በ4 ተኛው ናፍቆት የድሬዳዋ ሳምንት “ዓለማቀፍ የድሬዳዋ ቀን’ በተለያዩ ዝግጅቶች በድምቀት እየተከበረ ይገኛል።

ዛሬ ማለዳ ከጠዋቱ 12:00 ሰዓት ጀምሮ ከምድር ባቡር አደባባይ መነሻውን ያደረገ ስፖርታዊ የአካል ብቃት እንቅስቃሴን ተከትሎ የእግር ጉዞ በአስተዳደሩ የተከናወኑ የኮሪደር ልማት ስራዎች ጉብኝት እንደዚሁም ባለፉት ሶስት ዓመታት የናፍቆት ድሬ ሳምንታት የነበሩ የበዓሉን አጠቃላይ ገፅታ የሚያስቃኝ የፎቶ አውደ ርዕይ እና የድሬ ጣፋጭና ባህላዊ ምግቦች ቅምሻ መርሐግብሮች ተከብሯል ። የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ የተከበሩ አቶ ከር ጁሀርና…

Read More

በ4ተኛው ናፍቆት የድሬዳዋ ሳምንት “አለም አቀፍ የድሬዳዋ ቀን” በተለያዩ መርሃ ግብሮች በድሬዳዋ እየተከበረ ነው

4ኛው ናፍቆት ድሬ አለም አቀፍ የድሬዳዋ ቀን በሚል ስያሜ ከዛሬው የመክፈቻ የእግር ጉዞ የብሄር ሄረሰቦች ባህል፣ ታሪክ፣ ቋንቋና የማንነት መገለጫዎች ላይ ትኩረት ያደረጉ ሲንፖዚየም፣ የስነ-ፅሑፍ ስራዎች፣ስፖርታዊ ውድድሮች የልማት ፕሮጀክቶች ጉብኝት እንዲሁም አብሮነትን በሚያጠናክሩ ሁነቶች ለቀጣይ 5 ቀናት ይከበራል። ናፍቆት ድሬ የድሬዳዋ ተወላጆች እና ወዳጆችን ከመላው ዓለም በሰባሰብ ናፍቆታቸውን ወዳጅነታቸውን የሚያጠናክሩበት ከመሆኑም ባለፈ በአስተዳደሩ በማህበራዊ እና…

Read More

ድሬ ማይክሮ ፋይናንስ በ3ኛው የአፍሪካ የሥራ ዕድል ፈጠራ ፎረም ተሸላሚ ሆነ

ተቋሙ በፎረሙ ለአነስተኛ እና ጥቃቅን ኢንተርፕራይዞች ባበረከተው ከፍተኛ አስተዋጽኦ ተሸላሚ ሆኗል፡፡ 3ኛው የአፍሪካ የሥራ ዕድል ፈጠራ ፎረም ላይ የተሳተፈው ድሬ ማይክሮ ፋይናንስ በሀገር አቀፍ ደረጃ በመንግስት ከተቋቋሙ የአነስተኛ ብድር እና ቁጠባ ተቋማት መካከል ለአነስተኛ እና ጥቃቅን ኢንተርፕራይዞች የላቀ የብድር፣ የቁጠባ እና የሙያ ድጋፍ በመስጠት ሶስተኛ ደረጃ በመውጣት የክሪስታል እና ሰርተፍኬት ተሸላሚ ሆኗል፡፡ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ምክትል ጠቅላይ…

Read More

የድሬዳዋ አስተዳደር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ባለስልጣን የ2017 በጀት አመት የስራ አፈጻጸም በአስተዳደሩ ድጋፋዊ ሱፐርቪዥን ቡድን ተገመገመ

በዚህም ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ በበጀት አመቱ ያከናወናቸው ተግባራት የተከናወኑ በርካታ ሥራዎች በሪፖርት አቅርቧል። የድጋፋዊ ሱፐርቪዥን ቡድኑ የቀረበውን ሪፖርት ከተመለከተ በኋላ ባለስልጣን መስሪያቤቱ ሚሰጡ ግብረመልሶችን በመተግበር ረገድ በአመቱ የተሻለ አፈፃፀም ማስመዝገቡን አንስተዋል። የተሰሩ ስራዎችን መረጃ በአግባቡ በማደራጀት እረገድም ጥሩና ከዚህ በበለጠ እያጠናከሩ መሄድ እንደሚገባ ያስገነዘቡ ሲሆን የድጋፋዊ ክትትሉም አላማ ባለስልጣን መስሪያቤቱ በበጀት አመቱ ያከናወናቸውን ተግባራት አፈፃፀም…

Read More

አስተዳደር ከንቲባ ጽ/ቤትና ተጠሪ ተቋማት የብልፅግና ህብረት የ 2017 ዓ.ም አራተኛ መደበኛ ኮንፍረንስ በደማቅ ሁኔታ ተካሂዷል

