የድሬዳዋ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት የረመዳን ፆም 21ኛ ቀንን ምክንያት በማድረግ የኢፍጣር ፕሮግራም አካሄደ

ፕሮግራሙ ድሬዳዋ የፍቅር እንዲሁም የአብሮነት ተምሳሌት ከተማ መሆኗን የተገለፀ ሲሆን፤ የዛሬው የአፍጢር ፕሮግራምም በክርስትና እምነት ተከታይ እህት ወንድሞች አስተባባሪነት መዘጋጀቱ ተጠቁሟል። ከዚህ በተጨማሪም ት/ቤቱ በድልጮራ ሆስፒታል ለሚገኙ ታካሚዎችና አስታማሚዎች የአፍጢር ግብአቶች ድጋፍ እንዳደረገ ተገልጿል። በአጠቃላይም የዛሬው ፕሮግራም በተማሪዎች መካከል ያለውን የእርስ በእርስ ቅርበት ለመጨመር ታስቦ የተዘጋጀ መሆኑ ተመላክቷል። በአፍጢር መርሀ ግብሩ ሲያስተባብሩ ያነጋገርናቸው የክርስትና እምነት…

Read More

በድሬዳዋ በክርስትና እምነት ተከታዮች የተዘጋጀ የጎዳና ላይ የኢፍጣር መርሀግብር ተካሄደ

የ1446ኛው ዓመተ ሂጅራ የረመዳን ወር ጾምን በማስመልከት የክርስትና እምነት ተከታዮች ለእስልምና እምነት ተከታዮች በለገሀሬ ጎዳና ላይ ደማቅ የኢፍጣር መርሀግብር አካሂደዋል። ሙስሊም ክርስቲያኑ ለዘመናት ያቆዩት የአብሮነት፣የፍቅር፣ የአንድነት እና የስምምነት ምልክት ሆና የምትጠቀሰው ድሬዳዋ ዛሬም ወንድማማች እና እህትማማችነትን በማጠናከር ደማቅ ታሪክ በመስራት ላይ ትገኛለች። በመርሀ ግብሩ ተገኝተው የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የድሬዳዋ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ክቡር አቶ ሀርቢ…

Read More

በድሬዳዋ አስተዳደር በወረዳ 01 የመልካ መንገድ እንዲሁም በኮሪደር ልማት ምክንያት ከይዞታቸው ለተነሱ 261 የልማት ተነሺዎች የተሻሻለው የካሳ ክፍያ ሊሰጥ መሆኑን የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ፅ/ቤት የካሳ ክፍያ መልሶ ማቋቋም ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አስታወቀ

በዛሬው ዕለት የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ፅ/ቤት የካሳ ክፍያ መልሶ ማቋቋም ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ መሀመድ ጃማ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ በወረዳ 01 መልካ ጀብዱ በመንገድ መሰረተ ልማት እንዲሁም በኮሪደር ልማት ምክንያት ከይዞታቸው ለተነሱ 261 የልማት ተነሺዎች በአስተዳደሩ በተወሰነው ልዩ ውሳኔ መሰረት የካሳ ክፍያቸው ከዛሬ መጋቢት 12/2017 ዓ.ም ጀምሮ እንደሚከፈል ገልፀዋል፡፡ አቶ መሀመድ አያይዘውም ማህበረሰቡም ከንቲባ ፅ/ቤት ካሳ…

Read More

የካብኔ ውሳኔዋች

የድሬዳዋ አስተዳደር ካቢኔ ትላት ጠዋት ባካሄደው ስብሰባ ውሳኔ አስተላልፉል የድሬዳዋ አስተዳደር ካቢኔ ባካሄደው መደበኛ ስብሰባ በመሬትና መሬት ነክ ጉዳዮችን ተመልክቶ ውሳኔዎችን አሰተላልፏል፦ 1ኛ :- በአስተዳደሩ እየተሰሩ ለሚገኙ የልማት ኘሮጀክቶች በወረዳ 1 የመልካ ጀብዱ የልማት ተነሺዋች አካባቢያቸውን አፅድተው ለመንግስት በማስረከብ ለልማቱ ያላቸውን ተነሳሽነት እና የካሳ ክፍያውን በትዕግስት በመጠበቅ ላሳዩት ቀና ትብብር በአስተዳደሩ ስም ምስጋና በማቅረብ ከመጋቢት…

