ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለመልክዓ ምድራችን የተስማሙ እና በአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ የታገዙ ድሮኖችን በራስ አቅም ማምረት መቻሉን አስታወቁ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ለመልክዓ ምድራችን የተስማሙ እና በአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ የታገዙድሮኖችን ኢትዮጵያ በራሷ አቅም ማምረት መቻሏን ገለጹ። አሁን ላይ የጦር ቴክኖሎጂ 4ኛ ትውልድ ላይ ደርሷል ያሉት ጠቅላይ ሚንስትሩ ይህን የሚመጥኑ የጦር ቴክኖሎጂ ውጤቶች በሀገር ልጆች ማምረት ተችሏል፤ ይህም ለኢትዮጵያውያን ብሎም ለአፍሪካውያን ጭምር የሚያኮራ ነው ብለዋል። ጦርነት ለማስቀረትም ሆነ በአጭር ጊዜ ለመጨረስ ዝግጁነት ትልቅ ሚና አለው…

Read More

በኢፌዴሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ምክትል አፈ ጉባኤ ሎሚ በደኦ የተመራ ልኡካን ቡድን ድሬዳዋ ገባ

ልዑክ ቡድኑ ድሬዳዋ የገባው በነገው እለት የሚከበረው ማርች 8 ፕሮግራም ላይ ለመሳተፍ ሲሆን፤ ዛሬ ከሰአትም የተለያዩ የልማት ስራዎችን ልኡክ ቡድኑ የሚጎበኝ ይሆናል። እንግዶቹ የድሬዳዋ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ ሲደርሱ በድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ክብርት ወ/ሮ ፈቲያ አደን እንዲሁም በድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት ምክትል አፈ ጉባኤ ክብርት ወ/ሮ ከሪማ አሊ እንዲሁም በአስተዳደሩ በየደረጃው በሚገኙ…

Read More

በሰላም ግንባታ ላይ እየተሰራ ያለው የተግባቦት ስራ ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ ተገለጸ::

በትልልቅ ሀገራዊ የልማት ስራዎች ላይ የተሰራው የተግባቦት ስራ በሰላም ግንባታ ላይም ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ ተገለጸ። የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት “ውጤታማ ተግባቦት ለኢትዮጵያ ልዕልና” በሚል መሪ ሀሳብ ከሚዲያና ኮሙኒኬሽን ዘርፍ አመራሮችና ባለሙያዎች ጋር ውይይት እያካሄደ ነው። በውይይት መድረኩ የመንግስት ኮሚኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴኤታ ከበደ ደሲሳ፣ በግማሽ ዓመቱ በዋና ዋና መንግስታዊ ጉዳዮች ላይ አጀንዳ የማስጨበጥ ተግባራት መከናወናቸውን ገልጸዋል።…

Read More

የብልፅግና ፓርቲ የስራ አፈፃፀም ግምገማ ዛሬም ቀጥሎ እየተካሄደ ነው

ሁለተኛ ቀኑን የያዘው የብልፅግና ፓርቲ የ2017 ዓ.ም በጀት ዓመት የ6 ወራት የስራ አፈፃፀም ግምገማ መድረክ እንደቀጠለ ነው። በመድረኩም የብልፅግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት አደም ፋራህን ጨምሮ የብልፅግና ፓርቲ ዋና ፅሕፈት ቤት የዘርፍ አመራሮች፣ የክልል ቅርንጫፍ ፅሕፈት ቤት ኃላፊዎች እንዲሁም የክልል የአደረጃጀት እና የፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊዎች ተገኝተዋል። በአጠቃላይ ሀገራዊ ፓለቲካ ሁኔታ፣ ጠንካራ ፓርቲ ግንባታ ለማሳካትና በፓርቲና በመንግሥት…

Read More

በድሬዳዋ አስተዳደር እየተከናወነ የሚገኘው የኮሪደር ልማት ስራዎች ያለበት ደረጃ በዛሬው እለት ተጎብኝቷል።

በድሬዳዋ አስተዳደር በሚገኙ የተለያዩ አካባቢዎች የኮሪደር ልማት ስራዎች በስፋት እየተሰሩ ሲሆን እነዚህም የኮሪደር ልማት ስራዎች ጥራታቸውን ጠብቀው ይሰሩ ዘንድም የክትትል እና ቁጥጥር ስራዎች ተጠናክሮ እየተከናወነ ይገኛል ። በዛሬው እለትም የድሬዳዋ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ እና የንግድ ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ ኃላፊ አቶ ሀርቢ ቡህን ጨምሮ ከፍተኛ የአስተዳደሩ አመራሮች ከሰብሪያ ሆቴል አንስቶ እስከ ፋይናንስ እየተሰራ ያለውን የኮሪደር ልማት…

