የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የኃይል ማስተላለፊያ መስመር ዝርጋታ ተጠናቀቀ::
650 ኪሎ ሜትር የሚረዝመው የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የኃይል ማስተላለፊያ መሥመር ዝርጋታ ሙሉ በሙሉ መጠናቀቁ ተገለጸ፡፡ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ከኃይማኖት አባቶችና ከሲቪክ ማኅበራት ጋር ግድቡን በተመለከተ ዛሬ ውይይት አድርጓል፡፡ በዚህ ውይይት ላይ የኃይል መሥመር ዝርጋታው ከግድቡ ከተገነባበት ጉባ አንስቶ ብሔራዊ የኤሌክትሪክ ኃይል ቋት እስከሚገኝበት ሆለታ ድረስ ተዘርግቷል ተብሏል፡፡ የግድቡ ተደራዳሪዎች ቴክኒክ ቡድን አባል ዶክተር በለጠ…


