አቶ አደም ፋራህ እና አቶ ኦርዲን በድሪ ትናንት በድሬዳዋ ከተማ አሸዋ ገበያ ማዕከል ላይ በእሳት አደጋ የደረሰውን ጉዳት ተመለከቱ

በምክትል ጠቅላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ኃላፊ እና የብልፅግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት አደም ፋራህ እና የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳደር ኦርዲን በድሪ ትናንት በድሬዳዋ ከተማ አሸዋ ገበያ ማዕከል ላይ በእሳት አደጋ የደረሰውን ጉዳት ተመልክተዋል። አቶ አደም ፋራህ በአደጋው ጉዳት የደረሰባቸውን ዜጎች በዘላቂነት መልሶ ማቋቋም ይገባል ብለዋል። በጉብኝቱ ወቅት ክቡር አቶ አደም ፋራህ…

Read More

የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ክቡር አቶ ከድር ጁሀር በትላንትናው እለት በድሬዳዋ ከተማ አሸዋ የገበያ ቦታ ላይ በደረሰው የእሳት አዳጋ ጊዜያዊና ዘላቂ መፍትሔ ለማመላከት ተዘጋጅቶ በቀረበ መሪ እቅድ ላይ ከከፍተኛ የስራ ኃላፊዎችና የካቢኔ አባላት ጋር ተወያይተዋል

አጠቃላይ የጉዳት መጠን መለየትና በቀጣይ የመልሶ ማቋቋም ዝርዝር ተግባራትን ለማመላከት የተዘጋጀው መሪ እቅድ በክቡር ከንቲባው የሚመራ አስራ ሁለት አባላት ያሉት አብይ ኮሚቴና በስሩ አራት ንዑሳን ኮሚቴዎችን በማደራጀት መሪ እቅዱን መነሻ አድርገው በአስቸኳይ ዝርዝር ተግባራትን አቅደው ወደ ስራ እንዲገቡ የሚያስችል ሲሆን ፤ ተጎጂዎችን ማረጋጋት ፣ የጉዳት ልየታና መልሶ ለማቋቋም ንዑስ ኮሚቴው የንብረት ጉዳትን በአይነት ፣ በብዛትና…

Read More

ለአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ መርሀ-ግብር አስፋላጊ የሆኑ የቅድመ-ዝግጅት ስራዎች እየተሰሩ እንደሚገኝ ተገለፀ

በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ {ዶ/ር}የተጀመረው የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ መርሀ-ግብር በተለይም ባለፍት አመታት በሀገራችን ብሎም በድሬዳዋ አስተዳደር በርካታ ችግኞችን መትከል ተችሏል ። በድሬዳዋ አስተዳደርም በያዝነው አመት በከተማም ሆነ በገጠር ከ 3 ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ ችግኞች የሚተከሉ ሲሆን ከዚሁ ጋር ተያይዞም ለሚተከተሉት ችግኞች የሚሆኑ የጉድጓድ ቁፋሮ በዛሬው እለት ተካሄዶል ። በያዝነው አመት እንደ አስተዳደር ከ…

Read More

የጅቡቲ ከተማ ከንቲባ አቶ ሰኢድ ዳውድ በትላንትናው እለት በድሬዳዋ አሰተዳደር በተለምዶ አሸዋ ተብሎ የሚጠራው ገበያ ቦታ የደረሰውን የእሳት አደጋ ማዘናቸው ገለፁ፡፡

ከንቲባው ከድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ክቡር ከድር ጁሃር በስልክ ባደረጉት ግንኙነት የተፈጠረው የእሳት ቃጠሎ ከልባቸው እንዳዘኑና በቀጣይ ከአስተዳደሩ ጎን እንደሚቆሙ አረጋግጠውላቸዋል፡፡ ከንቲባ አቶ ሰኢድ ዳውድ በስልክ መልዕክታቸው ‘’በድሬዳዋ ላይ ስለደረሰው የእሳት ቃጠሎ በመስማቴ በጣም አዝኛለሁ ፣ በዚህ አሳዛኝ ወቅት የጅቡቲ ከተማ አስተዳደር እና የጅቡቲ ዋና ከተማ ህዝብ ከጎናቹ መሆናችንን ልገልፅልህ እወዳለሁ” ብለዋል፡፡ አቶ ሰኢድ ዳውድ አክለውም…

