የፌደራል መንግስት ኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት ከክልሎች ጋር በናበብ የ2017 ዓ.ም እስትራቴጂክ እቅድ ማቀዱ ይታወሳል።

የድሬዳዋ አስተዳደር መንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ከፊደራል የወረደውን እስትራቲጂ እቅድ ከአስተዳደሩ ነባራዊ ሁኔታ ጋር በማጣጣም እቅዱን በመከለስ የተቋሙ ኃላፊ አቶ ብሩክ ፈለቀ በተከለሰው እቅድ ላይ ከዳሬክቶሬቶች እና ደጋፊ የስራ ሂደት ጋር ተፈራረሙ። አቶ ብሩክ ፈለቀ በፊርማ ስነ ስርዓት እንደተናገሩት እቅዱ ፈፃሚ ባለሙያዋች ድረስ በማውረድ ለተፈፃሚነቱ ኃላፊነታችንን ልንወጣ ይገባል ብለዋል።

Read More

በሚካሔደው የኮሪደር ልማት ጎዳና ላይ የሚጣል የማህበረሰብ ክፍል የለንም ፦ ከንቲባ ከድር ጁሀር

#DGC መስከረም 20/2017 በድሬዳዋ አስተዳደር በወረዳ 03 አካባቢ የኮሪደር ልማቱ በሚያልፍባቸው አካባቢዎች የሚኖሩ የማህበረሰብ ክፍሎችን የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ከድር ጁሀር አወያይተዋል። በውይይቱ የተሳተፉ የወረዳ 03 የልማት ተነሺዎች ጥያቄዎቻቸውን ለከንቲባ ከድር ጁሀር አቅርበዋል፤ ድሬዳዋ ከተማ በልማት ወደኋላ ቀርታለች መልማት አለባት ፤ ልማቷ ግን ህብረተሰቧን ሊጎዳና ጎዳና ሊጥል በሚችል መልኩ መሆን የለበትም ፤ በልማቱ ምክንያት እንድንነሳ የተሰጠን…

Read More

“የከተማ ግብርና ሀገር አቀፉን የምግብ ዋስትና ያጎለብታል”፦ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

የከተማ ግብርናን ሥራ የከተማ የአኗኗር ዘይቤ ስትራቴጂ አካል አድርገን ስናስፋፋ የማሻገር አቅሙ ላይ ጥርት ያለ መረዳት ይዘን ነበር ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገልፀዋል። የከተማ ግብርና የግብርናውን ክፍለ ኢኮኖሚ ከማጎልበቱ ባሻገር የከተማ ምጣኔ ሃብትን እና የሥራ ፈጠራን ያሳድጋል። ሀገር አቀፉን የምግብ ዋስትና ያጎለብታል። የከተማ ልማት ሥራን ይደግፋል። ተጠቃሚዎችን በቀጥታ ከአምራች የአካባቢው ገበሬዎች ጋር ያገናኛል።…

Read More

ድሬዳዋ ከተማ ወላይታ ድቻን በማሸነፍ የሊጉ መሪ ሆኗል

በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የሁለተኛ ሳምንት ጨዋታ ድሬዳዋ ከተማ ወላይታ ድቻን 4 ለ 1 አሸንፏል። በድሬዳዋ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ዩጋንዳዊው ቻርልስ ሙሲጌ እና መሐመድ ኑር ናስር በተመሳሳይ ሁለት ግቦችን ለድሬዳዋ ከመረብ ላይ አሳርፈዋል። ያሬድ ዳርዛ ለወላይታ ድቻ በ75ኛው ደቂቃ ብቸኛዋን ግብ አስቆጥሯል። ውጤቱን ተከትሎ ድሬዳዋ ከተማ በስድስት ነጥብ የሊጉ መሪነት ይዟል። ተጋጣሚው ወላይታ ድቻ በውድድር ዓመቱ…

Read More

#ዜና የ5 ሚሊዮን የኮደርስ ስልጠና ለድሬዳዋ ነፃ የንግድ ቀጣና ልዩ በረከት ነው – ከንቲባ ከድር ጁሀር

#DGC መስከረም 18/2016 የ5 ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን ኮደርስ ስልጠና ኢንሸቲቭ የድሬዳዋ ነፃ የንግድ ቀጣናን የኦን ላይን ግብይት ለማቀላጠፍ መልካም እድል መሆኑን የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ከድር ጁሀር ገለጹ፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የ”5 ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን ኮደርስ” በ2026 አምስት ሚሊዮን ኢትዮጵያውያንን በዌብ ፕሮግራሚንግ፣ አንድሮይድ ማበልፀግ፣ ዳታ ሳይንስና በሰው ሰራሽ አስተውሎት መሠረታዊ የዲጂታል ክህሎት የማስጨበጥ አላማ ያለው ነው።…

