አወዛጋቢው ንዑስ አንቀፅ እንዲወጣ ተደርጎ የኢትዮጵያ የአደጋ ስጋት ሥራ አመራር አዋጅ ፀደቀ
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው 34ኛ መደበኛ ጉባኤ የኢትዮጵያ የአደጋ ስጋት ሥራ አመራር ረቂቅ አዋጅን በሙሉ ድምፅ አፀደቀ። አዋጁን በተመለከተ ዝርዝር ሪፖርት እና የውሳኔ ሐሳብ በምክር ቤቱ የውጭ ግንኙነት እና የሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ለምክር ቤቱ ቀርቧል። በአዋጁ ረቂቅ ላይ ከዚህ በፊት በተደረጉ ውይይቶች ውዝግብ ፈጥሮ የነበረው ከደመወዝ ላይ የሚቆረጥ መዋጮ በተደረገ ውይይት እና…


