በአስተዳደሩ ለ19ሺ ዜጎች የስራ እድል መፈጠሩ ተገለጸ

በድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት የበጀት፣ ኢኮኖሚ ንግድና ኢንድስትሪ ጉዳይ ቋሚ ኮሚቴ የድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮን የ2017 በጀት አመት እቅድ አፈፃፀም ግምገማ እና የመውጫ ውይይት አካሂዷል። በሪፖርቱም በበጀት አመቱ በከተማ እና በገጠር የስራ እድል ፈጠራ በግብርና በማህበራዊ እና በአገልግሎት ዘርፍ በተሰሩ ስራዎች አበረታች ለውጥ መመዝገቡ ተገልጿል። በበጀት አመቱ ለ19 ሺ ዜጎች የስራ እድል መፈጠሩ የተገለጸ…

Read More

ብሪክስ ከጠንካራ አዲስ ሀሳብ ተነስቶ ለዓለም አቀፍ ለውጥ የሚሰራ ብርቱ ኃይል ወደመሆን ተሸጋግሯል፡ – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ብሪክስ ከጠንካራ አዲስ ሀሳብ ተነስቶ ለዓለም አቀፍ ለውጥ የሚሰራ ብርቱ ኃይል ወደመሆን ተሸጋግሯል፤አዳዲስ አባላት በመጨመራቸውም የጋራ ድምፃችን የበለጠ ይጠናከራል ሲሉ ገልጸዋል። አያይዘውም የጋራ ዓላማችን የበለጠ ይጠራል፤ አቅማችንም ይሰፋል ሲሉ ነው ጠቅላይ ሚኒስትሩ የገለጹት፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በሪዮ ዲ ጄኒሮ እየተካሄደ በሚገኘው 17ኛው የብሪክስ ጉባዔ የሰላም፣ የጸጥታ እና ዓለም አቀፍ አመራር…

Read More

የድሬዳዋ የኮሪደር ልማት የከተማዋን ውበት አጉሉቶ ከማውጣቱ ባሻገር የኢንቨስትመንት ማእከልነቷን ያጠናክራል ሲሉ የድሬዳዋ ከተማ ነዋሪዎች ተናገሩ

በድሬዳዋ እየተከናወኑ የሚገኘው የኮሪደር ልማት ስራዎች በመጠናቀቅ ሂደት ላይ ይገኛሉ፤ በዚህም በምድር ባቡር መንገድ እየተሰራ የሚገኘው የኮሪደር ልማት ለከተማዋ በውበት ላይ ውበትን ከመጨመር ባሻገር መንገዱ ለነዋሪዎች ምቾትን እንደፈጠረ እንደሚገኝ የድሬዳዋ ነዋሪዎች ይናገራሉ። በዚህም አስተያየታቸውን ከሰጡን ነዋሪዎች መካከል ወጣት ሀምዲ መሀመድ የኮሪደር ልማቱ የእግረኛና ተሽከርካሪ እንዲሁም የብስክሌትና አረንጓዴ ስፍራዎችን የያዘ በመሆኑ ከዚህ ቀደም የነበረውን የመጨናነቅ ሁኔታ…

Read More

“በረ ቤክ ” በሚል ርእስ በጸሐፊ ሰበኬቤክ ደሜ ትውፊትን መሰረት አድርጎ የተጻፈ የአፋን ኦሮሞ መጽሐፍ ተመረቀ።

የኦሮሞን አፋዊ ስነጽሑፍ እና ትውፊት መነሻ ያደረገው ይህ በ87 ገጾች የተቀነበበው የሰበኬቤክ ደሜ “በረ ቤክ ” መጽሐፍ የኦሮሞን ባህላዊ ዳኝነት እና የፍትህ አሰጣጥ ጥበብ ፣የሞራል ልህቀት፣ ወግና ፍልስፍናና ሀገር በቀል እውቀት ትውፊታዊ መሰረት የቃኘበት መሆኑ በምረቃ ስነስርዓቱ ላይ ተገልጿል።

Read More

በ 15 ዓመታት የለንደን ቆይታዬ የቀሰምኩትን እውቀትና ልምድ ተጠቅሜ ማህበረሰቤን ለማገልገል ዝግጁ ነኝ”

