የድሬዳዋን የኢንቨስትመንት አማራጮች፣ የቱሪስት መስህቦችና መዳረሻዎችን በማታዋወቅ በኩል የሆቴልና ቱሪስ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ሰራተኞችን አቅም መገንባት አስፈላጊ መሆኑ ተገለጸ

ከድሬዳዋ የንግድና ኢንደስትሪ ማእከልነት ጎዞ ፍጥነት ጋር እኩል መራመድ የሚችል የሆቴልና ቱሪዝም ዘርፍ ልማት ስራ አስፈላጊ መሆኑ የተገለጸው ከአርባ ስድስት ሆቴሎች ለተውጣጡ አንድ መቶ ስልሳ ሰራተኞች ስልጠና ማጠናቀቂያ መድረክ ላይ ነው ፡፡ ለተከታታይ አራት ቀናት የድሬዳዋ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ከሆቴል ባለንብረቶች ማህበር ጋር በመተባበር የተሰጠውስልጠና የሆቴል ምግብና መጠጥ መስተንግዶና እንግዳ ተቀባይ ሰራተኞች አቅም በማጎልበት፤ የአስተዳደሩን…

Read More

የኦቲዝም ግንዛቤ ማስጨበጫ ወርን አስመልክቶ በድሬደዋ ታላቅ የእግር ጉዞ ፕሮግራም ተደረገ።

በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ16ኛ ጊዜ በሀገር አቀፍ ደረጃ ደግሞ ለ22ኛ ጊዜ የኢትዮጵያ የኦቲዝም የግንዛቤ ማስጨበጫ ወርን አስመልክቶ ከለገሀር አደባባይ እስከ ለገሀሬ የእግር ጉዞ መርሀግብር ተከናውኗል። በዚህም ከማለዳ ጀምሮ በማርሽ ባንድ በታጀበው የእግር ጉዞ መዳረሻም የለገሀሬ አካባቢ ነዋሪዎች ለእግር ጉዞው አስተባባሪዎችና ተሳታፊዎች፣ በኦቲዝም ጥላ ስር ለሚገኙ ልጆች እንዲሁም ለወላጆች ደማቅ አቀባበል አድርገውላቸዋል። በመርሀ-ግብሩ ላይ በኦቲዝም ጥላ…

Read More

የድሬዳዋ አስተዳደር ካቢኔ በ2016 በጀት ዓመት እየተተገበሩ የሚገኙ ሜጋ ፕሮጀክቶችን የአፈጻጻም ሪፖርት አድምጦ ገምግሟል

በአስተዳደሩ ከ124 በላይ ፕሮጄክቶች እየተተገበሩ ሲሆን በበጀት ዓመቱ እየተከናወኑ ከሚገኙት ውስጥ ለማህበረሰብ ብልጽግና ቅድሚያ የተሰጣቸው ሜጋ ፕሮጄክቶች በተቀመጠላቸው የግንባታ ጊዜ ውስጥ እንዲጠናቀቁ ከማድረግ አኳያ በተለየ ትኩረት ሊሰራ እንደሚገባ አቅጣጫ ተሰጥቷል ፡፡ የሲቪክ ማእከል ፣ የወጣቶች አካዳሚና ለተለያዩ ቢሮዎች አገልግሎት እንዲውል ታስቦ እየተገነባ ያለው ባለ አምስት ወለል ህንጻ ፕሮጄክቶች ካቢኔው ሪፖርቱን ካደመጠ በኋላ ተዘዋውሮ የጎበኛቸው ሲሆን…

Read More

“በድሬዳዋ አስተዳደር አሁን ላይ እየተከናወኑ የሚገኙት ግዙፍ ፕሮጀክቶች በሀገር አቀፍ ደረጃም በምሳሌ የሚቀርቡ ናቸው”።

በዛሬው ዕለት በሱማሌ ክልል ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ ኢብራሂም ኡስማን የተመራ ልኡካን ቡድን በድሬዳዋ አስተዳደር እየተከናወኑ የሚገኙ ትልልቅ ፕሮጀክቶችን ተዘዋውሮ ጎብኝቷል። ልኡክ ቡድኑ በጉብኝቱም የድሬዳዋ አስተዳደር ሁለገብ ወጣቶች ማዕከልን፣ የክብር ዶ/ር አርቲስት አሊ ቢራ ፖርክን፣ ሲቪክ ሴንተርን እንዲሁም የድሬዳዋ ኢንተርናሽናል እስታዲየምን ጎብኝቷል። በጉብኝቱ ወቅት ያነጋገርናቸው የሱማሌ ብሄራዊ ክልል ም/ ፕሬዝዳንት አቶ ኢብራሂም ኡስማን አሁን ላይ በድሬደዋ…

Read More

ድሬዳዋን ዘመናዊና ለነዋሪዎች ምቹ ለማድረግ የኮሪደር ልማት ከፍተኛ ሚና እንዳለው ተገለፀ

በዛሬው ዕለት የኮሪደር ልማት ድሬዳዋ ላይ ተግባራዊ በሚደረግበት ነጥቦች ዙሩያ የድሬዳዋ አስተዳደር ክቡር ምክትል ከንቲባ አቶ ሀርቢ ቡህ በተገኙበት ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት ተደርጓል። የኮሪደር ልማት በተለያዩ አዋጅችና ደንቦች የተቀመጠ ቢሆንም በተለያዩ ምክንያቶች እንዳልተተገበረ ምክትል ከንቲባው አንስተው፤ የኮሪደር ልማት ድሬዳዋን ለማዘመን ብሎም ለነዋሪዎች ምቹ ለማድረግ ከፍተኛ ድርሻ እንዳለው ገልፀዋል። በመድረኩ በድሬደዋ አስተዳደር የተመረጡ የከተማ…

