Amharic
#ዜና “የዛሬ ተመራቂዎች ከስልጠናው ካገኛችሁት እውቀት በተጨማሪ ራሳችሁን በቴክኖሎጂ በማሳደግ ማህበረሰቡን ማገልገል ይጠበቅባቹሀል”
የድሬዳዋ አስተዳደር ክቡር ከንቲባ አቶ ከድር ጁሀር የድሬዳዋ አስተዳደር የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ እና የድሬዳዋ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በጋራ በመሆን በተለያዩ መስኮች ያሰለጠኗቸውን 681 ሰልጣኞች በዛሬው ዕለት በድምቀት አስመርቀዋል:: በምርቃት ስነ-ስርአቱ ላይም የድሬዳዋ አስተዳደር ክቡር ከንቲባ አቶ ከድር ጁሀር በመገኘት ለተመራቂዎች የእንኳን ደስ አላችሁ መልእክታቸውን በማስተላለፍ በሰልጠና ቆይታችሁ ካገኛችሁት እውቀት በተጨማሪ በየጊዜ እራሳችሁን በቴክኖሎጂዎች በማበልፀግ…
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የሚኒስትሮች ምክር ቤትን የ100 ቀን የአፈፃፀም ግምገማ አስጀመሩ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የሚኒስትሮች ምክር ቤትን በመሰብሰብ የማክሮ ኢኮኖሚ እድገት እና ቁልፍ የክዋኔ መስፈሪያዎች የቀረቡበትን የካቢኔ የ100 ቀን የአፈፃፀም ግምገማ አስጀምረዋል። ግምገማው ዓለም አቀፋዊ ፖለቲካዊ እና ኢኮኖሚያዊ ዝንባሌዎችንና ፍኖቶችን በመፈተሽ በኢትዮጵያ ላይ የሚኖራቸውን ተፅዕኖ ተመልክቷል። 8.45 በመቶ በተተነበየው የመጪው ዓመት እድገት የለውጡ አበረታች ውጤቶች አካታች እና ዘላቂ የኢኮኖሚ እድገትን የሚያሳዩ፣ የጨመረ የመንግሥት ገቢ…
የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያው በሩብ ዓመቱ የተሻለ የኢኮኖሚ አፈጻጸም እንዲመዘገብ ማድረጉ ተገለጸ
የ2017 በጀት ዓመት የመጀመሪያው የ100 ቀናት አፈጻጸም ግምገማ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት መካሄድ ጀምሯል። የፕላንና ልማት ሚኒስትሯ ፍጹም አሰፋ (ዶ/ር)፤ በተያዘው በጀት ዓመት የ8 ነጥብ 4 በመቶ እድገት የማስመዝገብ ውጥን መያዙን ተናግረዋል፡፡ በ2017 የመጀመሪያው 100 ቀናት ተግባራዊ የተደረገው የተሟላ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያው የተሻለ የኢኮኖሚ አፈጻጸም እንዲመዘገብ ማድረጉም ነው የተገለጸው፡፡ ይህም የተቀመጠው እድገት እንደሚመዘገብ…
#ዜና | ” ከስልጠናው ያገኘውን እውቀት ወደ መሬት በማውረድ ማህበረሰባችንን እና ሀገራችንን በይበልጥ ከፍ ባለ ደረጃ በማገልገል የብልፅግና ጉዞአችንን አናፋጥናለን ” የብልፅግና ፓርቲ ሁለተኛ ዙር የአቅም ግንባታ ሰልጣኝ አመራሮች።
በድሬዳዋ አስተዳደር “የህልም ጉልበት፤ ለእምርታዊ እድገት” በሚል መሪ ሀሳብ ለ 10 ተከታታይ ቀናት ሲሰጥ የቆየው ሁለተኛ ዙር የብልፅግና ፓርቲ አመራሮች የአቅም ግንባታ ስልጠና በዛሬው እለት ተጠናቅቋል። የስልጠናውን መጠናቀቅ አስመልክቶም ሀሳባቸውን ለድሬዳዋ አስተዳደር መንግስት ኮምኒኬሽን ያካፈሉ ሰልጣኝ አመራሮች በተጨባጭ ሀገራችንን ለማሳደግና የብልፅግና ጉዟችንን ለማሳካት ስልጠናው ከፍተኛ አስተዋፆ እንዳላው በመግለፅ በሁሉም ዘርፎች የተጀመሩ የሪፎርም ስራዎችንንም አጠናክረን ለማስቀጠል…