በዚህም በኮንፍረንሱ ላይ የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ገበየሁ ጥላሁን ፓርቲው በርካታ ፈተናዎችን በመቋቋም ውጤታማ ስራዎችን በመስራት የህዝቡን ተጠቃሚነት ማሳደጉን ተናግረዋል። የከንቲባ ጽ/ቤት እና የተጠሪ ተቋማት የብልፅግና ፓርቲ በ 2017 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈፃፀም በአመራሩና በአባሉ የአስተሳሰብና የተግባር መቀራረብን ለማምጣት፣ አደረጃጀትና አሰራሮችን በጥብቅ ዲሲፒሊን ተግባራዊ በማድረግ፤ የውስጠ ፓርቲ ተግባራትን ለማጠናከር እና የዲሞክራሲ ስርዓቱን በማጎልበት…

Read More

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ሠራተኞች ጋር የችግኝ ተከላ አካሄዱ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በመትከል ማንሰራራት በሚል መርህ ዛሬ ማለዳ የችግኝ ተከላ መርሐ ግብርን በመቀጠል፤ ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ሠራተኞች ጋር የችግኝ ተከላ አካሂደናል ብለዋል።

Read More

ለአፍሪካ ፍላጎት ከኢትዮጵያ ጋራ እንሰራለን፦ ፕሬዝዳንት ሴሪል ራማፎሳ

የደቡብ አፍሪካው ፕሬዝዳንት ሴሪል ራማፎሳ ከብሪክስ የብራዚል ጉባዔ ጎን ለጎን ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ጋር መክረዋል። ፕሬዝዳንቱ በኤክስ ገጻቸው ላይ እንዳሰፈሩት “ሁሌም ወንድሜን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በማግኘቴ ደስተኛ ነኝ” ብለዋል። በብራዚል ሪዮ ዲጄኔሮ በተካሄደው 17ኛው የብሪክስ ጉባኤ፤ የአፍሪካን ፍላጎት እና ሁለንተናዊ ጥቅም ለማሳደግ በትብብር ለመስራት ቁርጠኛ መሆናቸውንም አረጋግጠዋል።

Read More

በካናዳ ከሚገኙ ሌሎችም የኢትዮጵያ ዲያስፖራዎች ጋር በጋራ በመሆን በኢንቨስትመንት ዘርፍ የመሰማራት ሀሳብ አለን”

አራተኛው ናፍቆት የድሬዳዋ ሳምንት ከሀምሌ 21 እስከ ሀምሌ 25/2017 ዓ.ም “ናፍቆት ድሬ ለድሬዳዋ ብልፅግና” በሚል መሪ ቃል በተለያዩ ሁነቶች ይከበራል። በዚህም በበዓሉ ላይ ለመጀመሪያ ጊዜ ለመሳተፍ ከሰባት ልጆቹና ከባለቤቱ ጋር ከአስር አመታት የካናዳ ቆይታ በኋላ ወደ ድሬዳዋ የመጣው ሰሀል ሀርጌ ድሬዳዋ በከፍተኛ የልማት ግስጋሴ ላይ እንደምትገኝ መመልከቱን ገልጿል። አቶ ሰሀል የድሬዳዋ የአፈተኢሳ ሰፈር ልጅ ሲሆን…

Read More

የዓለም የኢኮኖሚ ሥርዓትን ሚዛናዊ ለማድረግ የተመሰረተው ብሪክስ

የዓለም የኢኮናኖሚ ሥርዓት ለምዕራባውያን ያደላ እንደሆነ ይነገራል፡፡ ይህንን የኢኮኖሚ ሥርዓት ሚዛናዊ ማድረግ ይገባል በሚል ነበር ብሪክስ እኤአ በ2006 የተመሠረተው፡፡ መስራቾቹ ደግሞ ብራዚል፣ ሩሲያ፣ ህንድ እና ቻይና ሲሆኑ፣ ደቡብ አፍሪካ እኤአ በ2010 ጥምረቱን ተቀላቅላለች፡፡ ጥምረቱ የተመሰረተበት ዋና ዓላማ ተባብሮ በመስራት ሀገራቱ ኢኮኖሚያቸውን እንዲያሳድጉ ማድረግ ነው፡፡ የነዚህ ሀገራት ኢኮኖሚ በፍጥነት እያደገ በመምጣቱ ‘ታይገር ኤኮኖሚ’ የሚል ስያሜም አግኝቷል፡፡…

Read More

የኢትዮጵያ እና ቻይና ትብብር

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከቻይናው ጠቅላይ ሚኒስትር ሊ ኪያንግ ጋር በሪዮ ዴጄኔሮ ተገናኝተው በሁለትዮሽ ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል። በወቅቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ፤ ኢትዮጵያ እና ቻይና በማንኛውም ሁኔታ የማይለያዩ ሁለንተናዊ ስትራቴጂካዊ አጋሮች መሆናቸውን እንደተናገሩ ሺንዋ ዘግቧል። ኢትዮጵያ ከቻይና ጋር በኢኮኖሚ፣ በንግድ፣ በኢንዱስትሪ፣ በማዕድን፣ በኮሙኒኬሽን፣ በሰው ሰራሽ አስተውሎት፣ በመሠረተ ልማት፣ በቱሪዝምና በሌሎችም ዘርፎች ያላትን ትብብር ለማጠናከር እንደምትፈልግ…

Read More