6ኛው ሀገር አቀፍ ምርጫ ግንቦት 28 ቀን 2013 ዓ.ም እንዲሆን ሃሳብ ቀረበ::

    በተያዘው ዓመት የሚካሄደው 6ኛው ሀገር አቀፍ ምርጫ የድምፅ መስጫ ቀን ግንቦት 28 ቀን 2013 ዓ.ም እንዲሆን ሀሳብ ቀረበ። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ከፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር የምርጫ ረቂቅ የጊዜ ሰሌዳን አስመልክቶ የምክክር መድረክ እያካሄደ ነው።

    Read More

      በድሬዳዋ አስተዳደር ገቢዎች ባለስልጣን ከ160 በላይ ለሆኑ ለደረጃ ሀ ግብር ከፋዮች ስልጠና ሰተዋል። ከ14/04/2013 ዓም እስከ 16/04/2013 ዓም ድረስ ለደረጃ ሀ ግብር ከፋዮች ::

      ለሆቴል፣ግሮሰሪ፣ለልኳንዳቤቶች፣ህንፃ መሳሪያ፣ ስፔር ፓርት እና ሌሎች ዘርፍ ላይ በሂሳብ መዝገብ አያያዝ መመሪያ ዙሪያ ግንዛቤ ማስጨበጫ የተሰጠ ሲሆን ከሂሳብ ሰነድ አያያዝ እስከ ሂሳብ መግለጫ ያለውን ያጠቃለለ ነው። ዘርፉ በከፍተኛ ሁኔታ ግብይት ስለሚካሄድበት በዘርፉ ያለውን በደረሰኝ ያለመገበያየት ችግርንም ለመቅረፍ የሚረዳ መሆኑ ይታወቃል። በስልጠናዉ ላይ የግብር አንባሳደሮቻችን ስለ ግብር መክፈል መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

      Read More

        ሀገር ዓቀፍ የወባ ሳምንት ዘመቻ በይፋ ተጀመረ፡፡

        አንደ ፈረንጆቹ አቆጣጠር በ2030 እንደ ሀገራችን ደግሞ በ2023 ዓ/ም የወባ በሽታን ለማጥፋት በተያዘው ዕቅድ መሰረት ይህንኑ ዕቅድ ተግባራዊ ለማድረግ የሚረዳ ሀገር ዓቀፍ የወባ ሳምንት ዘመቻ በይፋ ተጀምሯል፡፡ የዘመቻውን መጀመር ይፋ ያደረጉት የከንቲባው የማህበራዊ ዘርፍ አማካሪ ተወካይ አቶ መሃመድ አሚን እንደተናገሩት ‹‹በአስተዳደራችንም ይሁን እንደ ሀገር ያለውን የወባ በሽታ ስርጭት ለማስወገድ የሚረዱ ተግባራትን በተለያዩ ጊዜያት በሚካሄዱ ሥራዎች…

        Read More

          የድሬዳዋ አስተዳደር ጤና ቢሮ ከኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ቁጥጥር ባለስልጣን ምስራቅ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ጋር በመተባበር ትላንት በሐረር ከተማ በትምባሆ ቁጥጥር ዙሪያ ውይይት አድርጓል፡፡

          የድሬዳዋ አስተዳደር ጤና ቢሮ “ጤናና ጤና ነክ አገልግሎት ግበዓት ቁጥጥር የሥራ ሂደት መሪ” ሲስተር ሰሪዶ ዑመር አማካኝነት በትምባሆ ቁጥጥር ዙሪያ በድሬዳዋ የተሰሩ ስራዎች በሪፖርት መልክ አቅርቧል፡፡ በቀረበው ሪፖርት መሰረት በሀገራችን የትምባሆ ቁጥጥር ምን እንሚመስል እና ምን ደረጃ ላይ እንደሚገኝ፣ ያጋጠማቸውን ተግዳሮቶች ፣ ከህብረተሰቡና ከመንግስት የሚጠበቁ ኃላፊነቶች በተጨማሪም ትንባሆን ለመከላከል በወጣው አዋጅ ዙሪያ ውይይት ተደረጓል፡፡ የውይይቱ…

          Read More

            ለአገር መከላከያ ሰራዊት የሚደረገው ድጋፍ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተገለፀ።

            በጁንታው የህወህት ቡድን በሰሜን እዝ የመከላከያ ሰራዊት ላይ በደረሰው ጥቃት ግዳጅ ላይ ሆነው ለቆሰሉና በምስራቅ እዝ ደረጃ 3 ሆስፒታል ላሉ አባላት የገንደ ሀኖሌ ነዋሪዎች ግምታቸው 40ሺህ ብር የሚገመት የፍየል ሙክት ደግፈዋል ። በድጋፍ አሰጣጥ ስነስርአቱ ላይ የምስራቅ እዝ ደረጃ 3 ሆስፒታል ሀላፊ ኮርኔል ብርሀኑ ዘመዴ ህዝቡ ለመከላከያ ሰራዊት እያደረገ ያለው ድጋፍ ህዝባዊ ወገንተኛነትን የሚያሳይ ነው…

            Read More