June 2021
ምስራቃዊ የእድገት ፋና የበጎ አድራጎት ማህበር 6 ተኛውን ሀገር አቀፍ ምርጫ ለመታዘብ ለተመረጡ ታዛቢዎች የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ አዘጋጅቷል ።
በ 2001 ዓ.ም የተመሰረተው ምስራቃዊ የእድገት ፋና የበጎ አድራጎት ማህበር በድሬዳዋ አስተዳደር በሚገኙ በከተማም ሆነ በገጠር ጤና ላይ ፣ ትምህርት ፣ ኤች.አይ.ቪ እንዲሁም የተለያዩ ማህበራዊ ስራዎችን በመስራት ላይ ይገኛል። ምስራቃዊ የእድገት ፋና የበጎ አድራጎት ማህበር እያከናወናቸው ካላቸው ዘርፈ-ብዙ የማህበራዊ አገልግሎት ስራዎች በዘለለ የፊታችን ሰኞ የሚካሄደውን 6 ተኛውን ሀገራዊ ምርጫ ተከትሎ ምርጫው ሰላማዊና ፍትሀዊ በሆነ አግባብ…
በታሪካዊው ቀን ታሪክ እንስራ ሰኞ ሰኔ 14 ቀን 2013 ዓ.ም የድምፅ መስጫ ቀን ዜጎች በሀገራቸው ጉዳይ ላይ የሚወስኑበትና ዲሞክራሲያዊ መብታቸውን የሚያረጋግጡበት ቀን ነው።
ይህንን ታሪካዊ ቀን “ኢትዮጵያን እናልብሳት” በሚል መሪ ቃል እየተከናወነ ያለውን 3ተኛውን የአረንገጓዴ አሻራ ቀን ምክንያት በማድረግ “ምርጫዬን እመርጣለሁ አረንገጓዴ አሻራዬን አኖራለሁ” በሚል መርህ በዚህ ታሪካዊ ቀን ታሪክ እንስራ ፡፡ ስለሆነም መምረጥ ዲሞክራሲያዊ መብታችን ነው ችግኝ መትከል ግን ታሪካዊ ግዴታችን ፤ በመሆኑም በእለቱ ምርጫ እየመረጥን በነብስ ወከፍ 6 ችግኞችን በመትከል ኢትዮጵያን አረንገጓዴ በማልበስ በታሪካዊው ቀን ታሪክ…
የምርምር ጽሁፎች ማቅረቢያ መጽሔት በምሁራን መካከል ጠንካራ ትስስር እንዲኖር ትልቅ አስተዋፆኦ እንደሚኖረው ተገለፀ ።
የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ሃርላ የተሰኘ የምርምር ጽሁፎች ማቅረቢያ መጽሔት (journal) አስመረቀ፡፡ በድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ የምርምርና ማህበረሰብ አገልግት ምክትል ፕሬዝዳንት ፅህፈት ቤት የተዘጋጀውና ከድሬዳዋ ከተማ 12 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በምትገኘው ጥንታዊዋ የሃራላ ከተማ ስም የተሰየመው የምርምር ጽሁፎች ማቅረቢያ መጽሔት (journal) በድሬዳዋ ዩኒቨርስቲ ተመርቋል ። በዚሁም የምረቃ ስነ-ስርዓት ላይ በመገኘት ንግግር ያደረጉት የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት የሆኑት ዶክተር ኡባህ…
ለበርካታ የአስተዳደሩ ነዋሪዎች የስራ እድል የፈጠረውን የራይት የወንዶችና የሴቶች የውበት ሳሎንን የአስተዳደሩ ከፍተኛ አመራሮች ጎብኝተውታል ።
እ.ኢ.አ በ 1991 ዓ.ም በአንድ ደንበርካ ፣ በሁለት ሰከንድ አንድ ማሽን ፣ የጫት ሽርጥና አሮጌ ቴፕ በመያዝ ስራውን ” ሀ ” ብሎ የጀመረው የራይት የወንዶችና የሴቶች የውበት ሳሎን ባለቤት አቶ መዝገቡ ልኡለቃል ወይም በቅጥል ስሙ አብዛኛው የከተማችን ነዋሪዎች የሚያውቁት ኑኑሼ በርካታ የኑሮ ውጣ ውረዶችን በማሳለፍ አሁን ላይ በከተማችን ድሬዳዋ በግንባር ቀደምትነት የሚጠራ የወንዶችና የሴቶች የውበት…
4 ሚሊዮን ብር በሆነ ወጪ በህብረተሰቡና በመንግስት የጋራ ስራ የተሰሩ የልማት ፕሮጀክቶች የምርቃትና የጉብኝት መርሀ-ግብር ተካሂዷል ።
