የባከኑ የህዝብና የመንግስት ሃብቶችን ማስመለስና አጥፊዎችን ተጠያቂ ማድረግ ይገባል ተባለ
የባከኑ የመንግስትና የህዝብ ሃብቶችን ማስመለስና አጥፊዎችን በህግ ተጠያቂ ማድረግ ላይ ትኩረት ተሰጥቶ መሰራት እንዳለበት የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት አባላት አሳሰቡ፡፡ ለገጠሩ ህዝብ ፍትህን ተደራሽ የማድረግ ሥራም ትኩረት ሊሰጠው እንደሚገባ ነው የተገለፀው፡፡ የአስተዳደሩ ምክር ቤት 42ተኛ ዓመታዊ መደበኛ ጉባኤ በአስተዳደሩ የዋና ኦዲተር ጽ/ቤት፤ የምክር ቤቱ ጽ/ቤት፤ የብዙኃን መገናኛ ኤጀንሲ፣ በአስተዳደሩ የመጀመሪያ ደረጃና ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤቶች…


