በድሬዳዋ አስተዳደር 02 ቀበሌ የሚገኙ ነዋሪዎች ለመከላከያ ሰራዊትና ለልዩ ሀይል አባላት የሚሆኑ የስንቅ ማዘጋጀት ስነ-ስርአት እያካሄዱ ነው።
የአሸባሪውን የህውሀት ጁንታ ቡድን ሀገርን የማፈራረስና የመበታተን የሽብር ተግባርና ተልእኮ የማምከንና ህግን የማስከበር ሀገራዊ ጥሪን ተከትሎ የኢ.ፌ.ድ.ሪ መከላከያ ሰራዊት እንዲሁም የልዩ ሀይል አባላት ህግን በማስከበሩ ግዳጅ ላይ ይገኛሉ ። ይህንንም ተከትሎ በድሬዳዋ አስተዳደር ልዩ ስሙ ሳቢያን ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በሚገኙ 22 መንደሮች ነዋሪውን በማስተባበር ለጀግናው የመከላከያ ሰራዊታችንና ለልዩ ሀይል አባላት የሚሆኑ ስንቆችን በማዘጋጀት ላይ ይገኛሉ…


