የኢድ አልፈጥር በአል ሲከበር ያለው የሌለውን በመርዳት እንዲሁም በፈጣሪ ዘንድ የሚወደዱትን ተግባራት በመፈፀም ሊሆን እንደሚገባ ተገለፀ፡፡
1442 ተኛው የኢድ አልፈጥር በአል በድሬዳዋ አስተዳደር የእምነቱ ተከታዮች በተገኙበት በታላቅ ድምቀት ተከብሯል፡፡ በድሬዳዋ አስተዳደር የኢድ አልፈጥርን በአል ለማክበር ከማለዳው 12 ሰዓት አንስቶ የእምነቱ ተከታዮች በከተማው በሚገኘው የኢድ ሰላት መስገጃ ስፍራ በሚያመሩበት ወቅት ተከቢርታ ወይም የአላህን ትልቅነት በማውሳት ወደ መስገጃ ስፍራው አምርተዋል፡፡ በኢድ ሰላት መሰገጃ ላይም በመገኘት ለእምነቱ ተከታዮች መልእክት ያስተላለፉት የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ አቶ…


