የህዳሴው ግድብ “የዘመናት ህልም ተምኔት ወደ የሚጨበጥ ስኬት የተቀየረበት እና የራሳችንን የእድገት ህልም በራሳችን አቅም ልንፈታ እንደምንችል ለዓለም ያሳየንበት” ነው- ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ
ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ በ6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እና የፌዴሬሽን ምክር ቤት 4ኛ ዓመት የሥራ ዘመን የመክፈቻ ሥነ-ሥርዓት ንግግራቸው የህዳሴው ግድብ የኢትዮጵያን የከፍታ ዘመን ከሚያመላክቱ ክዋኔዎች አንዱ መሆኑን ገልፀዋል፡፡ ፕሬዚዳንቱ ለግድቡ እዚህ መድረስ ሁሉም ኢትዮጵያዊ የነበረው ሚና እጅግ የላቀ እና በክብር መዝገብ ውስጥ በወርቅ ቀለም ተፅፎ በታሪክ የሚቀመጥ እና የሚወደስ ይሆናል ብለዋል፡፡ የግድቡ ግንባታ ከፍፃሜው…