Read More

1445 ኛዉን የኢድ አልፈጥር በአል በድሬዳዋ አስተዳደር በታላቅ ድምቀት ተከበረ ።

በህዝበ ሙስሊሙ ዘንድ ጉልህ ስፍራ የሚሰጠውና በታላቅ ድምቀት የሚከበረው 1445 ኛው የኢድ አልፈጥር በአል በዛሬው እለት በድሬዳዋ አስተዳደር ተከበረ ተከብሯል በአሉንም ለማክበር ከማለዳው 12 ሰአት አንስቶ በርካታ የእስልምና እምነት ተከታዮች ተክቢራዎችን እያሰሙ ወደ ኢድ ሰላት መስገጃም አምርተዋል ። በበአሉ ላይም በመገኘት ንግግር ያደረጉት የድሬዳዋ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ እና የንግድ ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ ኃላፊ አቶ ሀርቢ…

Read More

የድሬዳዋ አስተዳደር መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ አቶ ብሩክ ፈለቀ ለ1445 ኛውን የኢድ አል-ፊጥር በዓል በማስመልከት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል

ለእናንተ ለወገኖቼ የመልካም ምኞት መግለጫ ለማስተላላፍ በመቻሌ የተሰማኝን ከፍ ያለ ክብርና ልባዊ ደስታ ልገልጽላችሁ እወዳለሁ፡፡ “በዓሉን ስናከብር የመተጋገዝና አብሮ የመኖር የድሬዳዋ ዕሴቶች ይበልጥ እንዲያድጉ በታላቁ የረመዳን ፆም ያሳያችሁት ፍፁም የመረዳዳት፣ የመደጋገፍና የመከባበር መንፈስ ይጎለብት ዘንድ በአብሮነት ልታከብሩት ይገባል ብለዋል። በተቀደሰው የረመዳን ወር ለሀገራችሁ ጸጋና በረከት፣ ሰላምና ፍቅር እንደ ጾማችሁና እንደ ጸለያችሁ ሁሉ፥ በክብረ በዓሉም፣ ከዚያ…

Read More

የድሬዳዋ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ የተከበሩ ሀርቢ ቡህ ለኢድ አል ፈጥር በዓል ያስተላለፉት መልዕክት…….!!

ምክትል ከንቲባ ሀርቢ ቡህ 1 ሺህ 445ኛው ዓመተ ሒጅራ የረመዳን ወር ጾም ፍቺ፣ ዒድ አል ፈጥር በዓልን ምክንያት በማድረግ መልዕክት አስተላልፈዋል። ህዝበ ሙስሊሙ ባለፉት 30 ቀናት በጾምና ጸሎት ማሳለፉን በመጥቀስ የረመዳን ወር ከፈጣሪ ምህረት የሚለመንበት፣ መረዳዳት የሚጠናከርበትና በጎ ተግባራት የሚስፋፋበት ወር በመሆኑ የኢድ በዓልም የደስታ፣ የእዝነትና የርህራሄ የመተሳሰብ፣ ያለው ለሌው በማካፈል በአብሮነት የምናሳልፈው ማህበራዊ ግንኙነትን…

Read More

ድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት አፈ ጉባኤ የተከበሩ ወ/ሮ ፈቲህያ አደን የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት

የተከበራችሁ የአስተዳደራችን የእስልምና እምነት ተከታዮች እንኳን ለ1445ኛው የኢድ አልፈጥር በአል በሰላም አደረሳችሁ የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት በአዲስ ምእራፍ ከተቋቋመ ጊዜ ጀምሮ የህብረተሰቡን ፖለቲካዊ ፣ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጥያቄዎች ለመመለስ የሚያስችሉ ዘርፈ ብዙ ስራዎችን በመስራት ላይ ይገኛል፡፡ በምክር ቤቱ በተቋቋሙ ቋሚ ኮሚቴዎች አማካኝነት የአስተዳደሩን አስፈጻሚ አካላትን የስራ እንቅስቃሴ በመከታተል ፣ በመቆጣጠርና አስፈላጊ ድጋፎችን በማድረግ የብሄር ብሄረሰቦች መኖሪያ…

Read More

የብልፅግና ፓርቲ ድሬዳዋ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት ለመላው የእስልምና ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለ1445ኛዉ የኢድ አል ፊጥር በዓል በሰላም አደረሳችሁ እያለ በዓሉ የሰላምና የጤና እንዲሆንላችሁ ልባዊ ምኞቱን ይገልፃል፡፡

የኢድ አል ፊጥር በዓል ለአገራችንን ሰላም መጎልበት ዱዓ የሚደረግበት፣ የደስታ፣ የዕዝነትና የርህራሄ፣ የመተሳሰብ፣ በተለይም በእስልምና አስተምህሮ መሰረት ያለው ለሌለው አካፍሎ ሁሉም ወገናችን በደስታ የሚውልበት፣ ማህበራዊ ግንኙነትን የሚያጠናክርበት ዕለት እንዲሆን እመኛለው፡፡ ሀገራችን ኢትዮጵያ ባለፉት 6 የለውጥ አመታት በርካታ ፈተናዎች ቢያጋጥሟትም በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ በሳል አመራር ያጋጠሙንን ፈተናዎች ወደ ዕድል በመቀየር በኢኮኖሚ በፖለቲካና ማህበራዊ…

Read More