የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ሰራተኞች በህክምና ላይ የሚገኙ የሀገር መከላከያ ሰራዊት አባላትን ጎብኙ ::
የድሬዳዋ አስተዳደር የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ሰራተኞች እና አመራሮች አሸባሪው የህወኅት ቡድን፤ በሰሜን ዕዝ ላይ ባደረሰው ጥቃት ጉዳት ደርሶባቸው፤ በህክምና ላይ የሚገኙ የሀገር መከላከያ ሰራዊት አባላትን በመጎብኘት በ20ሺ ብር የሚገመት የቁሳቁስ ድጋፍ አደረጉ :: በጉብኝቱ ላይ የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ሀላፊ አቶ ኢስቂያስ ታፈሰ ባደረጉት ንግግር እንደገለፁት ጀግናዉ የሀገር መከላከያ ሰራዊት አባላት ለሀገራችን ሉዓላዊነት በሚከፍሉት…


