ለናፍቆት ድሬዳዋ ሳምንት” ለመታደም ወደ ከተማዋ የተለያዩ እንግዶች እየገቡ ነው።

    “ናፍቆት የድሬዳዋ ሳምንት”ከሐምሌ 11-15/2014 በተለያዩ ዝግጅቶች የሚከበር ሲሆን አስተዳደሩ ለድሬ ተወላጆችና ወዳጆች በአሉን በጋራ እናክብር ጥሪ ተቀብለው እንግዶች ወደ ፍቅር ከተማ ድሬደዋ መግባት ጀምረዋል። ቀድሞም የድሬዳዋ እሴት የሆነው በፍቅር አብሮ መኖርና አብሮ መብላት ፍቅራቸውንና ናፍቆታቸውን እየገለፁ የድሬ ወጣቶች ለበአሉ የሚገቡ እንግዶችን በልዩ ናፍቆት አቀባበል እያደረጉላቸው ይገኛሉ።

    Read More

      “ ባህሉን በአግባብ ና በአዎንታዊ ሁኔታ የሚጠቀም ማህበረሰብ ስብዕናውን በጠንካራ መሰረት ላይ መገንባት ይችላል “

      የድሬዳዋ አስተዳደር ም/ ከንቲባ ክቡር አቶ ሀርቢ ቡህ የባህል እና ስፖርት ሚኒስቴር ከድሬዳዋ አስተዳደር ባህል ና ቱሪዝም ጽ/ቤት ጋር በመተባበር በሀገር አቀፍ የባህል እሴት ግንባታ ላይ የምክክር መድረክ ተካሄደ፡፡ የባህል ና ስፖርት ሚኒስቴር ከድሬዳዋ አስተዳደር ባህል ና ቱሪዝም ጽ/ቤት ጋር በመተባበር “የባህል ዕሴቶቻችን ለዜጎች ስብዕና ግንባታ“ በሚል መሪ ቃል በታላቅ ድምቀት በተለያዩ ባህላዊ ትዕይንቶች ያሸበረቀ…

      Read More

        ጠ/ሚ ዐቢይ የኢትዮጵያ እና ሶማሊያ ግንኙነት ይበልጥ እንደሚጠናከር ያላቸውን እምነት ገለጹ

        የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ኢትዮጵያና ሶማሊያ የሁለትዮሽ ግንኙነታቸውን ይበልጥ እንደሚጠናክሩ ያላቸውን እምነት ገለጹ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በአዲሱ የሶማሊያ ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼህ ማህሙድ በዓለ ሲመት ላይ በሞቃዲሾ ተገኝተው ባደረጉት ንግግር በሶማሊያ ሰላማዊ የስልጣን ሽግግር በመደረጉ መደሰታቸውን ገልጸዋል። ኢትዮጵያ ባለፉት ዓመታት የጋራ እድገት እና ልማት ትብብር ላይ የተመሰረተ የውጭ ግንኙነት ፖሊሲ በመከተሏ ሁለቱ አገራት በቀጣናዊ ትስስር…

        Read More

          ከ ትራንስፖርትና ሎጂስቲክ ሚኒሰቴር ድሬዳዋ ቅሪንጫፍ የተላለፈ ማሳሰቢያ ::

          የታለመለት የነዳጅ ድጎማ ተጠቃሚነት ምዝገባ በሂደት ላይ የሚገኘውን የታለመለት የነዳጅ ድጎማ በቴክኖሎጂ በማገዝ ተግባራዊ ለማድረግ ከትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር ጋር በጋራ እየሠራን እንገኛለን። በዚህም መሠረት በድጎማው ተጠቃሚ እንድትሆኑ የተለያችሁ የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪ ተሽከርካሪ ባለንብረቶች ወይም ህጋዊ ወኪሎች አገልግሎቱ የሚሰጠው በቴሌብር አማካኝነት ስለሆነ በኢትዮ ቴሌኮም የሸያጭ ማዕከላት ዋና ወይም ቅጂ ሊብሬ እንዲሁም የታደሰ መታወቂያ በመያዝ የተሸከርካሪውን…

          Read More

            የኑሮ ውድነትን ለማረጋጋት እየተወሰደ ያለው እርምጃ ለውጥ እያመጣ ነው የድሬዳዋ ነዋሪዎች

            የኑሮ ውድነትን ለመቋቋም በድሬዳዋ የተጀመረው የቅዳሜና የእሁድ ገበያ ሸማቾችና አምራቾችን የሚያገናኝና ወቅታዊውን የኑሮ ውድነት ለመቋቋም የሚያግዝ በመሆኑ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት የድሬዳዋ ነዋሪዎች ተናገሩ፡፡ የግብርና ቢሮ በበኩሉ ባለፉት የገበያ ቀናት አበረታች ውጤት በግብርና ምርቶች ላይ እየተገኘ በመሆኑ ገበያው አመቺ በሆኑ በየአካባቢዎች ይስፋፋል ተብሏል፡፡ በድሬዳዋ አስተዳደር የግብርና ቢሮ የህብረት ስራ ማህበራት ግብአትና ግብይት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ኑረዲን…