Read More

/አደንዛዥ እጽን እና ሱሰኝነትን መከላከል የሁሉም ማህበረሰብ ኃላፊነት መሆኑ ተገለፀ::

የድሬ ፍሬዎች በጎ አድራጎት ማህበር ከድሬዳዋ ዩኒቨርስቲ ጋር በመተባበር ለህዳሴ አንደኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪዎች አደንዛዥ እጽን እና ሱሰኝነትን መከላከል ላይ ያተኮረ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጠ። በመድረኩ የተገኙት የድሬዳዋ አስተዳደር የወረዳ 06 ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ አባስ አሊ በሱስ ምክንያት የሚከሰቱ አደጋዎችን ለመቀነስ እንደነዚህ አይነት ግንዛቤን የሚያዳብሩ ስልጠናዎች ከፍተኛ አስተዋፆ እንዳላቸው ገልፀዋል። አቶ አባስ አያይዘውም አደንዛዥ…

Read More

የድሬዳዋ አስተዳደር ካቢኔ ዛሬ ባካሄደው መደበኛ ስብሰባ የተለያዩ ውሳኔዎችን አስተላልፏል።

1ኛ :- የሴቶችን አኮኖሚያዊ ችግሮች ለመቅረፍ በተለያዩ ገቢ ማስገኛ እንዲሰማሩ ለማስቻል በተቀረጸው ፕሮጀክት ዙሪያ ውይይት ተደርጎ አቅጣጫ የተሰጠበት ሲሆን 2ኛ:- የድሬዳዋ አስተዳደር የሰላም ምክር ቤት ማቋቋሚያ ደንብ ላይ ውይይት ተደርጎ ደንቡ እንዲፀድቅ ውሳኔ ተላልፏል። 3ኛ:- በተጨማሪም በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ካቢኔው በመወያየት ውሳኔዎችን አስተላልፏል። የድሬዳዋ አስተዳደር መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ።

Read More

በድሬዳዋ አስተዳደር የ2017 ዓ/ም የከተማ ሴፍቲኔትና ስራ ፕሮጄክት ስራ ማስጀመሪያ መርሃ ግብር ተከናዉኗል፡፡

ይህ ፕሮጄክት ፣ ከተረጂነት ተላቅቀው ስራ ፈጣሪና አምራች በሆኑ ነዋሪዎቿ የምስራቁ የሀገራችን ክፍል ተምሳሌት የሆነች ድሬዳዋን እውን ለማድረግ እየተከናወኑ ያሉ ስራዎች አካል መሆኑን የድሬዳዋ ከተማ ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ጀማል ኢብራሒም ገልጸዋል፡፡ ከአንድ ሺህ አራት መቶ በላይ አቅመ ደካሞች በቀጥታ ከሰባት ሺህ ስድስት መቶ በላይ ሰዎች ደግሞ በከተማ ጽዳትና ውበት ስራ የፕሮጄክቱ ተጠቃሚዎች እንደሚሆኑ…

Read More

በቀለአድ ክላስተር ሲከናወን የቆየው የበጋ ወራት የተቀናጀ የተፋሰስ ልማት ስራ በእውቅናና ሽልማት መርሀ ግብር ተጠናቀቀ

ሀገራዊ ለውጡን ተከትሎ የህዝብን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በልዩ ትኩረት እየተሰራባቸው ከሚገኙ ዘርፎች መካከል አንዱ የአፈርና ውሃ ጥበቃ ስራዎችን በማጠናከር ምርትና ምርታማነትን ማረጋገጥ ሲሆን “አፈራችን ለሀገራችን ብልፅግና”በሚል መሪ ቃል በቀለዓድ ክላስተር ለተከታታይ 30 ቀናት ሲከናወን የቆየው የ2017 ዓ.ም የበጋ ወራት የተቀናጀ የተፋሰስ ልማት ስራም በእውቅናና ሽልማት መርሀ ግብር ተጠናቋል። የተቀናጀ የበጋ ወራት የተፋሰስ ልማት ስራ እንደሀገር ልዩ…

Read More