በድሬዳዋ አስተዳደር የዝናብ ወቅት መራዘምን ጋር ተያይዞ የተከሰትውን ድርቅ ለመቅረፍ አፈጣኝ ምላሽ እየሰጠ እንደሚገኝ ተገለፀ ።
የዝናብ ወቅት መራዘምን ተከትሎ በገጠር ቀበሌዎች ንፁ የመጠጥ ውሀ አቅርቦት፣ የእንስሳት መኖ የሚደረገው ስርጭት ተጠናክሮ መቀጠሉን።በግብርና ውሃ ማእድንና ኢነርጂ ቢሮ የውሃ መስኖ ልማት ፅ/ቤት ሃላፊ አቶ ፉአድ መሃመድገልጸዋል። ችግሩን ለመቋቋም እየተደረገ ባለው ጥረት ቀድሞ በተደረጉ ዳሰሳዊ ጥናቶችን መሰረት በማድረግ በተለይ ከውሃና ከመስኖ ልማት ጋር በተያያዘ ያሉ አማራጮችን በሙሉ አቅም ጥቅም ላይ ለማዋል እየተሰራ እንደሚገኝ ሓላፊው…