            Read More

              ለሶስተኛው ዙር የኮቪድ-19 ወረርሺኝ መከላከያ ክትባት ዘመቻ መሳካት ሁሉም የበኩሉን ድርሻ መወጣት እንዳለበት ተገለፀ ።

              የኮቪድ-19 ወረርሺኝ በሽታ በሀገራችን ብሎም በድሬዳዋ አስተዳደር ከተከሰተበት ጊዜ አንስቶ በሽታውን ከመከካከልና ከመቆጣጣጠር አኳያ ዘርፈ ብዙ ስራዎች ሲሰሩ ቆይተዋል ። በተለይም የኮቪድ-19 ወረርሺኝ በሽታን ለመከላከል እስካሁን በተከናወኑ ሁሉን አቀፍ የመከላከል ተግባራት ባለፍት ሁለት ዙሮች በተሰጠው የኮቪድ-19 ወረርሺኝ መከላከያ ክትባት አማካኝነት የወረርሺኙ ስርጭት መጠንና በበሽታው ለከፍተኛ ህመምና ሞት የሚዳረጉ ህሙማን ቁጥርን መቀነስ ተችሏል ። በድሬዳዋ አስተዳደር…

              Read More

                ኮሚሽነር ዓለሙ መግራ የላቀ ስትራተጂ አመራር በመስጠት የክብር ሜዳይ ተሸለሙ ::

                በመስዋእትነታችን የሀገራችን አንድነትና የህዝባችን ሰላም ይረጋገጣል በሚል መሪ ቃል የፖሊስ የምስጋናና እውቅና ፕሮግራም የሀገሪቱ ጠ/ሚንስትር ዶ/ር አብይ አህመድ በተገኙበት በድምቀት ተካሂዷል ። በዚህ ደማቅ ክብረ በአል ላይ ከፍተኛ ጀብድ የፈፀሙ የፖሊስ አመራር እና አባላት የክብር ሜዳይ ሽልማት የተሸለሙ ሲሆን የድሬዳዋ ፖሊስ ጠቅላይ መምርያ አዘዥ ኮሚሽነር ዓለሙ መግራ የላቀ ስትራተጂ አመራር በመስጠት የክብር ሜዳይ እንዲሁም ም/ኮ…

                Read More

                  የድሬደዋ ደወሌ ምድር ባቡር ያለዉን እምቅ ሀብት በመጠቀም ለከተማዋ ብሎም ለምስራቅ ኢትዮጲያ ኩራት የሆነ ተቋም ለማድረግ እየተሠራ መሆኑ ተገለፀ።

                  በአስተዳደሩ ምክትል ከንቲባ አቶ ሀርቢ ቡህ የተመራ ከተለያዩ ተቋማት የተወጣጡ አመራሮች የድሬደዋ ደወሌ ምድር ባቡርን ጎብኝተዋል።በቅርቡ የሚኒስትሮች ም/ቤት መጋቢት 24 ቀን 2014 ባሣለፈዉ ዉሣኔ የድሬደዋ አስተዳደር ከድሬደዋ እስከ ደወሌ ድረስ ያለዉን የምድር ባቡር ንብረት በባለቤትነት እንዲያስተዳድር መወሠኑ የሚታወስ ነዉ።በጉብኝቱ ላይ የአስተዳደሩ የገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ ሀላፊን ጨምሮ የንብረት ርክክብ ኮሚቴ አባላትና የተለያዩ አመራሮች ተገኝተዋል። ዘገባው…

                  Read More

                    የአለም የአካባቢ ቀን “አንድ ምድር ብቻ” በሚል መሪ ቃል በድሬደዋ ዩኒቨርሲቲ በፓናል ውይይት ተከበረ፡፡

                    ዘንድሮ በአለም አቀፍ ደረጃ ለ49ኛ ጊዜ በሀገራችን ደግሞ ለ29 ጊዜ የተከበረውን የዓለም የአካባቢ ቀንን ምክንያት በማድረግ የድሬደዋ ዩኒቨርሲቲና የድሬደዋ አስተዳደር አካባቢ ፣ደን እና አየር ንብረት ለውጥ ባለስልጣን በመተባበር የፓናል ውይይት አካሂደዋል፡፡ በዚሁ የፓናል ውይይት ላይ በዩኒቨርሲቲው የማህበራዊ ሳይንስና ስነ-ሰብ ኮሌጅ ዲን የሆኑት ዶ/ር አለማየሁ ዘውዴ ባደረጉት የእንኳን ደህና መጣቹህ ንግግራቸው ከጊዜ ወደ ጊዜ በከፍተኛ መጠን…

                    Read More