ሴቶችን በስራ ቦታቸው ላይ ብቁ ውጤታማ እና ተወዳዳሪ እንዲሆኑ የመደገፍ እና ወደ አመራርነት የማምጣት ስራን ትኩረት ሰቶ እየሰራ እንደሚገኝ የድሬደዋ አስተዳደር ትራንስፖርት እና ሎጂስቲከስ ባለስልጣን አስታወቀ

በባለስልጣኑ አለም አቀፉ የሴቶች ቀን ማርች 8 “ሴቶችን እናብቃ ፤ ልማትና ሰላምን እናረጋግጥ!” በሚል መሪ ቃል በተለያዩ መርሀግብሮች ተከብሯል። በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ113ኛ በኢትዮጵያ ለ48ኛ ግዜ የሚከበረው አለም አቀፍ የሴቶች ቀን በአስተዳደራችን በተለያዩ መርሀግብሮች እየተከበረ ሲገኝ በድሬደዋ አስተዳደር ትራንስፖርት እና ሎጂስቲከስ ባለስልጣን የሚገኙ ሰራተኞችም እለቱን በተለያዩ መርሀግብሮች አክብረውታል። በዚሁ መርሀግብር መክፈቻ ላይ የተቋሙን ሀላፊ በመወከል…

Read More

በድሬዳዋ አስተዳደር ለ30 ቀናት ሲካሄድ የነበረው የበጋ ወራት የተቀናጀ የተፋሰስ ልማት ስራ ዘመቻ ተጠናቀቀ

በድሬዳዋ አስተዳደር አሰሊሶ ወረዳ “የተቀነጀ ተፋሰስ ለዘላቂ አረንጓዴ ልማት” በሚል መሪ ቃል ለ30 ቀናት ስካሄድ የነበረው የበጋ ወራት የተፋሰስ ልማት ስራ ዛሬ ተጠናቋል። የድሬዳዋ አስተዳደር ክቡር ከንቲባ አቶ ከድር ጆሀር በመዝጊያ መርሀ ግብር ላይ ባስተላለፉት መልዕክት የበጋ ወራት የተፋሰስ ልማት የበለጸገ አካባቢ እና ኢኮኖሚ በመገንባት ለትውልድ ምንዳ ለማስተላለፍ የላቀ ሚና ያለው መሆኑን ጠቅሰው የዘንድሮው የ30…

Read More

የሴቶችን ሁለንተናዊ ተሳታፊነት ለሀገር ግንባታ የጎላ አስተዋጽኦ አለው – የድሬዳዋ አስተዳደር የከንቲባ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ገበየሁ ጥላሁን።

የድሬዳዋ አስተዳደር የከንቲባ ጽ/ቤት አመራሮች እና ፈፃሚ ባለሙያዋች “ሴቶችን እናብቃ ልማትና ሰላምን እናረጋግጥ!” በሚል መሪ ሀሳብ ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን አክብረዋል። ዕለቱን አስመልክቶ የከንቲባ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ገበየሁ ጥላሁን ባስተላለፉት መልዕክት÷ የሴቶችን መብትና የፆታ እኩልነት በማረጋገጥ በሀገራችን ፖለቲካዊ፣ ማኅበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና የልማት ተሳትፎዎች ላይ ያላቸውን ድርሻ ለማሳደግ በሁሉም ዘርፍ እየሠራን ነው ብለዋል። የጽ/ቤቱ ኃላፊ ከዚህም…

Read More

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከዴንማርክ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ላርስ ራስሙሰን ጋር ተወያዩ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ላርስ ራስሙሰን በበርካታ የሁለትዮሽ እና የባለብዙ ወገን ጉዳዮች ዙሪያ ፍሬያማ ውይይት አድርገዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ከውይይቱ በኋላ፥ ኢትዮጵያ እና ዴንማርክ የቆየ ታሪካዊ ግንኙነት ያላቸው ሀገራት ናቸው ብለዋል። ይህ ግንኙነት ለተጠናከረ የሁለትዮሽ ትብብር ደልዳላ መሠረት ሆኖ የሚያገለግል ነው ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትስስር ገፃቸው ባሰፈሩት ፅሁፍ።

