“በረ ቤክ ” በሚል ርእስ በጸሐፊ ሰበኬቤክ ደሜ ትውፊትን መሰረት አድርጎ የተጻፈ የአፋን ኦሮሞ መጽሐፍ ተመረቀ።

የኦሮሞን አፋዊ ስነጽሑፍ እና ትውፊት መነሻ ያደረገው ይህ በ87 ገጾች የተቀነበበው የሰበኬቤክ ደሜ “በረ ቤክ ” መጽሐፍ የኦሮሞን ባህላዊ ዳኝነት እና የፍትህ አሰጣጥ ጥበብ ፣የሞራል ልህቀት፣ ወግና ፍልስፍናና ሀገር በቀል እውቀት ትውፊታዊ መሰረት የቃኘበት መሆኑ በምረቃ ስነስርዓቱ ላይ ተገልጿል።

Read More

በ 15 ዓመታት የለንደን ቆይታዬ የቀሰምኩትን እውቀትና ልምድ ተጠቅሜ ማህበረሰቤን ለማገልገል ዝግጁ ነኝ”

አራተኛው ናፍቆት የድሬዳዋ ሳምንት ከሀምሌ 21 እስከ ሀምሌ 25/2017 ዓ.ም “ናፍቆት ድሬ ለድሬዳዋ ብልፅግና” በሚል መሪ ቃል በተለያዩ ሁነቶች ይከበራል። በዚህም በበዓሉ ላይ ለመጀመሪያ ጊዜ ለመሳተፍ ከ 15 አመታት የለንደን ቆይታ በኋላ ወደ ትውልድ ሀገሩ ድሬዳዋ የመጣው ወጣት አርተን በበዓሉ ለመጀመሪያ ጊዜ ሊሳተፍ በመሆኑ የተሰማውን ከፍተኛ ደስታ ገልጿል። ወጣት አርተን ትውልድና እድገቱ ድሬዳዋ ሲሆን ትምህርቱን…

Read More

የሰቆጣ ቃል ኪዳን ትግበራ ሽፋንን ወደ 334 ወረዳዎች ማድረስ መቻሉ የአመራር ቁርጠኝት ማሳያ ነው፦ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ

የምግብና ሥርዓተ-ምግብ ስትራቴጂ እንዲሁም የሰቆጣ ቃል ኪዳን የ2017 በጀት ዓመት አፈፃፀም ግምገማ መድረክ ተካሂዷል። ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በዚሁ ወቅት፥ በ2017 በጀት ዓመት የሰቆጣ ቃል ኪዳን ትግበራ ሽፋንን ወደ 334 ወረዳዎች ማድረስ መቻሉ የአመራር ቁርጠኝት ማሳያ ነው ሲሉ ተናግረዋል። የምግብና ሥርዓተ-ምግብ ስትራቴጂ፣ የሰቆጣ ካል ኪዳን እና የማህበረሰብ አቀፍ የጤና መድህን ትግበራ ስኬታማ እንዲሆን ህብረተሰቡን…

Read More

የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) መልዕክት

ከብሪክስ መሪዎች ጋር በሪዮ ዲ ጄኒሮ በዚህ አመቱ ጉባኤ ላይ ተገኝተናል። የበለጠ እኩልነት እና ፍትኅ የሰፈነበት ዓለም ለማግኘት ትስስራችንን የበለጠ እናጠናክራለን። የብሪክስ መድረክ የጋራ የልማት እና አለምአቀፋዊ ትብብርን በማሳደግ ረገድ ጠቃሚ ሆኖ ቀጥሏል።

Read More

የብሪክስ ትብብር እየተጠናከረ ነው – ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን

የብሪክስ ትብብር ጠንካራ እየሆነ መምጣቱን ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ገለጹ። ፕሬዚዳንቱ በተንቀሳቃሽ ምስል ለብሪክስ የመሪዎች ጉባኤ ተሳታፊዎች ባስተላለፉት መልዕክት፤ የብሪክስ አባል ሀገራት በጋራ ኢኮኖሚያችንን ልናጠናክር ይገባል ብለዋል። አክለውም ይህን ለማጠናከር ብሔራዊ ገንዘቦችን እውቅና ሰጥተን እርስ በእርስ መገበያየት አለብን ብለው፤ ለዚህ ማሳያም በ2024 ሩሲያ 90 በመቶ ንግዷን የራሷን እና የሌሎች አጋር ሀገራትን መገበያያ ገንዘብ ተጠቅማ ማድረጓን አንስተዋል።…

