን ሰአት በቢዮአዋሌ ክላስተር በኬሀሎ ገጠር ቀበሌ እየተካሄደ ይገኛል ።

የድሬዳዋ አስተዳደር የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮም በቢዮአዋሌ ክላስተር በኬሀሎ ገጠር ቀበሌ ላይ የሚካሄዱትን አጠቃላይ መረጃዎች ወደ እናንተ የምናደርስም ይሆናል ። በአለማየሁ አበበ ፎቶ :- በቴዎድሮስ ልኡልሰገድ

Read More

“በተፈጥሮ ሀብት በታደለችው ታሪካዊቷ ጅማ ከተማ የተጀመረውን የኮሪደር ልማት ስራ እና የታሪካዊዉን የአባጅፋር ቤተ መንግስት እድሳት ጐብኝተናል።

መንግስታችን የቅርሶችን እድሳት እና የኮሪደር ልማት ስራን በመዲናችን አዲስ አበባ ብቻ ሳይሆን በሌሎች የሀገራችን ከተሞችም በመጀመር ከተሞቻችንን ለነዋሪዎቻቸው ምቹ እና ጽዱ እንዲሆኑ እንዲሁም የቱሪስት መስህብነታቸው እንዲጨምር በርካታ ስራዎችን በማከናወን ላይ ይገኛል። እንግዳ ተቀባይና ሰላም ወዳዱን የጅማ ከተማ እና የአካባቢውን ህዝብ እንኳን ደስ አላችሁ እያልኩ ወደር በማይገኝለት ተሳትፏቸሁ ይህ ራዕይ እውን እንዲሆን በማስቻላችሁ እና ላሳያችሁን ፍቅር…

Read More

ሔር ኢሴ የሶማሌ ኢሳ ማህበረሰብ ያልተፃፈ ባህላዊ ህግ በዮኔስኮ የማይዳስ የሰው ልጆች ወካይ የአለም ቅርስ ሆኖ መመዝገቡን ምክንያት በማድረግ፤ በድሬዳዋ አስተዳደር በተለያዩ መርሀ ግብሮች በዓሉ እየተከበረ ይገኛል።

ማምሻውንም የሶስት ሀገራት ማለትም የኢትዮጲያ፣ የጅቡቲና የሶማሊያ አርቲስቶች የተሳተፉበት ኮንሰርት ተካሂዷል። በኤደን ሳሙኤል ፎቶ:- ረመዳን አደም

Read More

የጅቡቲ ወጣቶችና ባህል ሚንስትር በዶ/ር ሂቦር ሞሚን አሶዌ የተመራ ልኡካን ቡድ ትናንት ማምሻውን ድሬዳዋ ገብቷል።

ልኡካኑ በሲቲ ዞን ላስደሬ የክፍያ መንገድ ሲደርሱ በድሬዳዋ አስተዳደር በምክትል ከንቲባ አቶ ሀርቢ ቡህ እና የሶማሌ ክልል የተለያዩ የስራ ኃላፊዎች አቀባበል አድርገውላቸዋል። ሚንስትሯ ድሬዳዋ የገቡት ሔር ኢሴ በዮኔስኮ መመዝገቡን ምክንያት በማድረግ ከ16-እስከ 17 በተለያዩ ዝግጅቶች የሚከበረውን በአል ለመታደም ነው። በአሉ በፓናል ውይይትና በድሬዳዋ ኢንተርናሽናል ስቴድየም በድምቀት ይከበራል ሲሉ የበአሉ አስተባባሪ ኮሚቴ አባልና በድሬዳዋ አስተዳደር ከተማ…

Read More