ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር የምግብ ሥርዓት በመከተል ፍላጎታችንን ለማሳካት እየሰራን ነው፡- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር የምግብ ሥርዓት በመከተል የወደፊት ፍላጎታችንን ለማሳካት እየሰራን ነው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ተናግረዋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በ2ኛው የተባበሩት መንግሥታት የምግብ ሥርዓት ጉባዔ ላይ ባደረጉት ንግግር፤ ኢትዮጵያ የምግብ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ ስትራቴጂና ፖሊሲዎችን ቀርፃ ተግባራዊ እያደረገች ነው ብለዋል፡፡ ኢትዮጵያ ከመጀመሪያው የተመድ የምግብ ሥርዓት ጉባኤ በኋላ፣ ከሀገር በቀል የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያው ጋር…