የተለያዩ ማህበራዊ ፣ ኢኮኖሚያዊ የልማት ዘርፎችና ፕሮጀክቶች ውጤታማ የሚሆኑት በተጠናከረ የህብረተሰብ ተሳትፎ ሲሆን በሀገር አቀፍ ደረጃም ሆነ በየአካካባቢው ለሚሰሩ የልማት ፕሮጀክቶች ስኬታማነት የህብረተሰብ ተሳትፎን ማረጋገጥ የሚቻለው በየደረጃው የሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎችን የልማት ጥያቄ መነሻ ያደረጉ የአካባቢ ልማቶችን በመለየት ቅደም ተከተል በመስጠትና የህብረተሰቡን የገንዘብ ፣ የቁሳቁስና የጉልበት አስተዋፆ ወደ ላቀ ደረጃ በማሸጋገር ነው ። ከዚሁ ጋር ተያይዞም…
የብልፅግና ፖርቲ ድሬደዋ አስተዳደር በቢዮ አዋሌ ክላስተር አዋሌ ቀበሌ ከነዋሪዎች ጋር የምረጡኝ ቀስቀሳ አካሂዷል።
በቀስቀሳ ላይ ፖርቲው በማህበራዊ ÷ በኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ዘርፍ በቀጣይ የሚያከናውናቸው እቅዶች ገለፃ የተደረገ ሲሆን በዋናነት ከነዋሪው የሚነሱ የልማት ጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠት እንደሚንቀሳቀስ ተገልጿል። በፖርቲው ስር አዋሌቀበሌን ወክለው ለድሬደዋ ምክርቤት የሚወዳደሩ ሶስት እጩዎችን ማለትም:- * አቶ ኑረዲን መሀመድ *ወ/ሮ ሳኒያ ሙስጠፋ *አቶ ሙራድ ሙክታር ለቀበሌው ነዋሪዎች አስተዋውቋል በተጨማሪ አቶ ኑረዲን መሀመድ እንዳሉት ፖርቲያችን ብልፅግናን ከመረጣቹ በቀበሌ…
የድሬዳዋ አስተዳደር ሳይንስና ቴክኖሎጂ ከኢኖቬሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ጋር በጋር በመተባበር ለባለድርሻ አካላት የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጥቷል ።
የሳይንስና ቴክኖሎጂን አዋጪነት ከግምት ውስጥ በማስገባት በሀገር አቀፍ ደረጃ አደረጃጀት ተፈጥሮለት በክልሎችና በከተማ አስተዳደር ደረጃ የሀገር አቀፍን አቅጣጫ በመከተል የተቋቋመ ሲሆን በዚህም እንደ ሀገር ሰፊ የሆኑ ስራዎች ከመሰራታቸውም በዘለለ በአሁን ሰአት በከተማችን ድሬዳዋም የሀገር አቀፍን አቅጣጫ መሰረት በማድረግ ሳይንስና ቴክኖሎጂ በዳይሬክቶሬት ደረጃ ተቋቁሞ ወደ ተግባር በመግባት በርካታ ስራዎች ተሰርተዋል ። ከዚሁ ጋር ተያይዞም የድሬዳዋ ሳይንስና…
በድሬዳዋ አስተዳደር የብልፅግና ፓርቲ የምርጫ ቅስቀሳና ለፓርላማ የሚወዳደሩ ዕጩዎችን የማስተዋወቅ ስራ ትላንት ምሽት በቀበሌ 08 ተካሄዷል ።
ከቀናት በኋላ በሀገራችን የሚካሄደውን 6 ተኛውን ሀገራዊ ምርጫ ምክንያት በማድረግ የድሬዳዋ ብልፅግና ፓርቲ በድሬዳዋ አስተዳደር በሚገኙ የከተማና ገጠር ቀበሌዎች የተለያዩ የምርጫ ቅስቀሳዎችን ሲያካሄድ ቆይቷል፡፡ የዚሁም አንድ አካል የሆነው የምርጫ ቅስቀሳና ለፓርላማ የሚወዳደሩ ዕጩዎችን የማስተዋወቅ ስራ በትላንትናው ምሽት በቀበሌ 08 በሚገኘው አስታጥቄ ሜዳ ላይ ዕጩዎችን የማስተዋወቅ ፕሮግራም የተካደ ሲሆን በዚሁም ስነ-ስርዓት ላይ በመገኘት ንግግር ያደረጉት የድሬዳዋ…
የአለም አቀፍ ደም ለጋሾች ቀንን ምክንያት በማድረግ በኮካ-ኮላ ፋብሪካ የደም ልገሳ ፕሮግራም ተካሂዷል ።
ደም ከተለያዩ በጎ ፍቃደኛ ከሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎች ተሰብስቦ አደጋ ለደረሰባቸው ፣ የደም ማነስ ላለባቸው ፣ በወሊድ ምክንያት ደም ለሚፈሳቸው ፣ የደም ህክምና ለሚያስፈልጋቸው ህሙማን የድሬዳዋ ጤና ቢሮ ደም ባንክ አገልግሎት ዘርፈ-ብዙ ስራዎችን እያከናወነ የሚገኝ ሲሆን በ 2013 ዓ.ም 5 ሺህ ዩኒት ደም ለመሰብደብ አቅዶ 5 ሺህ 103 ዩኒት ደም መሰብሰብ ችሏል ። ከዚሁ ጋር ተያይዞም…


