የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ከአዲስ አበባ አስተዳደር ጋር የነበራቸውን ቆይታ አስመልክቶ በማህበራዊ ሚዲያ የትስስር ገፃቸው የሚከተለውን መልዕክት አስተልምለፏል።

በአዲስ አበባ ቆይታችን ፥ ከከተማ አስተዳደሩ ጋር ለመስራት ከተፈራረምነው የእህት ከተሞች ስምምነት ባሻገር ፥ ሰው ተኮር በሆኑ የልማት ፕሮጀክቶች ጉብኝት የአመራር ሰጪነት ሚናችንን ለማጎልበት የሚረዱ ግብዓቶችን አግኝተናል። የአስተዳደራችን ካቢኔ በቀጣይ፥ በስማርት ሲቲ፥ በተቋማት ሪፎርም ትግበራ እና ምገባ ፕሮግራም፥ እንዲሁም በካፒታል ፕሮጀክቶች አፈፃፀም ዙሪያ ያገኘውን ልምድና ተሞክሮ ወደ መሬት በማውረድ፥ ለድሬዳዋችን ሁለንተናዊ እድገት በይበልጥ እንደሚተጋ አምናለሁ።…

Read More

#ዜና | በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በአጭር ጊዜ ውስጥ እውን የሆኑ ፕሮጀክቶች የሚደነቁ በመሆናቸዉ፥ በድሬዳዋ አስተዳደር በሰው ተኮር ስራዎች የሚተገበሩ እንደሆነ ተገለፀ።

#DGC የካቲት 24/2016 የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ከድር ጁሀር እና ካቢኔያቸው፥ በአዲስ አበባ የተገነቡ ህብረተሰብ ተኮር የልማት ፕሮጀክቶችን ጎብኝተዋል። ቡድኑ ተዘዋውሮ ከጎበኛቸው የልማት ፕሮጀክቶች ውስጥ ተስፋ ብርሀን የምገባ ፕሮግራም፥ የሴቶች ማበልፀጊያ ማዕከል እንዲሁም የለሚ የእንጀራ ማምረቻ ፋብሪካ ፣ የአረንጓዴ ልማትን እና ሌሎች ፕሮጀክቶች ይገኙባቸዋል። ካቢኔው በአጭር ግዜ ተሰርቶ የተጠናቀቀውን የአድዋ መታሰቢያ ሙዝዬምን የጎበኘ ሲሆን፥ ከንቲባ…

Read More

በድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ክቡር አቶ ከድር ጁሀር የተመራ ልኡክ ከአዲስ አበባ ከንቲባ ክብርት ከንቲባ አዳነች አቤቤ እና ካቢኔዎቻቸው ጋር የልምድ ልውውጥ መድረክ አካሂደዋል።

በመድረኩም ሁለቱ አስተደሮች በተለያዩ ዘርፎች ላይ በጋራ መስራት የሚያስችላቸውን የእህትማማች ከተሞች ስምምነት ተፈራርመዋል።

Read More

#ዜና | ህብረተሰቡ በፍትህ ዘርፍ ለሚያነሳቸዉ የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች ተገቢዉን ምላሽ በመስጠት ተአማኒነት ያለዉ የፍትህ ስርአትን መገንባት እንደሚገባ ተገለፀ፡፡

#DGC | የካቲት 2016 ዓ.ም በሶሰተኛ ዙር ለፍ/ቤት ዳኞች፣ዐ/ህጎችና ሌሎች የህግ ባለሞያዎች ሲሰጥ የነበረ የአቅም ማጎልበቻ ስለጠና ተጠናቋል ። በ3ኛ ዙር ለፍ/ቤት ዳኞች፣ዐ/ህጎችናሌሎች የህግ ባለሞያዎችሲሰጥ በነበረ የአቅም ማጎልበቻ ስለጠና መድረክ መጠናቀቂያ ላይ ተገኝተዉ የመዝጊያ ንግግር ያደረጉት እና መልእክት ያስተላለፉት የፌደራልና የድሬዳዋ የፍትህ ተቋማት የጋራ መድረክ ሰብሳቢ ተወካይና የድ/ዳ ፖሊስ ወ/ል/ም/ ዘርፍ ሃላፊ ም/ኮሚሽነር ማኦ ተሾመ”…

Read More

#ዜናሁለቱ ከተማ አስተዳደሮች በጋራ ለመስራት ተስማሙ

#DGC የካቲት23/2016 የአዲስ አበባ እና የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር በጋራ ለመስራት የእህትማማች ከተሞች ስምምነት ተፈራርመዋል:: ሁለቱ ከተሞች በቀጣይ በሰው ተኮር ፣ በአቅም ግንባታ ፣ በልምድ ልውውጥ እንዲሁም በህዝብ ለህዝብ ግንኙነት ላይ በጋራ ለመስራት የተግባቡ ሲሆን÷ ስምምነቱን የሁለቱ ከተማ አስተዳደር ከንቲባዎች ተፈራርመዋል:: በዚህ ወቅት የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ÷የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ልምድና ተሞክሮዎቹን ለማካፈል…