Read More

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከቻይናው ጠቅላይ ሚኒስትር ሊ ኪያንግ ጋር ተወያዩ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከቻይናው ጠቅላይ ሚኒስትር ሊ ኪያንግ ጋር 55 ዓመታትን ባስቆጠረው የኢትዮ-ቻይና ግንኙነት ላይ ውይይት ማድረጋቸውን ገለጹ። ግንኙነታቸው በሁኔታዎች ሁሉ እንደማይቀያየር አጋሮች፤ ባለፉት ሰባት ዓመታት የሁለቱ ሀገራት ትብብር ጉልህ ፍሬዎችን ማፍራቱንም ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት ጠቁመዋል። ኢንዱስትሪ፣ ማዕድን እና አይሲቲን ባካተቱ ቁልፍ የኢኮኖሚ ዓምዶች ላይ የሚደረገው ትኩረት እንዳለ ሆኖ፤…

Read More

በድሬዳዋ አስተዳደር የሞተር አልባ ትራንስፖርት እና የእግረኞች ቀን መርሀ -ግብር በተለያዩ ዝግጅቶች በድምቀት ተከብሯል

የድሬዳዋ አስተዳደር ትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ባለስልጣን የመንገድ ትራፊክ ደህንነት እና መድህን ፈንድ ዳይሬክቶሬት ከድሬዳዋ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ ትራፊክ ቁጥጥር ዳይሬክቶሬት ጋር በመቀናጀት ባካሄደው መርሀ-ግብር ላይ ላለፉት ወራት መሰረታዊ የመንገድ ደህንነት ትምህርትን ተምረው ያጠናቀቁ በቁጥር 35 የተማሪ ትራፊኮችም ተመርቀዋል። በስነ-ስረአቱ የባለስልጣን መስሪያቤቱ ዋና ስራ አስኪያጅ ክብርት ወ/ሮ ሹክሪ አብዱረህማን እንደተናገሩት ማህበረሰቡ አማራጭ የሞተር አልባ ተሽከርካሪዎችንና የእግር…

Read More

ግብርን በታማኝነት መክፈል የሀገር ወዳድነት ምልክት መሆኑ ተጠቆመ

የዜጎችን ኢኮኖሚያዊ እና ማኅበራዊ ተጠቃሚነት በማረጋገጥ የአገርን እድገት ለማስቀጠል ግብር ከፍተኛ ሚና የሚጫወት ሲሆን፤ ይህንን በመረዳት በድሬዳዋ አስተዳደር በተለያዩ ዘርፎች ተሰማርተው ግብራቸውን በታማኝነትና በግንበር ቀደም የሚከፍሉ ግብር ከፋዮች ግብርን በታማኝነት መክፈል የሀገር ወዳድነት ምልክት ነው ሲሉ ይናገራሉ። በዚህም የቢኒያም ብረታ ብረትና የህንፃ መሳሪያ መሸጫ ባለቤት የሆነው ወጣት ቢኒያም ይትባረክ ግብሬን በአግባቡ በመክፈል በተደጋጋሚ ተሸላሚ ሆኛለሁ…

Read More

“ከ17ኛው የብሪክስ ጉባኤ አስቀድሞ ከብራዚል ፕሬዝደንት ሉዊዝ ኢናቺዮ ሉላ ደ ሲልቫ ጋር ተገናኝተን በሁለትዮሽ እና ባለብዙ ወገን ጉዳዮች ላይ ውይይት አድርገናል። የዛሬው ውይይታችን በቅርብ እያደገ የመጣውን የሁለቱ ሀገሮቻችንን ግንኙነት የበለጠ በማጠናከር ረገድ አንድ ርምጃ ወደፊት የወሰደን ሆኗል። በተለያዩ ዘርፎች የንግድ እና ኢንቨስትመንት ትስስሮቻችንን የበለጠ ለማጠናከር ተስማምተናል።”

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

Read More

የአሜሪካ መንግሥት በአፍሪካ ሀገራት ላይ የጣለው የጉዞ ክልከላ ዲፕሎማሲያዊ ግኑኝነትን የሚያሻከር ነው – የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን

የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን የአሜሪካ መንግሥት ያወጣው የጉዞ ክልከላ አዋጅን አስመልክቶ መግለጫ ሰጥቷል። ኮሚሽኑ በመግለጫው፣ የአሜሪካ መንግሥት በተለያዩ ሀገራት በተለይም በአፍሪካ ሀገራት ላይ የጣለው የጉዞ ክልከላ ጉዳት የሚያስከትል መሆኑን አስታውቋል። ማንኛውም ሀገር የዜጎቹን ደኅንነት እና የሀገሩን ሉዓላዊነት የማስጠበቅ መብት እንዳለው እናከብራለን ያለው ኮሚሽኑ፣ የክልከላ አዋጁ ሚዛናዊነትን ያልጠበቀ፣ ተዓማኒነትን እና ረጅም ዘመናትን ያስቆጠረው የአሜሪካ እና የአፍሪካ ግኑኝነትን…

Read More