Read More

የጠቅላይ ሚኒስትሩ የኮሙኒኬሽን ዘዴ ለሥራ ተነሳሽነት የሚፈጥሩ ልምዶችን በማካፈል ላይ ያተኮረ ነው – የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት

የጠቅላይ ሚኒስትሩ የኮሙኒኬሽን ዘዴ ለሥራ ተነሳሽነት የሚፈጥሩ ልምዶችን በማካፈል ላይ ያተኮረ መሆኑን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት አስታውቋል፡፡ ጽ/ቤቱ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ላለፉት ሰባት ዓመታት ለየት ባለ መንገድ ግልጽነት እና ተደራሽነትን ዓላማ ያደረገ የኮሙኒኬሽን ዘዴ ሲያከናወኑ መቆየታቸውን አስታውሷል፡፡ ይህ የኮሙኒኬሽን ዘዴም በልዩ አተያይ ሐሳቦችን፣ ለሥራ ተነሳሽነት የሚፈጥሩ ልምዶችን እና ተግባራትን በማካፈል ላይ ያተኮረ መሆኑን ገልጿል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከክልሎች…

Read More

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በምሥራቅ ሐረርጌ ቆላማ አካባቢዎች እየለማ የሚገኝ የበጋ ስንዴ ልማትን ተመለከቱ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ዛሬ በምሥራቅ ሐረርጌ ቆላማ አካባቢዎች እየለማ የሚገኝ የበጋ ስንዴ ልማትን መመልከታቸውን ገልጸዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትሥሥር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት “መትጋት፣ መሥራት እና ማየት ከቻልን ኢትዮጵያ ከመረዳት አልፋ ሌሎችን መርዳት ትችላለች፤ ይህንን ሥራ አጠናክረን እንድንቀጥል አደራ እላለሁ” ብለዋል።

Read More

የወረዳ ምክር ቤቶች መደበኛ ጉባኤያቸውን አካሄዱ

#DGC የካቲት 30/2017 የድሬዳዋ አስተዳደር የከተማ ወረዳ ምክር ቤቶች 4ኛ የስራ ዘመን 4ኛ አመት 50ኛ መደበኛ ጉባኤያቸውን አካሂደዋል ። የ9 ወረዳ ምክር ቤት 50ኛ መደበኛ ጉባኤውን የ2017 በጀት አመት የ6ወር እቅድ ሪፖርት የቀረበ ሲሆን በመቀጠልም የተለያዩ አጀንዳዎች ላይም ተወያይተው አፅድቀዋል።

Read More

የድሬዳዋ አስተዳደር ንግድ፣ ኢንደስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ በጀርባ ሰፈር ባስገነባው የገበያ ማዕከል ሱቆች 29 ሰዎች እጣ ወጣላቸው

በድሬዳዋ አስተዳደር ንግድ፣ ኢንደስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ በጀርባ ሰፈር የተገነባው የገበያ ማዕከል የእጣ አወጣጥ ስነ-ስርአት በዛሬው ዕለት ተካሂዷል። በዚህም በመድረኩ የተገኙት የድሬዳዋ አስተዳደር ንግድ ኢንደስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ አብዲ ሙክታር እጣ የማውጣት ስነ ስርአቱ ግልፅና ፍትሀዊ በሆነ መልኩ መከናወኑን ገልፀው፤ 69 ሰዎች እጣ እንዲያወጡ ተደርጎ 29 እድለኞችም እጣ እንደወጣላቸው ተናግረው። እጣ ያሎጣላቸው ቀሪዎችም…

Read More