Read More

128ኛው የአድዋ ድል በዓል በአስተዳደሩ በታላቅ ሁነቶች በድምቀት በመከበር ላይ ይገኛል።

የድሬዳዋ አስተዳደር 128ኛው የአድዋ ድል በዓል ድሉን በሚመጥን መልኩ በተለያዩ ሁነቶች በከንቲባ ጽ/ቤት አዳራሽ በርካታ ታዳሚያን በተገኙበት በድምቀት በመከበር ላይ ይገኛል ። የአድዋ የድል በዓል የመላው የጥቁር ህዝቦች ኩራት፣ ጀግንነት ፣የፍቅር የአንድነት ማሳያ የድል በዓል ነዉ። አድዋን በሚዘክረው በዚሁ የድል በዓልም የድሬዳዋ አስተዳደር መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ሀላፊ አቶ ብሩክ ፈለቀ ጨምሮ የአስተዳደሩ ከፍተኛ የመንግስት…

Read More

እንኳን ለ128ኛው የዐድዋ ድል በዓል አደረሳችሁ፡፡

እናቶቻችንና አባቶቻችን ታላቁን የዐድዋ ድል ከሰጡን 128 ዓመታት አስቆጥረናል፡፡ የዐድዋ ድል የሰጠንን ዕሴቶች ግን በሚገባ የተጠቀምንባቸው አይመስለኝም፡፡ ቢያንስ አራቱን ታላላቅ የዐድዋ ድል ዕሴቶች ለሀገር ግንባታ ልንጠቀምባቸው የግድ ይለናል፡፡ የመጀመሪያው ኅብረ ብሔራዊ አንድነት ነው፡፡ ኅብረ ብሔራዊ አንድነት የኢትዮጵያ ዋናው መልኳ መሆኑን ከዐድዋ ዘመቻ በተሻለ ለማሳየት የቻለ ክሥተት በዘመናዊ ታሪካችን አናገኝም፡፡ የዐድዋ ዘመቻ ሁለት ጊዜ ኅብረ ብሔራዊ…

Read More

በድሬዳዋ አስተዳደር ሲካሄድ የነበረው የከፍተኛ ዲቪዚዮን ውድድር በመስቀለኛ ክለብ ሻምፒዮንነት ተጠናቀቀ።

ላለፉት አራት ወራት ሲካሄድ የቆየው የድሬዳዋ አስተዳደር የ2016 ዓ.ም ከፍተኛ ዲቪዚዮን የእግር ኳስ ክለቦች ሻንፒዮና ውድድር በዛሬው ዕለት የፍፃሜ ጨዋታ መስቀለኛን ከ 06 ህብረት በኮንጎ ሜዳ ያገናኘ ሲሆን በመስቀለኛ አሸናፊነት ውድድሩ ተጠናቋል። በዚህ ውድድር የድሬዳዋ አስተዳደር ክቡር ከንቲባ አቶ ከድር ጁሀር ከውድድሩ መጀመሪያ አስከ መዝጊያው ድረስ ከፍተኛ ትኩረት ሰጥተው ክትትልና ድጋፍ ማድረጋቸው ተገልጿል። የዛሬውንም የመዝጊያ…

Read More

9ነኛው የአፍሪካ የትምህርት ቤት ምገባ ቀን በዛሬው እለት በድሬዳዋ አስተዳደር ላይ ተካሄደ።

በአፍሪካ ለዘጠነኛ ጊዜ በሀገራችን ኢትዮጲያ ደግሞ ለአምስተኛ ጊዜ ” ሀገር በቀል የትምህርት ቤት ምገባ መዋለ ንዋይን ማፍሰስ ለተሻለ ትውልድ ግንባታ ” በሚል መሪ ሀሳብ በዛሬው እለት የአፍሪካ የትምህርት ቤት ምገባ ቀን በክብር ዶክተር አርቲስት አሊ ቢራ ስም በተሰየመው ገንደ ገበታ አንደኛና መካከለኛ ትምህርት ቤት ላይ ተካሂዷል ። በዚሁ መርሀ-ግብር ላይም በመገኘት ንግግር ያደረጉት የድሬዳዋ አስተዳደር…

Read More

የአድዋ ድል የኢትዮጵያን ስብራቶች ለመጠገን ትልቅ ትምህርት የሚሰጥ የታሪክ አሻራ መሆኑን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ተመስገን ጥሩነህ ገለጹ።

አድዋ ለዘላቂ ሰላምና ለጠንካራ ሀገረ መንግሥት ግንባታ ሀገር አቀፍ ንቅናቄ ማጠቃለያ መርኃ ግብር በአድዋ ድል መታሰቢያ ተካሂዷል። በዚሁ ወቅት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ተመስገን ጥሩነህ፤ ጀግኖች ኢትዮጵያውያን በአድዋ ጦርነት በተባበረ ክንዳቸውና በአልገዛም ባይነት ወኔያቸው ወራሪ ኃይልን አንበርክከዋል ብለዋል። የአድዋ ድል በህብር፣ በፍቅርና በትብብር የተገኘ ግዙፍ ድል መሆኑን ጠቅሰው፥ የወቅቱ የኢትዮጵያ ጦር በህብረ ብሔራዊ አንድነት የተዋቀረ…

Read More