“ያለፉትን ማክበር የዛሬዎቹን ማትጋት ነው!!” ይህን የተናገሩት በትራንስፖርት ባለስልጣን ድሬደዋ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ዋና ዳሬክተር ወ/ሮ ሰአዳ አዋሌ ናቸው፡
በቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ለረጅም አመታት በማገልገል በጡረታና በሞት ከተቋሙ የተለዩ ሰራተኞች እና ቤተሰቦቻቸውን ጉብኝት ተካሂዷል፡፡ ወ/ሮ አሰጋሽ ከበደ በተቋሙ ከ1996 -2008 በሂሳብ ክፍል ባለሙያነት ሲያገለግሉ በድንገተኛህመም ተቋሙንከለቀቁ 6 አመት ሆኗቸዋል፡፡ ታድያ ከምንም በላይ ሰውን ተርበዋልና ደንገት ከቤታቸው መቱትን ባልደረቦቻቸውን ሲያፊታቸው ፈክቶ እንባቸው በአይናቸው ሞልቶ ነበር የተቀበሉን፡፡ በዋና ዳይሬክተሯ አማካኝነት የተዘጋጀውን ጥቂት ገንዘብና አስቤዛ ተረክበው በሁኔታው መደናገጣቸውን…


