የድሬዳዋ አስተዳደር ንግድ፣ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ እና ተጠሪ ተቋማት የ2017 ዓ.ም 2ተኛ ሩብ አመት ማጠቃለያ ኮንፍረንስ ዛሬ ተካሄደ።

”ከቃል ወደ ባህል” በሚል መሪ የተካሄደው መድረክ በቢሮውና ተጠሪ ተቋማት የብልፅግና ፓርቲ አባላት የተገኙበት መድረክ ተካሂዷል ። በመድረኩ ላይ የተገኙት የቢሮው ምክትል ኃላፊና አነስተኛና መካከለኛ ማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪ ልማት ዳይሬክተር አቶ አብዲ ሙክታር እንደገለፁት ባለፉት ስድስት ወራት በመሠረታዊ ድርጅት የታቀዱ እቅዶችን ከግብ ለማድረስ በርካታ ስራዎች እንደተሰሩ ገልፀዋል። በተለይም አዳዲስ አባላትን ከማፍራት አንፃርና በሰው ተኮር ስራዎች ላይ…

Read More

የሶማሊያ ፌደራል ሪፐብሊክ ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ መሃሙድ ለይፋዊ ጉብኝት አዲስ አበባ ገቡ

የሶማሊያ ፌደራል ሪፐብሊክ ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ መሃሙድ ለይፋዊ ጉብኝት አዲስ አበባ ገብተዋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለፕሬዝዳንቱ በቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ አቀባበል አድርገውላቸዋል፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኀበራዊ ትስስር ገጻቸው ፤ “የሶማሊያ ፌደራል ሪፐብሊክ ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ መሃሙድ ይፋዊ ጉብኝት ለማድረግ እንኳን ወደ ኢትዮጵያ መጡ እላለሁ” ብለዋል፡፡

Read More

አነስተኛና መካከለኛ ማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪ ክላስተር ልማት ኮርፖሬሽን የገቢ መጠኑን በተሻለ ደረጃ ማሳደጉን አስታወቀ።

የኮርፖሬሽኑ የ2017 ዓ.ም የስድስት ወራት ዕቅድ አፈፃፀም በድሬደዋ አስተዳደር ምክር ቤት የበጀት፣ ንግድና ኢንዱስትሪ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ተገምግሟል። ግምገማው ከዚህ በፊት በኮርፖሬሽኑ ስር በሚተዳደሩ ገበያ ማዕከላት፣ ማምረቻዎችን ወርክ ሾፕ መስክ ምልከታን ግብረ መልስ ያካተተ ሲሆን የቋሚ ኮሚቴው አባላትም ምላሽ የሚሹ ጥያቄዎችን አያይዘው ሠንዝረዋል። አነስተኛ መካከለኛ ማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪ ክላስተር ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ኡስማን…

Read More

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የኢትዮጵያ ሙዓለ ንዋዮች ገበያ (ESX) መርቀው ከፍተዋል።

ይኽ ተግባር የኢትዮጵያን የፋይናንስ ዘርፍ በማዘመን ረገድ ዐቢይ ርምጃ ነው። ESX ለዘርፉ ግልፅነትን የተላበሰ የገበያ ስፍራ ይፈጥራል። በሁለተኛው የሀገር በቀል የኢኮኖሚ ሪፎርም ጥላ ሥርም በኢንቨስትመንት ለሚመራ እድገት በር ይከፍታል። በመንግሥትም በግልም ዘርፎች የፋይናንስ አካታችነትን በማስፋት የቁጠባ እንቅስቃሴን ማሳደግን ብሎም ኢንቬስተሮችን መጠበቅን ታላሚ አድርጎ ተነስቷል። ESX በሶስት የገበያ ክፍሎች ላይ ይሰራል። እነዚህም ለቢዝነስ ተቋማት፣ ለመንግሥት እና…

Read More

የድሬዳዋ አስተዳደር ካቢኔ ዛሬ ባካሄደው መደበኛ ስብሰባ የተለያዩ ውሳኔዎችን አስተላልፏል።

1ኛ :- በአስተዳደሩ በሚገኙ የተለያዩ አካባቢዎች እየተሰራ ያለውን የኮሪደር ልማት ያለበትን አሁናዊ ሁኔታ የአስተዳደሩ የካቢኔ አባላት በዛሬው እለት ሲጎበኙ ከስራ ተቋራጮችና ከኮሪደር ልማት አስተባባሪዎች ጋር ውይይት በማካሄድ ስለ ኮሪደር ልማት ስራው አጠቃላይ ማብራሪያ በተደረገላቸው እና የመጀመሪያው ምዕራፍ የኮሪደር ልማት ዕቅዱ በጥሩ አፈፃፃም እየተከናወነ መሆኑን፣ እንዲሁም የልማት ስራዎቹ ጥራትና ውበቱን ጠብቆ መጠናከር እንዳለበትና አስቸኳይ መፍትሄ ለሚሹ…

Read More

በድሬዳዋ አስተዳደር በሚገኙ የተለያዩ አካባቢዎች እየተሰራ ያለውን የኮሪደር ልማት ያለበትን አሁናዊ ሁኔታ የአስተዳደሩ የካቢኔ አባላት በዛሬው እለት ጎብኝተዋል ።

በዛሬው እለት የነበረው የጉብኝት መርሀ-ግብርም ከመጀመሩ አስቀድሞ የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ክቡር አቶ ከድር ጁሀር እና የካቢኔ አባላት ከስራ ተቋራጮችና ከኮሪደር ልማት አስተባባሪዎች ጋር ውይይት ያካሄዱ ሲሆን በውይይቱም ስለ ኮሪደር ልማት ስራው አጠቃላይ ማብራሪያ እንዲሁም ገለፃ ተደርጎላቸዋል ። በዚህም መሰረት የመጀመሪያው ምዕራፍ የኮሪደር ልማት ዕቅድ በጥሩ አፈፃፃም እየተከናወነ መሆኑን የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ክቡር አቶ ከድር ጁሀር…

Read More

የድሬዳዋ አስተዳደር ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በምስራቅ ኢትዮጵያ ጠንካራ ተቋማትን ለመፍጠር እየሰራ መሆኑን አስታወቀ

ኮሌጁ ይህን ያስታወቀው በምስራቅ ኢትዮጵያ የሚገኙ የቴክኒክና ሙያ ተቋማትን ጋብዘው የልምድ ልውውጥና ጉብኝት በተደረገበት ጊዜ ነው ፡፡ የምስራቅ ኢትዮጵያ የልህቀት ማዕከል የመሆን ራዕይን ሰንቆ የተነሳው ኮሌጅ ብቻውን ተጉዞ የትም እንደማይደረስ በመረዳት በምስራቅ ኢትዮጵያ የሚገኙ የቴክኒክ ሙያ ተቋማት ያለበቸውን ክፍተት የለየና የቀጣይ አቅጣጫን የቀየሰ ምክክርና ጉብኝት ማድረጋቸውን ተገልጿል ፡፡ ከኢንደስትሪ ትስስር በተመለከተ ኮሌጆች የኢንደስትሪዎችን በር ማንኳኳጥ…

Read More