የቻድ ጦር በፕሬዚዳንቱ ቅጥር ግቢ ላይ ያነጣጠረ ጥቃትን ማክሸፉን አስታወቀ።
በከሸፈው ጥቃት 19 ሰዎች መገደላቸውን የሀገሪቱ መንግስት አስታውቋል። ጥቃቱ የደረሰው የቻይናው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዋንግ ዪ በዋና ከተማዋ ኒጃሜና ከመንግስት ባለስልጣናት ጋር ከተገናኙ ከጥቂት ሰአታት በኋላ ነው። በጥቃቱ ቢያንስ 19 ሰዎች ተገድለዋል የተባለ ሲሆን የሀገሪቱ የፀጥታ ኃይሎች ታጣቂዎች በዋና ከተማዋ ኒጃሜና የሚገኘውን የፕሬዚዳንቱን ግቢ ለመውረር ያደረጉትን ሙከራ መከላከል መቻላቸው ተገልፆል። ረቡዕ አመሻሽ ላይ በፕሬዚዳንቱ ጽህፈት…