Read More

‹‹ኢትዮጵያ ከአፍሪካ ልማት ባንክ ጋር ያላት አጋርነት ውጤታማ ሆኖ ቀጥሏል። ዛሬ ማለዳ ባንኩ በኢትዮጵያ በሚያካሂዳቸው ፕሮጀክቶች ላይ ከዶክተር አብዱል ካማራ ጋር ተወያይተናል። በተጨማሪም ወንድሜ ዶ/ር አኪንዉሚ አዴሲና የኦባፌሚ አዎሎው የአመራር ሽልማትን በማግኘቱ ይህን ዕድል ተጠቅሜ እንኳን ደስ ያለህ ለማለት እወዳለሁ።›› – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

Read More

የረመዳን ፆም ወርን ምክንያት በማድረግ ለኪነ-ጥበብ ባለሞያዎች እና አርቲስቶች ድጋፍ ተደረገ ።

በተለያዩ የበጎ-አድራጎት ስራዎች ሁሉ ሁሌም ከወገኖቹ ጎን የሆነው የኤንዲ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ባለቤት እና ስራ አስኪያጅ የሆነው ኢንጂነር ነገራ ዱጉማ የረመዳን ፆም ወርን ምክንያት በማድረግ ለኪነ-ጥበብ ባለሞያዎች እና አርቲስቶች የምግብ ፍጆታ እንዲሁም የገንዘብ ድጋፍ ማድረግ ችሏል ። በዛሬው እለት 11 ለሚሆኑ የኪነ-ጥበብ ባለሞያዎች እና አርቲስቶች ድጋፍ የተደረገ ሲሆን የኤንዲ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ባለቤት እና ስራ አስኪያጅ የሆነው…

Read More

በዘንድሮ የተቀናጀ የበጋ ወራት የተፋሰስ ልማት ስራ የአርሶ አደሩን ህይወት በዘላቂነት የሚቀይሩ በርካታ ስራዎች መሰራታቸው ተገለፀ።

በሁለም የገጠር ቀበሌዎች ለ18 ቀናት ሲከናወን የቆየው የ2016 ዓ.ም የተቀናጀ የበጋ ወራት የተፋሰስ ልማት ስራዎች ማጠቃልያ ሪፖርት በዛሬው ዕለት የድሬዳዋ አስተዳደር ክቡር ከንቲባ አቶ ከድር ጁሀር በተገኙበት ቀርቦ ተገምግሟል። በማጠቃለያ መድረኩ ክቡር ከንቲባ አቶ ከድር ጁሀር በተፋሰስ ልማት ስራው ላይ የተሳተፉ በየደረጃው ያሉ አመራሮች ላከናወኑት ስራ ምስጋና ያቀረቡ ሲሆ፤ በዚህ በዘንድሮ የበጋ ወራት የተፋሰስ ልማት…

Read More

#ዜና በድሬዳዋ አስተዳደር አለም አቀፍ የሴቶች ቀን የማጠቃለያ መድረክ ተካሄደ

‘ሴቶችን እናብቃ፤ልማትና ሰላምን እናረጋግጥ!” በሚል መሪ ቃል በአለም አቀፍ ደረጃ ለ113ኛ በኢትዮጵያ ለ48ኛ ጊዜ የሚከበረው አለም አቀፍ የሴቶች ቀን (mARCH 8)የማጠቃለያ መድረክ በድሬዳዋ አአስተዳደር ተካሄደ ። ቀኑን አስመልክቶ በተዘጋጀው መድረክ ላይ በክብር እንግድነት የተገኙት የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ የተከበሩ ከድር ጆሀር ባስተላለፉት መልዕክት ሴቶች በሀገራች በተሰጣቸው የኃላፉነት ቦታ ሁሉ ውጤትን በማስመዝገብ በብቃትና በብልሀት የተሰጣቸውን ኃላፊነት የሚወጡ…

Read More