Read More

በቀን 150 ሺህ ኩንታል የማምረት አቅም ያለውን የለሚ ብሔራዊ የሲሚንቶ ፋብሪካ መርቀን ሥራ አስጀምረናል።

ይህ ሜጋ ፕሮጀክት የመንግሥታችን በፍጥነት፣ በግዝፈት እና በንፅህና የመገንባት ጽኑ አቋማችን የማሳያ ነው። እጅግ አስፈላጊ የሆኑ መሠረተ ልማቶችን በፍጥነት እና በብቃት አጠናቅቆ ዝግጁ የማድረግ ተምሳሌትም ነው። ይህ በአሁኑ ወቅት በመላ ሀገራችን ያሉ ተመሳሳይ ፋብሪካዎች ተደምረው የሚያመርቱትን ሃምሳ ከመቶ የሚያመርት ፋብሪካ እውን እንዲሆን የተሳተፋችሁ በሙሉ እንኳን ደስ አላችሁ። ከሁለት አመታት በኋላ ወደዚህ ስፍራ ስመለስ የአመራር መርሆዎቻችን…

Read More

በኢትዮጵያ የፈረንሳይ አምባሳደር ሚስተር አሌክሲስ ላሜክ የተመራ የልኡካን ቡድን ለስራ ጉብኝት ዛሬ ማለዳ ድሬዳዋ ገብቷል

#DGC መስከረም 10/2017 አምስት የተለያዩ የፈረንሳይ ሴናተሮችን ያካተተው እና በሚስተር ሀውገስ ሳውሪ የቡድን ፕሬዚዳንትነት እየተመራ ድሬዳዋ አለማቀፍ አየር ማረፊያ የደረሰውን የፈረንሳይ አምባሳደር በአስተዳደሩ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ደማቅ አቀባበል ተደርጎላቸዋል። የልኡካን ቡድኑ በድሬዳዋ አስተዳደር በሚኖረው ቆይታው የቱሪዝም መስህቦችን ታሪካዊ ቦታዎችን የኢንቨስትመንት አማራጮችን እንደሚጎበኝ የወጣው መርሃ ግብር ያመላክታል ። ከሁለት ሳምንት በፊት የሹመት ደብዳቤያቸውን ይዘው ወደ ኢትዮጵያ…

Read More

የናሽናል ሲሚንቶ አክሲዮን ማህበር በአስተዳደሩ ስር ለሚገኙ አስራ አንድ ትምህርት ቤቶች ድጋፍ አደረገ

#DGC መስከረም 9 /2016 የድሬዳዋ ናሽናል ሲሚንቶ አክሲዮን ማህበር ከአንድ ነጥብ ሁለት ሚሊየን ብር በላይ የሚያወጡ የትምህርት መማሪያ ቁሳቁሶችን በዛሬው እለት በገጠር እና በከተማ ለሚገኙ አስራ አንድ የአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ድጋፍ አድርጓል፡፡ የናሽናል ሲሚንቶ አክሲዮን ማህበር ስራ አስፈፃሚ ሚስተር ሊኡ ጄሽንግ በድጋፍ ስነ ስርዓቱ ላይ ተገኝተው ባስተላለፉት መልዕክት ፋብሪካው አገር ከመገንባት ባሻገር የትምህርቱን ዘርፍ…

Read More

#ዜና በድሬዳዋ አስተዳደር በመስኖ ልማት የተሰሩ ስራዎች አበረታችና የአርሶ አደሩን ህይወት የቀየሩ መሆናቸው ተገለጸ

#DGC መስከረም 8/2016 በዛሬው ዕለት ከኢጋድ፣ ከወርልድ ባንክና ከኢ.ፌ.ድ.ሪ ግብርና ሚኒስተር የተውጣጣው ልኡካን ቡድን በድሬዳዋ አስተዳደር ገጠር ቀበሌዎች በምግብ ስርአት ማጠናከሪያ ፕሮግራም /በኤፍ ኤስ አር ፒ / የተሰሩ ስራዎችን ከአስተዳደሩ አመራሮችንና ከሚመለታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በጋራ በመሆን ተዘዋውሮ ጎብኝቷል፡፡ በጉብኝቱም በሁሉ ሞጆ፣ በዱጁማ በኢጃናኒና በገንደ ሬጌ ገጠር ቀበሌዎች በመስኖ ልማትና በወንዝ ጠለፋ፣ በመስኖ ካናል ፕሮጀክት…

Read More

የኢጋድ ልኡካን ቡድን ለስራ ጉብኝት ድሬዳዋ ከተማ ገባ

የኢጋድ ልኡካን ቡድን ማምሻውን ድሬዳዋ ከተማ የገባ ሲሆን ልኡክ ቡድኑ በፉድ ሲስተም ሪዚሊያንስ ፕሮጀክት የተሰሩ ስራዎች እንደሚጎበኝ ከወዲሁ ታውቋል::ልኡክ ቡድኑ ድሬዳዋ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ ሲደርስም ደማቅ አቀባበል ተደርጎላቸዋል:: በኤደን ሳሙኤል ፎቶ፦ ቴድሮሰ ልዑልሰገድ

Read More