Read More

የቀደመ የጀግንነት ታሪኮቻችንን ድህነትን ድል በማድረግ መድገም እንደሚገባ ተገለፀ

ከተረጂነት ወደ ምርታማነት ለተሟላ ሃገራዊ ሉአላዊነትና ክብር በሚል ርዕስ የተዘጋጀ ህዛባዊ ውይይት ተካሂዷል። በመድረኩ የድሬደዋ አስተዳደር ከንቲባ የተከበሩ ከድር ጁሀር ኢትዮጵያ በተደጋጋሚ የተቃጣባትን የውጭ ወረራና የገዥነት አስተሳሰብን በዜጎቿ አንድነት በመመከት ሉዓላዊነቷን ማስከበሯ ከሀገራችን አልፎ ለሌሎች አፍሪካ ሀገሮች የነፃነት ተምሳሌት ለመሆን በቅታለች፡፡ ይሁን እንጂ የሀገራችን ህዝቦች ለነፃነታቸው የተፋለሙትን ያክል በየጊዜው በሚፈጠሩ ጦርነቶችና እጅግ ኋላቀር የሆነ አስተሳሰብ…

Read More

ድሬዳዋን ለማልማት ሁሉም በየተሰማራበት ዘርፍ የበኩሉን አስተዋፆ መወጣት እንደሚገባው ተገለፀ

የድሬዳዋ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ኮሚሽን ከአፍረን ቀሎ የአትሌቲክስ ክለብ እና ከድሬዳዋ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ጋር በመተበባር “ድሬዳዋን በጋራ እናልማ” በሚል መሪ ቃል የ5 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ እና የማህበረሰብ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ በዛሬው ዕለት በድምቀት አካሄደ። በመረሀ ግብሩ ንግግር ያደረጉት የድሬዳዋ አስተዳደር ክቡር ከንቲባ አቶ ከድር ጁሀር ድሬዳዋን ለማልማት እንደዚህ አይነት እስፖርታዊ ዝግጅቶች በመከናወናቸው መደሰታቸውን…

Read More

በድሬዳዋ አስተዳደር ”የመሬት ማገገም በረሃማነትና ድርቅን መቋቋም” መሪ ቃል የዓለም የአከባቢ ቀን ተከበረ

በስነስርዓቱ ላይ የድሬደዋ አስተዳደር የአከባቢ ደንና አየር ንብረት ለውጥ ባለስልጣን ኃላፊ አቶ አብዱ መሀመድ አባመጋል እንደገለፁት :መሬት እንዲያገግም በማድረግ በረሃማነትና ድርቅን በመቋቋም የተራቆቱ ቦታዎችን በማልማት ከተረጂነት መላቀቅ እና ምርትና ምርታማነት እንዲጨምር አካባቢን መንከባከብ እንደሚያስፈልግ አስገንዝቧል ። የተጎዱ አከባቢዎችን በልዩ ሁኔታ እንዲያገግም በማድረግ ከድርቅ ስጋትና ከድህነት መውጣት እንደሚቻል በዚሁ ወቅት ተገልጿል ። የምግብ ዋስትናን ለማረገጋጥ የሚቻለው…

Read More

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር፥ አቶ ጥላሁን ከበደ በድሬዳዋ አስተዳደር ጉብኝት አካሄዱ

ርዕሰ መስተዳድሩ ድሬዳዋ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ ሲደርሱ የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ከድር ጁሃር ፣ በብልፅግና ፓርቲ የድሬዳዋ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ኢብራሂም ዩሱፍን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች አቀባበል አድርገውላቸዋል። በድሬዳዋ ቆይታቸውም በከተማ ስራ አስኪያጅ ፣ በግብርና ቢሮ ፣ በንግድና ኢንዱስትሪ ፣ በወጣቶችና ስፖርት ኮሚሽን እንዲሁም በስራ እና ክህሎት ቢሮ የተከናወኑ ፕሮጀክቶችን የጉብኝታቸው አካል…

Read More