አራተኛው ናፍቆት የድሬዳዋ ሳምንት ከሀምሌ 21 እስከ ሀምሌ 25/2017 ዓ.ም “ናፍቆት ድሬ ለድሬዳዋ ብልፅግና” በሚል መሪ ቃል በተለያዩ ሁነቶች ይከበራል። በዚህም በበዓሉ ላይ ለመጀመሪያ ጊዜ ለመሳተፍ ከ 15 አመታት የለንደን ቆይታ በኋላ ወደ ትውልድ ሀገሩ ድሬዳዋ የመጣው ወጣት አርተን በበዓሉ ለመጀመሪያ ጊዜ ሊሳተፍ በመሆኑ የተሰማውን ከፍተኛ ደስታ ገልጿል። ወጣት አርተን ትውልድና እድገቱ ድሬዳዋ ሲሆን ትምህርቱን…

Read More

የሰቆጣ ቃል ኪዳን ትግበራ ሽፋንን ወደ 334 ወረዳዎች ማድረስ መቻሉ የአመራር ቁርጠኝት ማሳያ ነው፦ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ

የምግብና ሥርዓተ-ምግብ ስትራቴጂ እንዲሁም የሰቆጣ ቃል ኪዳን የ2017 በጀት ዓመት አፈፃፀም ግምገማ መድረክ ተካሂዷል። ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በዚሁ ወቅት፥ በ2017 በጀት ዓመት የሰቆጣ ቃል ኪዳን ትግበራ ሽፋንን ወደ 334 ወረዳዎች ማድረስ መቻሉ የአመራር ቁርጠኝት ማሳያ ነው ሲሉ ተናግረዋል። የምግብና ሥርዓተ-ምግብ ስትራቴጂ፣ የሰቆጣ ካል ኪዳን እና የማህበረሰብ አቀፍ የጤና መድህን ትግበራ ስኬታማ እንዲሆን ህብረተሰቡን…

Read More

የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) መልዕክት

ከብሪክስ መሪዎች ጋር በሪዮ ዲ ጄኒሮ በዚህ አመቱ ጉባኤ ላይ ተገኝተናል። የበለጠ እኩልነት እና ፍትኅ የሰፈነበት ዓለም ለማግኘት ትስስራችንን የበለጠ እናጠናክራለን። የብሪክስ መድረክ የጋራ የልማት እና አለምአቀፋዊ ትብብርን በማሳደግ ረገድ ጠቃሚ ሆኖ ቀጥሏል።

Read More

የብሪክስ ትብብር እየተጠናከረ ነው – ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን

የብሪክስ ትብብር ጠንካራ እየሆነ መምጣቱን ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ገለጹ። ፕሬዚዳንቱ በተንቀሳቃሽ ምስል ለብሪክስ የመሪዎች ጉባኤ ተሳታፊዎች ባስተላለፉት መልዕክት፤ የብሪክስ አባል ሀገራት በጋራ ኢኮኖሚያችንን ልናጠናክር ይገባል ብለዋል። አክለውም ይህን ለማጠናከር ብሔራዊ ገንዘቦችን እውቅና ሰጥተን እርስ በእርስ መገበያየት አለብን ብለው፤ ለዚህ ማሳያም በ2024 ሩሲያ 90 በመቶ ንግዷን የራሷን እና የሌሎች አጋር ሀገራትን መገበያያ ገንዘብ ተጠቅማ ማድረጓን አንስተዋል።…

Read More

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከቻይናው ጠቅላይ ሚኒስትር ሊ ኪያንግ ጋር ተወያዩ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከቻይናው ጠቅላይ ሚኒስትር ሊ ኪያንግ ጋር 55 ዓመታትን ባስቆጠረው የኢትዮ-ቻይና ግንኙነት ላይ ውይይት ማድረጋቸውን ገለጹ። ግንኙነታቸው በሁኔታዎች ሁሉ እንደማይቀያየር አጋሮች፤ ባለፉት ሰባት ዓመታት የሁለቱ ሀገራት ትብብር ጉልህ ፍሬዎችን ማፍራቱንም ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት ጠቁመዋል። ኢንዱስትሪ፣ ማዕድን እና አይሲቲን ባካተቱ ቁልፍ የኢኮኖሚ ዓምዶች ላይ የሚደረገው ትኩረት እንዳለ ሆኖ፤…

Read More