የድሬዳዋ አስተዳደር የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ አቶ ብሩክ ወርቅነህ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል::
አቶ ብሩክ በመቀጠል እንኳን ለከተራ እና ለብርሃነ ጥምቀቱ በሰላም አደረሳችሁ! ከአሉ በኋላ አያይዘው … በዓለ ጥምቀቱ ለእኛ ለኢትዮጵያውያን ከሃይማኖታዊ ክብረ በዓልነቱ በዘለለ ማኅበራዊ ኑሯችን የሚደምቅበት፣ በልዩ ልዩ አልባሳት የምናጌጥበት፣ ልዩ ልዩ ኅብረ ዜማዎችን የምንሰማበት ባህላዊ እሴቶቻችን የሚስተናገዱበት በዓል ጭምር ነው ብለዋል። እንደ ጥምቀት ያሉ የአደባባይ በዓሎቻችንን በአማረና በደመቀ ሁኔታ እንዲከበሩ ሁላችንም እኩል ልንደክም ይገባል ብለዋል።…


