የ ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ የ 2015 በጀት 1ኛ ሩብ ዓመት ሪፖርት
የ 2015 በጀት 1ኛ ሩብ ዓመት ሪፖርት 2015 BOFED Q1 final neww
የ 2015 በጀት 1ኛ ሩብ ዓመት ሪፖርት 2015 BOFED Q1 final neww
ለሀገር ኅልውና እና ደህንነት ዋጋ የከፈሉ እና የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጆች ጀግኖቻን ክብር ከፍ የሚያደርግ እና ተገቢውን እንክብካቤ እንዲያገኙ የሚያስችል የኢትዮጵያ ጀግኖች የጦር አካል ጉዳተኞች የተሃድሶ እና ሥልጠና ማዕከል ማቋቋሚያ አዋጅ ለመንግሥት መቅረቡን የሴቶች እና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ/ር ኤርጎጌ ተስፋዬ ገለጹ። ሚኒስትሯ ይህን የገለጹት ዛሬ በድሬዳዋ ከተማ እየተካሄደ በሚገኘው ዓለም አቀፍ የአካል ጉዳተኞች ቀን…
የጤና ሚኒስቴር ምኒስትር ዶ/ር ሊያ ታደሰ እና የሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ የሥራ ኃላፊዎች በድሬዳዋ አስተዳደር ተገኝተው የሥራ ጉብኝት አድርገዋል፡፡ ክብርት ሚኒስትሯ የድል ጮራ ሪፈራል ሆስፒታልን፤ የኢትዮ-ፈረንሳይ የድንገተኛ አደጋ ህክምና ማዕከልን እንዲሁም በሳቢያን ጠቅላላ ሆስፒታል እየተገነባ ያለውን የዲያሊሲስ/ የኩላሊት እጥበት አገልግሎት መስጫ ማዕከልን፤ በሆስፒታሉ የህሙማን ቅብብሎሽ ስርዓቱን ለማዘመን የሚረዳውን የኤሌክትሮኒክስ ስርዓት(EMR) እና ሥራ ለማስጀመር በዝግጅት ላይ የሚገኘውን…
በነገው እለትም የፌደራልና የአስተዳደሩ አመራሮች በተገኙበት በተለያዩ መረሀ ግብሮች በአሉ እንደሚከበር ለማወቅ ተችሏል።
በድሬዳዋ አስተዳደር ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ የግንባታ ፈቃድ አሰጣጥና ቁጥጥር ባለሥልጣን ለአስተዳረሩ ጽህፈት ቤት ሀላፊዎች፣ የሂደትና የቀበሌ አመራሮች፣ ከፈተኛ የመንግስት የስራ ሀላፊዎች በተገኙበት በህንፃ አዋጅ ቁጥር 624/2001 ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰቷል፡ በስልጠናው ላይም ፅ/ቤቱ እንደ ግንባታ ቁጥጥር ባለስልጣን በ2006 ዓ.ም የተመሰተረተ ሲሆን በአስተዳደሩ ምክር ቤት በአዋጅ ቁጥር 33/2006 የተቋቋመ መሆኑን የድሬዳዋ አስተዳደር ግንባታ ፍቃድና…
ዘንድሮ ለ30ኛ ጊዜ የሚከበረው የአካል ጉዳተኞች ቀን በዓል በአስተዳደሩ ህዳር 24 /2015 ዓ.ም በተለያዩ መርሃ ግብሮች እንደሚከበር የድሬዳዋ አስተዳደር ሴቶች እና ህፃናት ማህበሪዊ ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ጫልቱ ሁሴን በዛሬው እለት በሰጡት ጋዜጣዊ መግላጫ አስታውቀዋል፡ በዓሉ «አካታች የፈጠራ ስራ እና ሽግግራዊ መፍትሄ በኢትዮጱያ አካል ጉዳተኞች ሁለንተናዊ ተደራሽነት» በሚል መሪ ቃል በተለያዩ መርሃ ግብሮች እንደሚከበር ኃላፊዋ…
የኦሮሚያና ሶማሌ ክልሎች አጎራባች ዞኖች የሰላምና የልማት ኮንፈረንስ በሶማሌ ክልል ሊባን ዞን ጉሬ ዳሞሌ ወረዳ ተካሂዷል። በመድረኩ የኦሮሚያ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አወሉ አብዲ እና የሶማሌ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኢብራሂም ዑስማን እንዲሁም የባሌ ዞን እና ሊበን ዞን አመራሮች ተገኝተዋል፡፡ በኦሮሚያ ክልል ጅብሪ እና በሶማሌ ክልል በጉራ-ዳሞ ኦሌ ወረዳዎች የሚኖሩ የኦሮሞና ሶማሌ ወንድማማች…
የድሬደዋ ዩኒቨርሲቲ ከድሬደዋ አስተዳደር ጋር በተለያዩ መስኮች ተቀራርቦ ሲሰራ የቆየ ሲሆን በተለይም ካለፋት ሦስት ዓመት ወዲህ በተለይ በአቅም ግንባታ ፣ በምርምር እና በማኅበረሰብ አገልግሎት የተለያዩ ተግባራትን ሲያከናውን ቆይቷል፡፡ አሁን ደግሞ ለቀጣይ ሦስት ዓመት የሚቆይና አስተዳደሩን ድህንትና ስራአጥነትን በመቀነስ ልማትና እድገት ለማረጋገጥ የሚያደርገውን እንቅስቃሴ የሚያግዙ ስራዎች በተለያየ ማህበራዊ ና ኢኮኖሚያዊ መስኮች ላይ በጋር መስራት እንዲያስችላቸው የጋራ…
ህዳር 29 ለ17ኛ ጊዜ የሚከበረውን የብሄር ብሄረሰቦች እና ህዝቦች ቀን በዓልን አስመልክቶ በድሬዳዋ አስተዳደር መገናኛ ብዙሀን ድርጅት፣ በድሬደዋ አስተዳደር ምክር ቤትና በድሬዳዋ አስተዳደር መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ የጋራ አዘጋጅነት “ፌደራሊዝም፣ ህብረ ብሔራዊ አንድነትና ህገ-መንግስታዊ ” በሚል መሪ ቃል የተለያዩ ባለድርሻ አካላት በተገኙበት ውይይት ተደርጓል። በቶክ ሾዉ ፕሮግራሙ ላይ በድሬዳዋ ዩኒቨርስቲ የህግ ኮሌጅ ዲን የሆኑት አቶ…
የተከበራችሁ መላው የድሬዳዋ አስተዳደር ነዋሪዎች እና የሀገራችን ዜጎች “ሕብረ ብሔራዊ አንድነት ለዘላቂ ሰላም” በሚል መሪ ቃል በታላቅ ድምቀት ለምናከብረው 17ኛው የኢትዮጵያ ብሔር፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን በዓል እንኳን በሠላም አደረሳችሁ! አደረሰን! በመቀጠልም ሕብረ ብሔራዊ ብዝሃነት ባለባቸው እና ሕገ-መንግሥታዊ ዕውቅና በሰጡ ሀገራት የተዘረጋውን የፌደራል ሥርዓትን ስንመለከት ሌሎች ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ዓላማዎች እንደተጠበቁ ሆኖ በዋናነት ከማንነት ጋር ተያይዘው ለሚነሱ…