የአፋን ኦሮሞ ቋንቋን ተረትና ምሳሌ የያዘው “ማክማክሳ” መፅሀፍ ተመረቀ
3 ሺ የአፋን ኦሮሞ ቋንቋን ተረትና ምሳሌ የያዘው “ማክማክሳ” የተሰኘ መፅሀፍ በዛሬው ዕለት በድምቀት ተመርቋል። በመድረኩ በመገኘት ንግግር ያደረጉት የብልፅግና ፓርቲ የድሬዳዋ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ኢብራሂም ዩሱፍ በምርቃት ስነ-ስርአቱ ላይ በመገኘታቸው የተሰማቸውን ደስታ ገልፀው፤ መፅሀፉ ለተማሪዎች እንዲሁም ለመላው ማህበረሰብ እንደሚጠቅም ገልፀዋል። አቶ ኢብራሂም አያይዘውም እንደነዚህ አይነት ባህልና ወግን ለትውልድ የማስተላለፍ ስራ ላይ በመሰማራታቸው…


