Amharic
በድሬዳዋ አስተዳደር ከ1 ሺ 7 መቶ በላይ የሚሆኑ የሚኒሻ አባላት ተመረቁ::
የድሬዳዋ አስተዳደር ፍትህ፣ ፀጥታና ህግ ጉዳዮች ቢሮ ከአስተዳደሩ 38 የገጠር ቀበሌዎች ለተውጣጡ የሚኒሻ ሀይል አባላት ከጥር 1 እስከ 15 /2017 ዓ.ም ሲሰጥ የቆየውን የአቅም ማጎልበቻ ስልጠና ያጠናቀቁ አባላትን በዛሬው ዕለት በድምቀት አስመርቋል።. በምርቃት መርሀ ግብሩ የተገኙት የድሬዳዋ አስተዳደር ክቡር ከንቲባ አቶ ከድር ጁሀር ለተመራቂዎች የእንኳን ደስ አላችሁ መልእክታቸውን በማስተላለፍ፤ 1 ሺ 7 መቶ አርባ አምስት…
የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር የ2017 በጀት ዓመት የሁለተኛ ሩብ ዓመት የማዘጋጃ ቤታዊ፣ የሴክተር ተቋማት፣ የከተማና ገጠር ወረዳዎች የስራ አፈፃፀም ሪፖርት ግምገማ መድረክ መካሄዱን ቀጥሏል::
በዛሬው የከሰዓቱ ውሎ የከተማና ገጠር ወረዳዎች የስራ አፈፃፀም ሪፖርት ግምገማ መድረክ የተካሄደ ሲሆን በከተማና በገጠር ወረዳዎች ላይ እየተሰሩ ያሉ ስራዎች ለመድረኩ ቀርበው ውይይት ተደርጎባቸዋል። የድሬዳዋ አስተዳደር ክቡር ከንቲባ ከድር ጁሃር ወረዳዎች የአካባቢያቸውን ፅዳት በማጠናከር፣ የህብረተሰቡን ቅሬታ የወረዳው ሀላፊ እራሳቸው ቢሮ ተገኝተው እንዲፈቱላቸው፣ የኮሪደር ልማቱ የሚደርስባቸው ወረዳዎች ላይ ህብረተሰቡን አስቀድመው እንዲያወያዩ የሌማት ቱሩፋት እና ዲጂታል መታወቂያ…
ከነዳጅ ጋር ተያይዞ ህገ-ወጥ ስራዎችን በሚሰሩ አካላት ላይ ህጋዊ እርምጃዎች እየሰተወሰደ መሆኑ ተገለፀ
የድሬዳዋ አስተዳደር የ 2017 በጀት ዓመት የ 2 ተኛ ሩብ አመት የማዘጋጃ ቤታዊ ፣ የሴክተር ተቋማት ፣ የከተማና ገጠር ወረዳዎች የስራ አፈፃፀም ሪፖርት ግምገማ መድረክ በዛሬው እለት መካሄደ የጀመረ ሲሆን ሪፖርቱንም የአስተዳደሩ የፕላንና ኢኮኖሚ ልማት ኮሚሽን ኮሚሽነር የሆኑት አቶ ሀይለማርያም ዳዲ ያቀረቡ ሲሆን ሪፖርቱንም መነሻ በማድረግ የተለያዩ ሀሳብ አስተያየቶች ተነስተዋል ። በድሬዳዋ አስተዳደር የቅዳሜ እና…
የኢንደስትሪ ማእከልነት ለማረጋገጥ የሚያስችሉ የልማት ስራዎችን በማገዝ ረግድ በልዩ ትኩረት እየሰራ መሆኑንን የአስተዳደሩ መሬት ልማት ማንጅመንት ቢሮ አስታወቀ፡፡
የድሬዳዋ አስተዳደር ምክርቤት የከተማ ልማት፣ ኮንስትራክሽን እና ማዘጋጃ ቤታዊ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የመሬት ልማትና ማኔጅመንት ቢሮን የ6 ወራት እቅድ አፈፃፀምን ተመልክቷል፡፡ በአስተዳደሩ እየተካሄደ በሚገኘው የኮሪደር ልማት የመልካ ጀብዱ የኮሪደር ልማት፥ የነፃ የንግድ ቀጠና ፣ የምድር ባቡር እና የደረቅ ወድቡን በመኪና ትራንስፖርት በማሳለጥ በኩል ትልቅ አስተዋፅኦ አለው፡፡ ለዚህ ኮሪደር ግንባታ ለተነሺዎች ምትክ ቦታ በመስጠት እና ቦታውን…
የብልፅግና ፓርቲ የድሬዳዋ አስተዳደር ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የ2017 በጀት ዓመት 2ኛ ሩብ አመት የፓርቲ ስራዎች እቅድ አፈፃፀም የግምገማ መድረክ በዛሬው ዕለት ተካሄደ::
የግምገማ መድረኩን የመሩት የድሬዳዋ አስተዳደር ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽፈት ቤት ኃላፊ አቶ ኢብራሂም ዩሱፍ ፓርቲው የመጀመሪያ ታሪካዊ ጉባኤውን ካካሄደ በኋላ አሁን ላይ ሁለተኛ መደበኛ ጉባኤን ለማድረግ በዝግጅት ሂደት ላይ መሆኑን ጠቁመው፤ ከጉባኤ እስከ ጉባኤ የተሰሩ ስራዎች እንደ አስተዳደር ተገምግመው ያሉትን ጠንካራ ጎኖች ለማስቀል ብሎም ደካማ ጎኖች ላይ አተኩሮ ለመስራትም የዛሬው መድረክ የሚያግዝ መሆኑን ተናግረዋል። አቶ ኢብራሂም…
የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት የበጀት፣ ኢኮኖሚ፣ ንግድና ኢንዱስትሪ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ለተከታታይ ቀናት ምልከታ ያደረገባቸውን ጉዳዮች መነሻ በማድረግ የድሬዳዋ አስተዳደር የገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮን የ2017 ዓ/ም የመጀመሪያ 6ወር የስራ አፈፃፀም ግምገማ እና ግብረ መልስ ሰጥቷል
የድሬዳዋ አስተዳደር የገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ እና የቢሮው ተጠሪ ተቋም የሆኑት የገቢዎች ባለስልጣን አመራሮች በተገኙበት የመጀመሪያ 6ወራት የእቅድ አፈጻጸም ሪፓርት ተገምግሟል ። ቋሚ ኮሚቴው የመጀመሪያ 6 ወራት የተቋማት እቅድ አፈጻጸም ለመገምገም በተዘጋጀው ቼክ-ሊስት መሰረት ከአሁን በፊት ለቢሮው የተሰጡ ግብረ_መልሶች ፣የመደበኛ እና የካፒታል ፕሮጀክቶች አፈጻጸም፣ የፋይናንስና ንብረት አያያዝ እና አስተዳደደር፣ የ6ወር የገቢ እቅድ አፈፃፀም የማህበራዊ ሀላፊነት…
በድሬዳዋ አስተዳደር ቋሚ እና ጊዜያዊ የስራ እድል ሊፈጥሩ የሚችሉ 3 ቢሊዮን ብር ካፒታል ያስመዘገቡ 245 ባለሀብቶችን መሳብ መቻሉ ተገለፀ
የድሬዳዋ አስተዳደር የ 2017 በጀት ዓመት የ 2 ተኛ ሩብ አመት የማዘጋጃ ቤታዊ ፣ የሴክተር ተቋማት ፣ የከተማና ገጠር ወረዳዎች የስራ አፈፃፀም ሪፖርት ግምገማ መድረክ በዛሬው እለት እየተካሄደ ሲሆን በሪፖርቱ ከካይዘን ትግበራ ሀብት ብክነት ጋር ተያይዞ በአምራች ኢንዱስትሪዎችና በአገልግሎት ዘርፍ በካይዘን ትግበራ 5 ሚሊዮን ብር ለማዳን ታቅዶ 14,202,900 የሚገመት ሀብት ከብክነት ለማዳን የተቻለ ሲሆን ወደ…
የድሬዳዋ አስተዳደር የ 2017 በጀት ዓመት የ 2 ተኛ ሩብ አመት የማዘጋጃ ቤታዊ ፣ የሴክተር ተቋማት ፣ የከተማና ገጠር ወረዳዎች የስራ አፈፃፀም ሪፖርት ግምገማ መድረክ በመካሄድ ላይ ይገኛል
የስራ አፈፃፀም ሪፖርቱን የአስተዳደሩ የፕላንና ኢኮኖሚ ልማት ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ኃይለማርያም ዳዲ ያቀረቡ ሲሆን በግብርና ሆርቲካልቸር ልማት ባለፍት 6 ወራት 6,825 አርሶ አርብቶ አደሮችን የኤክስቴንሽን አገልግሎት ተጠቃሚ ለማድረግ ታቅዶ 6,631 አርሶ አርብቶ አደሮችን ተጠቃሚ ማድረግ እንደተቻለና ከነዚህም ውስጥ 67.3 % አባወራ 32.7 % እማወራም መሆናቸውን ነው በሪፖርቱ ላይ የተገለፀው ። የህብረት ስራ ማህበራትን ሪፎርም ከማድረግ…
የብልፅግና ፓርቲ የድሬዳዋ አስተዳደር ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የ2017 በጀት ዓመት 2ኛ ሩብ አመት የፓርቲ ስራዎች እቅድ አፈፃፀም የግምገማ መድረክ እየተካሄደ ይገኛል።
የግምገማ መድረኩንም የድሬዳዋ አስተዳደር ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽፈት ቤት ሀላፊ አቶ ኢብራሂም ዩሱፍ እየመሩት ይገኛሉ። በአሁኑ ሰአትም የተጠቃለለ የአስተዳደሩ የፓርቲ ስራዎች ሪፖርት እየቀረበ ይገኛል። በኤደን ሳሙኤል ፎቶ:- ሰላም አበበ