የድሬዳዋ አስተዳደር የመንግስት ኮሚዪኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ እና የድሬዳዋ አስተዳደር ገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ አመራሮችና ሰራተኞች በጋራ በመሆን በደም እጥረት ምክንያት የሚከሰተውን ሞት ለመቀነስ እንዲቻል በዛሬው እለት የደም ልገሳ መርሀ ግብር አካሄዱ::
በመርሀ-ግብሩ ላይ ደም ሲለግሱ ያነጋገርናቸው ተሳታፊዎች በተለያዩ ጊዜያት የሚለገሰው ደም በየሆስፒታሉ በወሊድና በተለያዩ ምክንያቶች ደም በማጣት የሚሰቃዩ ወገኖችን ህይወት ለማትረፍ ከፍተኛ አስተዋፆ እንዳለው ተናገረው፤ ደም መለገስ የውስጥ እርካታን እንደሚፈጥርና ሰብአዊነት ተግባር መሆኑንም ገልጸዋል፡፡ አስተያየት ሰጪዎቹ አያይዘውም በቀጣይም በዚህ መልኩ ከስራ ባልደረቦቻቸው ጋር በጋራ በመሆን ደም መለገሳቸውን አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ጠቁመዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለቀድሞ ፕሬዚዳንት ሣሕለ ወርቅ ዘውዴ ምስጋና አቀረቡ፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ኢትዮጵያን በፕሬዚዳንትነት ላገለገሉት ሣሕለ ወርቅ ዘውዴ በኢትዮጵያ መንግሥት ስም ምስጋና አቅርበዋል፡፡ የለውጡ አንዱ ዓላማ ሥርዓትን ማጽናት ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ የሥራ ኃላፊዎች በሕግ የተሰጣቸውን ኃላፊነት በተሰጣቸው ጊዜ ይወጣሉም ብለዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ባስተላለፉት መልዕክት ሌሎች ደግሞ በተራቸው እነርሱን ተክተው ሀገራዊ ዓላማን በትውልድ ቅብብል ከግብ ያደርሳሉም ሲሉ ገልፀዋል።…
የድሬዳዋ አስተዳደር በራሱ ገቢ የራሱን ወጪ ለመሸፈን እየተሰሩ ያሉ ስራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ የድሬዳዋ አስተዳደር ገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ ኃላፊ ወ/ ሮ ሙሉካ መሀመድ አስታወቁ
በ2016 ዓ.ም 77 ፐርሰንት የአስተዳደሩ ወጪ በራሱ ገቢ መሸፈኑን ያነሱት ኃላፊዋ በቀጣይ በ 2017 ዓ.ም አስተዳደሩ ሙሉ በሙሉ የራሱን ወጪ የሚችልበትን ሁኔታ ለማመቻቸት ስራዎች በተጠናከረ መልኩ እየተሰሩ መሆናቸውን ኃላፊዋ ተናገረዋል፡፡ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ አጠቃላይ ሁኔታን መሰረት አድርጎም የህዝቡን ጥያቄዎች ለመመለስና በአገልግሎት፣ በኢንደስትሪና በግብርናው ዘርፍ ያሉትን ገቢ ለማሳደግ ብሎም በአጠቃላይ የአስተዳደሩን ገቢ ለመጨመር ስራዎች በቅንጅትና በርብርብ…
የአፍሪካ ቀንድ ሠላም እና ደህንነት አስተማማኝ እንዲሆን ኢትዮጵያ ትጉህ ተሳትፎ ታደርጋለች- ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ
የአፍሪካ ቀንድ ሠላም እና ደህንነት አስተማማኝ እንዲሆን ኢትዮጵያ ትጉህ ተሳትፎ እንደምታደርግ ፕሬዚዳንት ታዬ አጽሥላሴ ተናግረዋል፡፡ ፕሬዚዳንቱ በዲፕሎማሲው ረገድ በተለይ ከጎረቤት ሀገራት ጋር ያለውን ሁለንተናዊ ግንኙነት ይበልጥ ለማጠናከር እንደሚሰራ ገልጸዋል፡፡ ኢትዮጵያ ከሶማሌላንድ ጋር በሰጥቶ መቀበል መርህ በደረሰችው ስምምነት አማራጭ ወደብ እና የባህር በር ማግኘት መቻሏን አስታውሰዋል፡፡ ስምምነቱን ተከትሎ “የተፈጠረውን አላስፈላጊ የዲፕሎማሲ ትኩሳት ለማርገብ እና ገጽታዋን ለማጠልሸት…


